Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
333 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“የትግራይ ወጣቶች ጦርነት በቃን የሚል ድምጽ እያሰሙ ነው”

- አቶ ጌታቸው ረዳ
++++++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች የኋላቀር ቡድኑን የጦርነት ጉሰማ "በቃን" በሚል ድምፅ እየተቃወሙት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

አቶ ጌታቸው አዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ወጣቶች ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ ትግራይ ውስጥ ያለው ወጣት አሁንም ጦርነት በቃን የሚል ድምፁን እያሰማ በመሆኑ፣ ጦርነት የሚሰብከውን ኋላቀር ቡድን "ሰላም" በሚል ቃል ልናሸንፈው ይገባል።

ባለፉት 30 ዓመታት ጦርነትን በመሸሽ የተጀመረው ስደት ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሄዱ ማድረጉን ያስታወሱት አማካሪው፤ አሁን ባለው ሁኔታም በትግራይ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ተሰድደው ለማለቅ ሦስት ዓመት የሚፈጅባቸው እንደማይመስል በመግለጽ የሁኔታውን አሳሳቢነት አብራርተዋል።

ውይይት መፍትሔ ማስገኛ ዘዴ ቢሆንም ወደ ተግባር ካልተቀየረ ልምድ ሆኖ እንደሚቀር የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ የተደራጁ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ በጦርነት ቀስቃሾች ላይ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ጌታቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ማንኛውንም ፓርቲ ወይም አደረጃጀትን ወክለው ሳይሆን፤ ትግራይን በማዳኑ ሂደት የሁሉም ድርሻ አስፈላጊ መሆኑን ስለሚያምኑ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጦርነትን አንፈልግም የሚለው የወጣቶች ድምፅ መቐለ መሽጎ ጦርነት የሚሰብከውን ቡድን ሊያስደነግጠው እንደሚችል የገለጹት አማካሪው፤ ወጣቱ ድምፁን ይበልጥ ማሰማትና ለሰላም መደራጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በሔርሞን ፍቃዱ
+++++++++++++++++++

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ #ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰላም #ጦርነት_በቃን #ጌታቸው_ረዳ #ኢትዮጵያ
3😁1
ነእፓ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አሸንፎ መንግሥት ከሆነ እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓትን እንደሚተገብር አስታወቀ
+++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በመጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸንፎ መንግሥት የሚመሠርት ከሆነ፣ እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓትን በተግባር ለመተርጎም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የፓርቲው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሮ ነቢሃ መሀመድ ከጋዜጣ ፕላስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ እውነተኛ የፌዴራሊዝምና አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን ማረጋገጥ ከተቻለ ስለ ክፍፍል የሚነሱ ሥጋቶችን ማስቀረት ይቻላል።

ለዚህም ፓርቲያቸው የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕና የእኩልነት ሥራዎችን በትኩረት ለማከናወን ማቀዱን ገልጸዋል።

አካታች የማኅበረ-ኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት ለሕዝቦች አንድነትና ለሀገር ሉዓላዊነት መሠረት መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ነቢሃ፤ ልዩነትን እንደ ችግር ከመውሰድ ይልቅ የውበት ምንጭ መሆኑን መረዳት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

እንደ ኃላፊዋ ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት የሚረጋገጠው በልዩነት ውስጥ አንድነትና ብርታት እንዳለ ሲታወቅ ነው።

በመሆኑም ነእፓ አብሮነትን፣ መተባበርንና የቀድሞውን የኢትዮጵያዊነት ማንነት ማምጣት የሚያስችሉ፣ እንዲሁም ዜጎችን ወደ ሥራ የሚያስገቡ የፖሊሲ አማራጮችን በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
++++++++++++++++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ጋዜጣ_ፕላስ #ነእፓ_ፓርቲ #ምርጫ_2018 #ፌዴራሊዝም #ኢትዮጵያ #ኢኮኖሚ
7🤣2👎1
ለዲጂታሉ ዓለም ዝግጁ - ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 | Ready for the Digital World - Digital Ethiopia 2030

በመደመር መንፈስ እየተመራን፣ የጋራ ጥረታችንን ለሀገራዊ ዕድገት በመቀየር በዲጂታሉ ዓለም ዕድሎችን ለመወሰን ዝግጁ የሆነች ኢትዮጵያ እየገነባን ነው።

#DigitalEthiopia2030 #PMOEthiopia
1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሰተላለፉ
+++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ዒድ አል ፈጥር የበረከት በዓል ተደርጎ ይታመናል። ሮመዳንም የአላህ (ሱወ) ደግነት የሚገለጥበት፣ ውድ ስጦታዎችን ለሰው ልጆች የሰጠበት ወር ነው። ቁርአን ወደ ምድር የወረደበት፣ ጀሃነም ተዘግቶ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ ሁሉም እንደ እምነቱ ጽናትና እንደ አላህ (ሱወ) እዝነት ምናዳዎችን የሚያገኝበት ወቅት በመሆኑ ሕዝበ ሙስሊሙ ዘወትር የሮመዳንና ዒድ አል ፈጥርን መምጣትን በጉጉት ይጠብቃል።
በዒድ አል ፈጥር ከፈጣሪ በረከት የሚቸራቸው የሮመዳንን ወር በፆምና በዱዓ ያሳለፉት ናቸው፤ በበዓሉ መምጣት የሚያደሰቱትም ሮመዳንን በመልካም ተግባር ለማሳለፍ የበረቱ ናቸው። በተቀደሰው ወር ከክፋት የተቆጠቡ፤ ለድኾችና አቅመ-ደካሞች ዘካት የሰጡ፤ የበደሏቸውን ይቅር ለማለት የደፈሩ በሐሴትና በመንሳዊ ኃይል ተሞልተው ለዒዱ ይደርሳሉ። በተቃራኒው ለዱዓ የሰነፉና ለመስጠት የሰሰቱ ከፈጣሪ በረከት አያገኙም።
ከፊታችን ግንቦት ላይ የሚካሄደው ምርጫ ሀገራችንን የዴሞክራሲን ድል የምትቀዳጅበት፣ ወደ ቀጣይ ብሩህ ዘመንዋ የምትሸጋገርበት በር ነው። እንደ ሀገር ለዓመታት ዴሞክራሲን ስንናፍቅ ኖረናል። ጉዞአችን አልጋ በአልጋ አልነበረም። ነገር ግን ከፈተና በሁዋላ በረከት፣ ከብርታት በኋላ ሐሴት እንዳለ ከሮመዳን ጾምና ከዒድ አል ፈጥር በዓል እንማራለን።
መልካም የዘራ ሰው መልካም ምርት እንደሚያጭድ ሁሉ፤ እሾክ የዘራውም አሜኬላ ያጭዳል። ስለተመኘን ብቻ አሜኬላው በመልካም ሰብል አይለወጥም። በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ ዘርና ምርት የተቆራኙ ናቸው። ስለዴሞክራሲም ስናስብ ይሄንን ሐቅ መዘንጋት የለብንም። የምንገነባው ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት የሚወሰነው በቅድመ ምርጫ ተሳትፎአችን ልክ ነው።
ተሳትፎአችን ከጠየመ ዴሞክራሲያችንም ይጠይማል። ደካማ ተሳትፎ አድርገን ጠንካራ ዴሞክራሲ ለማዋለድ መመኘትም ሞኝነት ነው። ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በባዶ መሬት አይበቅልም፤ በግጭትና ሥርዓት አልበኝነትም አይገነባም። ይልቁንም ስክነትን፣ ለትብብርና ቅንጅት ልብን ክፍት ማድረግን፣ በጨዋታው ሕግ መመራትን ይጠይቃል።
ሮመዳን ቤተሰብ የሚገናኝበት፣ ኅሊና የሚሰበሰብበት፣ ሰውነት የሚገራበት እና መንፈስ የሚቀናበት ወር ነው። ዒድ አል ፈጥር ደግሞ የሰውን ልጅ ጤናማ ግንኙነቶች የሚያመለክት በዓል ነው። የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር፣ ከራሱ ጋር እና ከወገኑ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ጤናማ ካልሆነ ጠቅላላ ሕይወቱ ጤናማ አይሆንም። በሮመዳን ወቅት ጾሙ ሰዎችን ከራሳቸው ጋር ያገናኛቸዋል፤ ሰላትና ዱአ ከፈጣሪያቸው ጋር ያገናኛቸዋል፤ አፍጣርና ዘካት ደግሞ ከማኅበረሰቡ ጋር ያገናኛቸዋል። ኢትዮጵያውያን ጤናማ ሕይወትን መምራት እንድንችል እነዚህን ሦስቱን ጤናማ ማድረግ አለብን።
ሰው ከፈጣሪው እና ከራሱ ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ ካልሆነ ለማኅበረሰብም ለሀገርም ጠንቅ ነው። ሰው ከራሱ ጋር እየተጋጨ ከኖረ ከሁሉም ጋር ይጋጫል።
ዛሬ ጦርነትን ባህል፣ ዝርፊያን ልማድ፣ ጥፋትን ዕሴት፣ ውድመትን ክብር አድርገው የሚኖሩት ሰዎች የመጀመሪያው ችግራቸው ከፈጣሪያቸውና ከራሳቸው ጋር አለመስማማት ነው። ውስጣዊ ባሕርያቱ ያልተስማሙለት ሰው ከማንም ጋር አይስማማም። ዕርቅ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ መግባባት እና መስማማት የሚባሉት ነገሮች አይገቡትም።
ሰው ከፈጣሪውና ከራሱ ጋር ከተስማማ፣ ከማንም ጋር መስማማት ይችላል። ከእንስሳትም ጋር ሳይቀር። “ለድንቢጥ እንኳን ቢሆን የራራ ሰው፤ በፍርድ ቀን (ቂያማህ) አላህ ይራራለታል” ሲሉ ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩት ለዚህ ነው። የእስልምና ዋናው መሠረቱ ሰላም የሆነው ለዚህ ነው። ሰላም ማለት ከራስና ከአካባቢ ጋር በጤናማ ግንኙነት ለመኖር መቻል ነውና።
የዘንድሮውን የዒድ በዓል ስናከብር በዓለማችን ስለ ሰላም የሚነገረውን ያህል የዓለም ሕዝቦች በሰላም መኖር ለምን አልቻሉም ብለን እንጠይቅ? የግጭትና የጦርነት ድንጋይ እየደጋገመ ለምን ይመታናል? ከአዛኝ ይልቅ ገዳይን እንደ ጀግና የሚያየው ልምምዳችን ለምን ገናና ሆነ? የሰው ልጅ ከግጭትና ከጦርነት ያተረፈው ድህነትና ኋላ ቀርነት መሆኑን እያየን ለምን አልተማረንም? ሠልጥኗል በምንለው ዓለም የሚኖሩ ወገኖቻችን እንዴት ግጭትንና ጦርነትን የሚያበረታቱ ሆኑ? ይህ ትውልድ እነዚህን ጥያቄዎች በሚገባ አጢኖ ምላሽ ሊያገኝላቸው ይገባል።
ከራሳቸው ጋር ሰላም ያጡ አካላት የማኅበረሰቡን ሰላም እንዲረብሹ ልንፈቅድላቸው አይገባም። ከሮመዳን ዕሴቶች ጋር የተጣሉ ሰዎች ዘመኖቻችንን እንዲረብሹ ልንፈቅድላቸው አይገባም። በዐሥራ ሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መኖር ቀድሞ መገኘት ነው። በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን እንደ ዐሥራ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን መኖር ግን መረገም ነው።
መግደል፣ ማገት፣ የገበሬውን እርሻ ማቃጠል፣ ሴቶችን መድፈር፣ ማኅበራዊ ተቋማትን መመዝበር፣ ቅርስና ታሪክን ማበላሸት፣ ጠመንጃን የሁሉም ነገር መድኃኒት አድርጎ መውሰድ፣ እነዚህ ሁሉ ከ800 ዓመታት በፊት ያለፉ የሰው ልጅ ጠባያት ናቸው።
ከሦስት አካላት ጋር የታረቁ ሰዎች ብርቱዎች ናቸው ይባላል፤ ከራሳቸው፣ ከማህበረሰባቸው እና ከፈጣሪያቸው ጋር። እንደ ኢትዮጵያዊ እኛም ራሳችንን የገዛን፣ ፈጣሪን የምንፈራ እና ለማህበረሰብ ሰላምና እድገት የምንጨነቅ መሆን አለብን። ኢትዮጵያ የምታድግና የምትበለጽገው በዜጎችዋ እንጂ በሌላ አይደለም።
ዜጎችዋ ሲገነቡ ትገነባለች፤ ዜጎችዋ ሰላም ሲሆኑ ሰላም ትሆናለች፤ ዜጎችዋ ሲስማሙ የብልጽግና ጉዞዋ ይሰምራል። የኢትዮጵያም መበልጸግ የሌላ ሳይሆን የእኛ መበልጸግ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚፈለግብንን መሥዋዕትነት ሁሉ የመክፈል ኃላፊነት የእኛ ነው።
የእኛ ልፋት ከዛሬ አልፎ ለትውልድ ይተርፋል። ሀገር መውደዳችን የሚታወቀው እና መልካም ዜግነታችን የሚገለጠው በሥራችን ነው። ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) “ምርጥ ሰዎች ማለት ሌሎችን ለመጥቀም የበረቱ ሰዎች ናቸው” ብለው ያስተማሩትም ለዚህ ነው።
ይሄን የዒድ አል ፈጥር በዓል እነዚህን መልካም ዕሴቶች እያሰብን፣ ሦስቱን ጤናማ መሥመሮችንም እያጸናን እንድናከብረው አደራ እላለሁ።
በድጋሚ መልካም የዒድ አል ፈጥር በዓል ይሁን!
ዒድ ሙባረክ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መጋቢት ፣ 2018 ዓ.ም
5
“በኢትዮጵያ የሚከበረው ዒድ አል-ፈጥር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የሚታደምበት በዓል ነው”

- ፕሮፌሰር አደም ካሚል
+++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በኢትዮጵያ የሚከበረው ዒድ አል-ፈጥር እንደ መካና መዲና በዓለም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በጋራ የሚታደምበት ታላቅ በዓል መሆኑን የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል ገለጹ።

ፕሮፌሰር አደም ከጋዜጣ ፕላስ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳብራሩት፤ የረመዳን ጾም ሕዝበ ሙስሊሙ ለ30 ቀናት በመጾም ከፈጣሪው ምሕረት የሚጠይቅበት ታላቅ ወቅት ነው።

ጾሙን ያጠናቀቀው ምእመን የዒድ አል-ፈጥርን በዓል ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ሴት ወንድ ሳይል በአደባባይ በአንድነት የሚያከብረው ልዩ በዓል መሆኑን ተናግረዋል።

ከበዓሉ አንድ ቀን አስቀድሞም አቅም ለሌላቸው ወገኖች ዘካ በመስጠት የተግባራዊ መረዳዳት ሥርዓት የሚከናወንበት መሆኑንም አውስተዋል።

ዓለም አሁን እያስተናገደች ያለውን የሰላም እጦትና የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ፣ ወቅቱ ከምንጊዜውም በላይ ጸሎት የሚደረግበት መሆኑን ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያም ፍጹም ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ያላቸውን ከፍተኛ ምኞት አክለዋል።

የዒድ አል-ፈጥር በዓል ብሔር፣ ቋንቋና ቀለም ሳይለይ ሕዝበ ሙስሊሙ በአንድነት ፈጣሪን የሚያመሰግንበት በመሆኑ፤ ማኅበረሰቡ በዓሉን እርስ በርስ በመረዳዳት፣ በመጠያየቅና በመተሳሰብ እንዲያከብር ፕሮፌሰር አደም ጥሪ አቅርበዋል።

በሰለሞን ወልዴ
#ዒድ_አል_ፈጥር #ረመዳን #ኢትዮጵያ
1
#የዒድ_አልፈጥር_በዓል

1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
7👍1
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
👍6