Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
333 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የዱባይ ገዢ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ግርማዊ ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱምን አግኝቼ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
‎በሁለቱ ሀገሮቻችን እና ሕዝቦቻችን መካከል ስላለው ጠንካራ የቢዝነስ፣ ትምህርት እና ባህል ትስስር ተነጋግረናል። ከዚህች ጠንካራ፣ ውብ እና ጽኑ ከተማ ጋር ያለን ትስስር በቀጣይ ጉብኝቶችም ይጠናከራል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
10👍3
በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል። በመሆኑም ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል።
በመሆኑም የነዳጅ አከፋፋዮች፣ማደያዎችና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በሃላፊነት ስሜት እንድንጠቀም ለማሳሰብ እወዳለው።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍3😁2
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
Photo
“ወድቆ መቅረት የለም”፤ ከሥልጣን እስከ መቄዶንያ
+++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ሕይወት እንዲህ ናት፤ ከፍታን በቀኟ ከያዘች በግራዋ ዝቅታን ይዛ እንካችሁ ማለት ልመዷ ነው።
ይህ አባባል የቀድሞው ባለስልጣን አሁን በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት የአቶ መላኩ አሰፋ የሕይወት ምስክርነት ሊሰጡበት የሚያስችል ነው።
አቶ መላኩ አሰፋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሲወጡ ትልቅ ራዕይ አንግበው ነበር የወጡት።
በኢትዮጵያ ማዕድን ሀብት ልማት ኮርፖሬሽን ውስጥ ለ10 ዓመታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። የኢትዮጵያን ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽንን በምክትል ፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ወክለው ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትሮች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተደራድረዋል፤ ተወያይተዋል።
የሰው ልጅ ሕይወት ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለምና በኋላ ግን የአቶ መላኩ ሕይወት በዚህ ልትቀጥል አልቻለችም።
አቶ መላኩን ከባድ የአዕምሮ ሕመም ገጠማቸው። ያ ሁሉ ዝና፣ ያ ሁሉ ሥልጣንና እውቀት በሕመሙ ጥላ ሥር ተሸፈነ።
በአንድ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሟገቱት ግለሰብ፣ ሕመም አሸንፏቸው ጎዳና ላይ ለመውደቅ በቁ።
ከውድቀትም በኋላ ትንሳኤ ከሕመምም በኋላ ፈውስ አለና አቶ መላኩ በሕመሙ ተሸንፈው አልቀሩም። ወደመቄሄዶንያ ገቡ፡፡
በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር ባገኙት ፍቅር፣ እንክብካቤና ሕክምና ዳግም ለመወለድም ታደሉ። አእምሯቸው ተመልሶና ማንነታቸውን መልሰው በማግኘት ዛሬ ለመቄዶንያ ትልቅ ውለታ እየመለሱ ይገኛል።
በአሁኑ ጊዜ አቶ መላኩ በመቄዶንያ ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያና የስክሪፕት ጸሐፊ ናቸው።
በፋና እና በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚተላለፉ የመቄዶንያ የአየር ሰዓቶች ላይ ከ70 በላይ ስክሪፕቶችን አዘጋጅተዋል። በተጨማሪም ዶክመንተሪዎችንና ቃለ መጠይቆችን በብቃት ያከናውናሉ።
አቶ መላኩ መቄዶንያ ከበጎ አድራጎት ማኅበርነት አልፎ ወደ "ቻሪቲ ቪሌጅ" (Charity Village) እንዲያድግ የራሳቸውን ሙያዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ያስረዳሉ።
"መቄዶንያ የኢትዮጵያውያን የበጎነት ጥግ የታየበት፣ የሀገርን ሸክም የተሸከመ ተቋም ነው" ሲሉ መቄዶንያን ይገልጹታል።
"እኔ ድኜ ዛሬ እዚህ ሥራ ላይ ብገኝም፣ ነገ ለማንም ምን እንደሚመጣ አይታወቅም። ስለዚህ ሰውን አትናቁ፣ መቄዶንያን ደግሞ ደግፉ" ሲሉም መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ።
በክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ የተመሰረተው መቄዶንያ እንደአቶ መላኩ አይነት በርካታ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፉ ግለሰቦችን ያስጠለለ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልል ከተሞችም ቅርንጫፎችን ከፍቶ ሰውን ከጎዳና እያነሳ እየጦረ ይገኛል፡፡
መቄዶንያ ከመጋቢት 6 ጀምሮ የገበያ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህም ተቋሙ ለጀመረው ባለ 15 ወለል ሆስፒታል እና በክልል ከተማ እየተገነቡ ላሉ ቅርንጫፎች ማስጨረሻ የሚሆን ነው፡፡
መላው ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም በገቢ ማሳባሰቢያው በመሳተፍ ተቋሙን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በሄለን ወንድምነው
9👏2🥰1
"ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት አድርገናል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍153😁3
“የትግራይ ወጣቶች ጦርነት በቃን የሚል ድምጽ እያሰሙ ነው”

- አቶ ጌታቸው ረዳ
++++++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች የኋላቀር ቡድኑን የጦርነት ጉሰማ "በቃን" በሚል ድምፅ እየተቃወሙት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

አቶ ጌታቸው አዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ወጣቶች ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ ትግራይ ውስጥ ያለው ወጣት አሁንም ጦርነት በቃን የሚል ድምፁን እያሰማ በመሆኑ፣ ጦርነት የሚሰብከውን ኋላቀር ቡድን "ሰላም" በሚል ቃል ልናሸንፈው ይገባል።

ባለፉት 30 ዓመታት ጦርነትን በመሸሽ የተጀመረው ስደት ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሄዱ ማድረጉን ያስታወሱት አማካሪው፤ አሁን ባለው ሁኔታም በትግራይ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ተሰድደው ለማለቅ ሦስት ዓመት የሚፈጅባቸው እንደማይመስል በመግለጽ የሁኔታውን አሳሳቢነት አብራርተዋል።

ውይይት መፍትሔ ማስገኛ ዘዴ ቢሆንም ወደ ተግባር ካልተቀየረ ልምድ ሆኖ እንደሚቀር የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ የተደራጁ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ በጦርነት ቀስቃሾች ላይ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ጌታቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ማንኛውንም ፓርቲ ወይም አደረጃጀትን ወክለው ሳይሆን፤ ትግራይን በማዳኑ ሂደት የሁሉም ድርሻ አስፈላጊ መሆኑን ስለሚያምኑ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጦርነትን አንፈልግም የሚለው የወጣቶች ድምፅ መቐለ መሽጎ ጦርነት የሚሰብከውን ቡድን ሊያስደነግጠው እንደሚችል የገለጹት አማካሪው፤ ወጣቱ ድምፁን ይበልጥ ማሰማትና ለሰላም መደራጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በሔርሞን ፍቃዱ
+++++++++++++++++++

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ #ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰላም #ጦርነት_በቃን #ጌታቸው_ረዳ #ኢትዮጵያ
3😁1
ነእፓ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አሸንፎ መንግሥት ከሆነ እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓትን እንደሚተገብር አስታወቀ
+++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በመጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸንፎ መንግሥት የሚመሠርት ከሆነ፣ እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓትን በተግባር ለመተርጎም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የፓርቲው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሮ ነቢሃ መሀመድ ከጋዜጣ ፕላስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ እውነተኛ የፌዴራሊዝምና አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን ማረጋገጥ ከተቻለ ስለ ክፍፍል የሚነሱ ሥጋቶችን ማስቀረት ይቻላል።

ለዚህም ፓርቲያቸው የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕና የእኩልነት ሥራዎችን በትኩረት ለማከናወን ማቀዱን ገልጸዋል።

አካታች የማኅበረ-ኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት ለሕዝቦች አንድነትና ለሀገር ሉዓላዊነት መሠረት መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ነቢሃ፤ ልዩነትን እንደ ችግር ከመውሰድ ይልቅ የውበት ምንጭ መሆኑን መረዳት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

እንደ ኃላፊዋ ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት የሚረጋገጠው በልዩነት ውስጥ አንድነትና ብርታት እንዳለ ሲታወቅ ነው።

በመሆኑም ነእፓ አብሮነትን፣ መተባበርንና የቀድሞውን የኢትዮጵያዊነት ማንነት ማምጣት የሚያስችሉ፣ እንዲሁም ዜጎችን ወደ ሥራ የሚያስገቡ የፖሊሲ አማራጮችን በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
++++++++++++++++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ጋዜጣ_ፕላስ #ነእፓ_ፓርቲ #ምርጫ_2018 #ፌዴራሊዝም #ኢትዮጵያ #ኢኮኖሚ
7🤣2👎1
ለዲጂታሉ ዓለም ዝግጁ - ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 | Ready for the Digital World - Digital Ethiopia 2030

በመደመር መንፈስ እየተመራን፣ የጋራ ጥረታችንን ለሀገራዊ ዕድገት በመቀየር በዲጂታሉ ዓለም ዕድሎችን ለመወሰን ዝግጁ የሆነች ኢትዮጵያ እየገነባን ነው።

#DigitalEthiopia2030 #PMOEthiopia
1