Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
333 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የእመርታ ቤተ መጻሕፍት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመደመር መጻሕፍት ሽያጭ እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተገኘ በጀት የተገነባ ፕሮጀክት ነው።

ቤተ መጻሕፍቱ ከ1ሺ ካሬ ሜትር በላይ የቦታ ስፋት ላይ ያረፈ እና ዘመናዊ መሠረተ ልማት እንዲኖረው ተደርጎ ተገንብቷል። ሶስት የወለል ብዛት የያዘው እመርታ ቤተ መጻሕፍት፤ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ተስማሚ የሆነውን የድሬን አየር እያገኙ እንዲገለገሉም የቴራስ ቦታ ተዘጋጅቶለታል።

‎ቤተ- መጻሕፍቱ የብሬል ማንበቢያ ቦታ፣ ለልዩ ፍላጎት ተጠቃሚዎች የተዘጋጀ የአይቲ ማዕከል፣ ከክፍል ውጭ የንባብ ቦታ፣ የግል እና የቡድን ማንበቢያ እና የጥናት ክፍሎች፣ እንዲሁም የኮንፈረንስ ክፍልን አካቷል።

በአጠቃላይ እመርታ ቤተ-መጻሕፍት በአንድ ጊዜ ለ1ሺህ ሰው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሆኖ የተገነባ ሲሆን በመጽሐፍ መደርመሪያው ላይ ብቻ 1ሚሊየን መጻሕፍትን የመያዝ አቅም አለው።

#PMOEthiopia
👍63
በሀረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሠራው የገጠር ኮሪደር ሥራ በአካባቢው በተገኙ ቁሳቁሶች፤ በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወነ የአነስተኛ መንደር ሞዴል ክንውን ነው። የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ እቅድና ተግባራዊ የአሰራር ውጤት ያሳየ ነው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍84
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"በሀረር ከተማ የተቋቋመው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ ሀገር አቀፍ መርሃ ግብር አካል ነው።

በሀረር የመሶብ ማዕከል 8 ተቋማት በ24 የአገልግሎት መስኮቶች 67 የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎቶችን በአንድ ስፍራ ለተገልጋይ ያቀርባል።

ይኅው ሀገራዊ አፈፃፀም የመንግሥት አገልግሎትን ብቃት፣ ተደራሽነት እና የዜጎች እርካታ በማሻሻል፣ በተቋማት መካከከል የተበታተነ አገልግሎትን በመቀነስ፣ ኅብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት የሚያጠፋውን ጊዜ እና ገንዘብ መቀነስ አስችሏል።

‎በመላው ሀገራችን የመሶብ ሥነዘዴ፤ መንግሥት ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የተቀናጀ የአገልግሎት አሰጣጥ ያለውን ጽኑ አቋም በሚያመላክት መንገድ እየተስፋፋ ይገኛል።

የተቀናጀ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የመንግሥት አገልግሎት አፈፃፀም ቁልፍ የክዋኔ ማመላከቻ እና አጠቃላይ የዜጎች ተጠቃሚነት ማጎልበቻ ሆነዋል።
👍4🔥1
ከመጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች

- ሌ/ጄኔራል አስራት ደኔሮ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
- ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
- አቶ ኤርዚቅ ኢሳ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

#PMOEthiopia
1
ከህግ ውጪ ከሥራቸው የተሰናበቱ 942 ሰራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመለሱ
+++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ከህግ ውጪ ከሥራቸው የተሰናበቱ 942 ሰራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡

“የዳኝነትና የዲሞክራሲ ተቋማት እመርታ፤ ለተሳካ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የዳኝነትና የዲሞክራሲ ተቋማት የሪፎርም ጉዞን የሚዳስስና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚመለከት ኮንፈረስ ተካሂዷል፡፡

የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ በኮንፈረንሱ ላይ እንደገለጹት፤ የህዝብ አስተዳደር እንዲሻሻልና የመንግስት ተጠያቂነት ለማሳደግ ይሰራል፡፡

አስተዳደራዊ በደል የደረሰባቸው ግለሰቦች የሚያቀርቧቸውን ቅተሬታዎችና አቤቱታዎች በመከታተል መምርምሮ እልባት እንዲያገኙ እየሰራ ይገኛል፡፡ በቀጣይም የአቤቱታ ምላሽ አሰጣጡን ከ78 በመቶ ወደ 85 በመቶ ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ሥራዎች ወደ ተቋሙ ከሚመጡ አቤቱታዎች መካከል 78 በመቶው እልባት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፤ ለአስተዳደራዊ በደል ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የቁጥጥር ሥራዎችን በመስራት 87 በመቶ መፍትሔ እንዲያኙ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

እንደዋና ዕንባ ጠባቂዋ ገለጻ፤ መሬታቸው ያለአግባብ የተወሰደባቸው 828 አቤቱታ አቅራቢዎች ጉዳያቸው ተመርምሮ ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸውና 14 ሚሊየን ብር ካሳ እንዲከፈላቸው ተደርጓል፡፡ ከህግ ውጪ ከሥራቸው ተሰናብተው የነበሩ 942 ሰራተኞች ደግሞ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ መደረጉን አብራርተዋል፡፡

አቤቱታ አቅራቢዎች ከህግ አግባብ ውጪ የተከለከሉትን ልዩ ልዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰው፤ ዜጎች መረጃ የማግኘት፤ የመጠየቅ፣ የማዘጋጀት መብታቸው እንዲከበርና የመረጃ ነጻነት ህጉ እንዲተገበር ክትትል እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡፡

የተጠናከረ የቁጥጥርና የምርመራ ሥርዓትን መዘርጋት፤ የአስተዳደራዊ በደል እንዲቀንስ መስራት የተቋሙ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የህዝብ አስተዳደር በግልጽነትና በተጠያቂነት መርህ እንዲመራ ለማድረግና ህገ መንግሥታዊነትን ለማስፈን እንደሚሰራ በመግለጽ፤ ተቋማት የሚሰጧቸው ፍትሃዊነት የጎደለው ውሳኔዎችና ትዕዛዞች በወቅቱ ለማረምና ለመከላከል እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus #ዕንባ_ጠባቂ #መረጃ ነጻነት #አስተዳደራዊ_በደል_ማረም
10