Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.9K photos
333 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከዐድዋ ተራሮች እስከ ጉባ፤ ዐድዋ በልኩ ሲዘከር!

የዐድዋ ድል የጦር ሜዳ ድል ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በራሷ እንደምትወስን ለዓለም የታወጀበት አዋጅ ነበር።

መስዋዕትነታቸውን የምንዘክረው በትላንትናው ግርማ በመኖር ብቻ ሳይሆን፣ የዛሬውን አሻራችንን በመገንባት ነው። በዐድዋ መንፈስ እየተመራን የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ መቅረጻችንን እንቀጥላለን።

ከዐባይ ወንዝ የተነሳው 'ሁለተኛው ዐድዋችን' ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ያለፈውን ዘመን የምንዘክረው የአሁኑን ጊዜ በአሸናፊነት በመምራት መሆኑን ሕያው ምስክር ነው።

መደመርን ባነጸው በዐድዋ መንፈስ ስንመራ ሀገራችን የማታሳካው አንዳች ነገር አይኖርም። በአንድ ዓላማ በመሰለፍ በመደመር ስንጓዝ የኢትዮጵያ አቅም ከቶ ሊገታ አይችልም። ታላቅ የነበርን፤ ይበልጥም ታላቅ እንሆናለን!

#PMOEthiopia
🥰21
53ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 53ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው መደመር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአዋጅ ቁጥር 1294/2015 መሠረት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ የሚቋቋም ሲሆን በዘርፉ ወጣቶችን ለማሰልጠንና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ የሆኑ ምሁራንን ለማፍራት የሚሰራ ነው፡፡ ደንቡ የዩኒቨርሲቲውን ተግባርና ሃላፊነት በመደንገግ ተቋሙ ለሀገር ዕድገት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ለባለሃብቶች ካሳ ለመክፈል ግዴታ የሚገባበትን ሁኔታ ለመወሰን በቀረበ ደንብ ላይ ነው፡፡ ባለሀብቶች የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ሊያፋጥኑ በሚችሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንዲያስችል ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

3. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው በሶስት የፋይናንስ ድጋፍ ሰምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪው ለብሄራዊ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ከኮሪያ ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ የስልሳ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ሺ /60,223,000/ የአሜሪካን ዶላር ብድር ሲሆን ከወለድ ነጻ፣ ብድሩን በማስተዳደር ረገድ ለሚወጡ ወጪዎች 0.1% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበት እና የ15 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ40 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡

ሁለተኛው ለታዳሽ፣ የተቀናጀ፣ ዘላቂ ኃይል እና ዲጂታላይዜሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ከፈረንሳይ የልማት ኤጄንሲ የሰማንያ ሚሊዮን /80,000,000/ ዩሮ ብድር ሲሆን አነስተኛ ወለድ 1.2% የሚከፈልበት፣ ብድሩን በማስተዳደር ረገድ ለሚወጡ ወጪዎች 0.5% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበት እና የ7 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ20 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡

ሶስተኛው ለከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ሥራ ፈጠራ የሚውል ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር የአንድ መቶ ሰማንያ አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ /184,100,000/ ኤስ ዲ አር ብድር ሲሆን ከወለድ ነጻ፣ ብድሩን በማስተዳደር ረገድ ለሚወጡ ወጪዎች እንዲሁም ጥቅም ላይ ላልዋለው ገንዘብ 1.25% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበትና የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ30 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ሶስቱም የብድር ስምምነቶች ከአገራችን የብድር አስተዳደር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርአት ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ በሀገራችን የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዐትን ተግባራዊ ለማድረግ አዋጅ ቁጥር 372/1996 ወጥቶ በስራ ላይ የቆየ ቢሆንም ለአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ ባለመውጣቱ በአፈጻጸም ሂደት ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን ለማረም፣ ለአዋጁ አፈጻጸም አስቻይ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመደንገግና አስፈላጊውን የቁጥጥር ሥርዐትና መዋቅራዊ አደረጃጀት ለመፍጠር እንዲያስችል ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

5. በተጨማሪም የወርቅ ማዕድን እና የብረት ማዕድን ምርት ፈቃድ ረቂቅ ስምምነቶች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቷል፡፡ ለምክር ቤቱ የቀረቡት ሁለት ረቂቅ ስምምነቶች የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ከማሳደግ፣ ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር፣ ለኢኮኖሚያችን አዎንታዊ ሚና ከመወጣት አንጻር ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸውና ከአካባቢ ጥበቃና ከማህበረሰብ ተጠቃሚነት አንጻርም የመንግስትን የፖሊሲ አቅጣጫ የተከተሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ የማዕድን ሚኒስቴር ስምምነቶቹን እንዲፈራረምና ወደ ስራ እንዲገቡ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ይሁንታ ሰጥቷል፡፡

6. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ የነበረው የቱሪዝም ልማት ፖሊሲ በዘርፉ የተከሰቱ ለውጦችን ከማስተናገድ፣ መልካም አጋጣሚዎችና የመልማት አቅሞችን ከመጠቀም እና ለአገራዊ ዕድገት ሚናውን ከመወጣት አንጻር ክፍተቶች የነበሩበት ነው፡፡ ዘርፉን በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ ጋር አጣጥሞ በመምራት እና በማልማት ለአገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማስቻል አስፈላጊ በመሆኑ ረቀቂ ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

#PMOEthiopia
3
"አርበኛን የሚያጀግን ባንዳን የሚፀየፍ ትውልድ ልንገነባ ይገባል"

- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
+++++++++++++++++

ጋዜጣ_ፕላስ | አርበኛን የሚያጀግንና ባንዳን የሚፀየፍ ትውልድ መገንባት እንደሚገባ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ይህንን የገለጹት 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት እየተከበረ በሚገኝበት ወቅት ነው።

በዓድዋ ዘመን ሀገርን በመካድ ለጠላት የተሰለፉ ባንዳዎች እንደነበሩ ሁሉ፣ ዛሬም የባንዳነት ርዝራዦች ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመሰለፍ ብሔራዊ ጥቅምን ለመሸጥ እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

"ገመናን ለመሸፈን ተብሎ እውነታው ካልተገለጠ ባንዳነት በአደባባይ ወጥቶ የአርበኛ ማኅበረሰብ ግንባታን አደጋ ላይ ይጥላል" ሲሉም አሳስበዋል።

መምህራንንና የሕክምና ባለሙያዎችን የሚያግቱ፣ ተማሪዎችን የሚገድሉና የልማት ፕሮጀክቶችን ለማፍረስ የተላኩ ኃይሎች ሀገርን ለማዳከም እየተረባረቡ መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጠቁመዋል።

"እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን" ያሉት ኢታማዦር ሹሙ፤ ታዝሎ የሚመጣውን የውጭ ጠላትና አዝሎ የሚመጣውን የሀገር ውስጥ ባንዳ በእኩል ደረጃ ተዋግቶ የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ዓድዋ #ሉዓላዊነት #ጀግንነት #ብርሃኑ_ጁላ #አርበኝነት #130ኛው_ዓድዋ
👍31
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ ከተናገሩት የተወሰደ
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ዛሬ፤ በመላው አፍሪካ እና ጥቁር ህዝብ ላይ ጨልሞ በነበረ ሰማይ ጸሀይ የፈነጠቀበት ቀን ነው! ኢትዮጵያ ድንበሯን ገፍቶ ሉዐላዊነቷንና የህዝቧን ነጻነት የደፈረውን የወራሪውን ጦር በአድዋ ተራሮች ድል የነሳችበትና ለሶስት ሺህ አመታት ያልተደፈረውን ስልጣኔዋን ያጸናችበት ቀኗ ነው፡፡ ተከብረን የምንኖርባትን ኢትዮጵያን ከድንቅ ስልጣኔ እና ታሪክ ጋር ከነታላቅ ክብሯ በደም መስዋእትነት ላስረከቡን አባቶቻችን ክብር ይገባቸዋል፡፡

ዛሬ የምንኖር ኢትዮጵያውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ሞተው ያቆሙልንን ሀገር በአንድነትና በፍቅር በመኖር ልናስቀጥል ይገባል፡፡

ከእነሱ ተምረን ድህነትን፣ መከፋፍልንና ኋላ ቀር አስተሳሰብን አሻፈረኝ በማለት ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ልናሻግር ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ከሆነችው በላይ ታላቅ የምትሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!
3
ዛሬ ምሽት እንደተለመደው በረመዳን መንፈስ ከቡሩንዲ፣ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከሶማሊያ፣ ከኢራቅ፣ ከሶሪያ፣ ከፍልስጤም፣ ከአፍጋኒስታን፣ ከኤርትራ፣ ከየመንና ሱዳን ከመጡ ስደተኞች ጋር አፍጥር ታድመናል።

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በትግርኛ ያደረጉት ቆይታ- ነገ ምሽት 2:30 ይጠብቁን!

ቀዳማይ ሚኒስትር ዐቢይ ኣሕመድ(ዶ/ር) ምስ ኢዜኣ ብቋንቋ ትግርኛ ዝገበርዎ ፃንሒት- ፅባሕ ምሸት ሰዓት 2፡30 ይፀበዩና!

#PMOEthiopia
5🔥5
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
5👍1