ሐዋሳ እና ብስክሌተኞቿ
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በኢትዮጵያ ከተሞች ብስክሌትን አዘውትረው የመጠቀም ባህል ካዳበሩ ነዋሪዎች መካከል የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ይጠቀሳሉ። በከተማዋ የተሰራው የኮሪደር ልማት ሥራ ዘመናዊነትን እንድትጎናጸፍ ፣ እንድትዋብና ምቹ እንድትሆን ያደረጋት ሲሆን፤ ጎዳናዎቿ ብስክሌት የሚጋልቡ አብዮተኞች እንዲበራከቱ አስችሏታል፡፡ በብስክሌት እየተጓዙ ጤናቸውን የሚጠብቁ እየተዝናኑ ነዳጅን የሚቆጥቡ የከተማዋ ነዋሪዎችም እየበዙ መጥተዋል፡፡ እርዎስ? እርስዎ የሚኖሩበት ከተማስ?

❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከሉሲ እስከ ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ፤ የአፋር ስጦታ!
ዛሬ በአፋር ክልል የ'’ገበታ ለትውልድ’' ፕሮጀክታችን አካል የሆነውንና የሰው ልጅ ታሪክ ከጀመረበት ጥንታዊ ምድር የተገነባውን ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ለመመረቅ ተገኝተናል።
የከባቢው ጸጋ የተገለጠበት ይኽ ስራ የቱሪዝም ልህቀትና የግብርና ዘርፍ መነቃቃትን አዲስ ምዕራፍ በማብሰር፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ይበልጥ ጎልታ እንድትታይ የማድረግ ከፍተኛ ዐቅም አለው!
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ሁሉን አቀፍ ምድራዊ ገነት!
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ’ገበታ ለትውልድ’ ውጥን አካል የሆነው ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’፤ ማህበረሰብን ለማበልጸግና ሀገራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለራዕይ መሪ የአመራር ጥበብና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ምስክር ነው።
ሎጅው በተለያዩ የፍራፍሬ እና የደን ዛፎች በለመለመ 78,000 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ተፈጥሯዊ የ"ሰማያዊ ዓይን" ፍልውሃ መዋኛ፣ ሁለት ግዙፍ ሰው ሰራሽ ሐይቆችና 3.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የእግር ጉዞ (ሀይኪንግ) ምቹ መንገድ አካቷል።
የማረፊያ ክፍሎቹንም በተመለከተ፦ የግል መዋኛ ገንዳ ያላቸው ሁለት ፕሬዝዳንታዊ ቪላዎች፣ አስራ ሁለት እርስ በእርስ የተያያዙ የመኝታ ክፍሎች እና አስራ ስድስት ባለ አንድ መኝታ ቤቶችን ይዟል። በተጨማሪም ዘመናዊ የምግብ አዳራሾች፣ የእንግዳ መቀበያ ህንፃ፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የቢሮ ክፍሎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ እና ሁለት ሄሊኮፕተሮችን በአንድ ጊዜ ማሳረፍ የሚችል ስፍራ (ሄሊፓድ) ያካተቱ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል።
ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ከቱሪስት መዳረሻነቱ ባለፈ፣ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰትን በመሳብ ታላላቅ ጉባዔዎችን ለማስተናገድ ተደማሪ ዐቅም ነው። በመስተንግዶ እና በአገልግሎት ዘርፎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለአካባቢው ኢኮኖሚ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ሲሆን ፕሮጀክቱ በጠንካራ አመራር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መዳረሻን የማቅረብ የገበታ ለትውልድ መርሃ-ግብር ርዕይን ሰንቆ ቀጣይነት ላለው ቀጣናዊ ዕድገት እንደ ወሳኝ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
#PMOEthiopia #VisitEthiopia #EthiopiaDelivers

በፍራፍሬና በደን ዛፎች የተከበበው የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ጉብኝት። ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ያለው ቅርበ የጎብኝዎችን ምቾት ከመጨመሩም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#ገበታ_ለትውልድ #PMOEthiopia #VisitEthiopia #EthiopiaDelivers

❤1👍1