Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.8K photos
333 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“ህጋዊ የንግድ ስርዓትን የሚያቀጭጩ እና እንቅፋት የሚፈጥሩ ነገሮች በሙሉ ሊስተካከሉ ይገባል”

- አቶ ሙስጠፌ መሐመድ
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
+++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ህጋዊ የንግድ ስርዓትን የሚያቀጭጩ እና እንቅፋት የሚፈጥሩ ነገሮች በሙሉ ሊስተካከሉ ይገባል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጂግጂጋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን “ጉምሩክ ስለኢትዮጵያ” የውይይት መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ ህጋዊ ነጋዴዎችን ከገበያ በማውጣት እና የሀገር ኢኮኖሚን በማቀጨጭ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

ኮንትሮባንድ የንግድ ስርዓቱን ከማዛባት ባሻገር የማህበረሰብ ጤና፣ ሰላም እና ደህንነት ላይ እክል የሚፈጥር የሀገር እክል ነው ብለዋል።

የኮንትሮባንድ መረብ ውስብስብ እና በርካታ ተዋናዮች ያሉበት በመሆኑ በፀጥታ አካላት ብቻ በሚደረግ ጥረት እልባት ሊያገኝ አይችልም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ይህንን የልማት ጠላት ለመከላከል እና ለማስወገድ ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ህጋዊ ነጋዴዎች የንግድ ህግን አክብረው እና ለታክስ ህግ ተገዥ ሆነው በመስራት ለክልሉም ሆነ ለሀገሪቱ ገቢ እያስገኙ እንደሚገኙ አቶ ሙስጠፌ ገልጸዋል።

አክለውም፣ ክልሉ የሚሰራቸው የልማት ስራዎች ከግብር ከፋዩ በሚገኝ ገቢ የሚሰራ ነው፤ በዚህም ህጋዊ ነጋዴዎቻችን ሊኮሩ ይገባል ብለዋል።

ህጋዊ ነጋዴዎችን የንግድ ስራዎቻቸውን ለማስፋፋት ምቹ የንግድ ስነ-ምህዳር በመፍጠር እና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የክልሉ መንግስ እንደሚያበረታታቸውም አመልክተዋል።

በዮሐንስ መልካሙ (ጂግጂጋ)
8
የእመርታ ቤተ መጻሕፍት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመደመር መጻሕፍት ሽያጭ እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተገኘ በጀት የተገነባ ፕሮጀክት ነው።

ቤተ መጻሕፍቱ ከ1ሺ ካሬ ሜትር በላይ የቦታ ስፋት ላይ ያረፈ እና ዘመናዊ መሠረተ ልማት እንዲኖረው ተደርጎ ተገንብቷል። ሶስት የወለል ብዛት የያዘው እመርታ ቤተ መጻሕፍት፤ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ተስማሚ የሆነውን የድሬን አየር እያገኙ እንዲገለገሉም የቴራስ ቦታ ተዘጋጅቶለታል።

‎ቤተ- መጻሕፍቱ የብሬል ማንበቢያ ቦታ፣ ለልዩ ፍላጎት ተጠቃሚዎች የተዘጋጀ የአይቲ ማዕከል፣ ከክፍል ውጭ የንባብ ቦታ፣ የግል እና የቡድን ማንበቢያ እና የጥናት ክፍሎች፣ እንዲሁም የኮንፈረንስ ክፍልን አካቷል።

በአጠቃላይ እመርታ ቤተ-መጻሕፍት በአንድ ጊዜ ለ1ሺህ ሰው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሆኖ የተገነባ ሲሆን በመጽሐፍ መደርመሪያው ላይ ብቻ 1ሚሊየን መጻሕፍትን የመያዝ አቅም አለው።

#PMOEthiopia
👍63
በሀረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሠራው የገጠር ኮሪደር ሥራ በአካባቢው በተገኙ ቁሳቁሶች፤ በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወነ የአነስተኛ መንደር ሞዴል ክንውን ነው። የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ እቅድና ተግባራዊ የአሰራር ውጤት ያሳየ ነው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍84