Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
333 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
‎‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ሁሉን አቀፍ ምድራዊ ገነት!

‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ’ገበታ ለትውልድ’ ውጥን አካል የሆነው ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’፤ ማህበረሰብን ለማበልጸግና ሀገራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለራዕይ መሪ የአመራር ጥበብና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ምስክር ነው።

‎ ሎጅው በተለያዩ የፍራፍሬ እና የደን ዛፎች በለመለመ 78,000 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ተፈጥሯዊ የ"ሰማያዊ ዓይን" ፍልውሃ መዋኛ፣ ሁለት ግዙፍ ሰው ሰራሽ ሐይቆችና 3.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የእግር ጉዞ (ሀይኪንግ) ምቹ መንገድ አካቷል።

‎የማረፊያ ክፍሎቹንም በተመለከተ፦ የግል መዋኛ ገንዳ ያላቸው ሁለት ፕሬዝዳንታዊ ቪላዎች፣ አስራ ሁለት እርስ በእርስ የተያያዙ የመኝታ ክፍሎች እና አስራ ስድስት ባለ አንድ መኝታ ቤቶችን ይዟል። በተጨማሪም ዘመናዊ የምግብ አዳራሾች፣ የእንግዳ መቀበያ ህንፃ፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የቢሮ ክፍሎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ እና ሁለት ሄሊኮፕተሮችን በአንድ ጊዜ ማሳረፍ የሚችል ስፍራ (ሄሊፓድ) ያካተቱ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል።

‎ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ከቱሪስት መዳረሻነቱ ባለፈ፣ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰትን በመሳብ ታላላቅ ጉባዔዎችን ለማስተናገድ ተደማሪ ዐቅም ነው። ‎በመስተንግዶ እና በአገልግሎት ዘርፎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለአካባቢው ኢኮኖሚ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ሲሆን ፕሮጀክቱ በጠንካራ አመራር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መዳረሻን የማቅረብ የገበታ ለትውልድ መርሃ-ግብር ርዕይን ሰንቆ ቀጣይነት ላለው ቀጣናዊ ዕድገት እንደ ወሳኝ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።

#PMOEthiopia #VisitEthiopia #EthiopiaDelivers
በፍራፍሬና በደን ዛፎች የተከበበው የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ጉብኝት። ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ያለው ቅርበ የጎብኝዎችን ምቾት ከመጨመሩም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

#ገበታ_ለትውልድ #PMOEthiopia #VisitEthiopia #EthiopiaDelivers
1👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቃና ቲቪ ጋር በኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ያደረጉትን ልዩ ቆይታ ይከታተሉ! በውይይቱ የከተማ ፕላን፣ የዘላቂ ልማት እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነ፤ እንዲሁም የመሠረተ ልማትን፣ የንግድና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በመላው ሀገሪቱ ለማሳደግ ያላቸው ፋይዳ በጥልቀት ይዳሰሳል!

መጋቢት 15 ከምሽቱ 2:30 ላይ!

Join Prime Minister Abiy Ahmed Ali for an exclusive discussion with Kana TV on the future of Ethiopian cities! Explore how urban planning, sustainable development, and corridor projects are transforming Addis Ababa and beyond; boosting infrastructure, trade, and economic opportunities across the country.

March 24th at 8:30pm!

#PMOEthiopia
7👍3