Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.9K photos
334 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው የአዘርባጃን የሕዝብ አገልግሎት እና ማኅበራዊ ፈጠራ የመንግሥት ኤጀንሲ (ASAN) የፈጠራ ማዕከልን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ አዘርባጃን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚመራ አስተዳደርን ለማስፋፋት እና የሕዝብ አገልግሎቶችን በዲጂታል ለማዘመን የምትከተለውን ስትራቴጂያዊ አካሄድ የሚያሳይ ነው።

በሀገሪቱ የ AI ኢንጂነሪንግ እና የአመራር ሥልጠና ዋና ማዕከል የሆነውን የ AI አካዳሚን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

‎ልዑኩ ጉብኝቱን በመቀጠል በክልሉ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የነዳጅ እና የጋዝ ማቀነባበሪያ ማዕከላት አንዱ ወደሆነው ሳንጋቻል ተርሚናል እና ወደ አላት ነፃ የኢኮኖሚ ቀጣና አምርቷል። እነዚህ ጉብኝቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢነርጂ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትብብር ይበልጥ የማጠናከር አቅም አላቸው።

#PMOEthiopia
7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዘርባጃን ሪፐብሊክ የነበራቸውን ጉብኝት በማጠናቀቅ ዛሬ ከሰአት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

Following a successful Official Visit to the Republic of Azerbaijan, Prime Minister Abiy Ahmed has returned to Ethiopia this afternoon.

#PMOEthiopia
14
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ130ኛው የዐድዋ ድል በዓል ያስተላለፉት መልዕክት
++++++++++++
የዐድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን የማይቀየር ዐቋምና ዐቅም ያሳየ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅም፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት ላይ የማይቀየር ዐቋም አላቸው። ይሄንን ዐቋማቸውን በጽኑ መሠረት ላይ ለመትከል ደግሞ ሁሉንም አቅማቸውን ይጠቀማሉ።

ሥርዓታትና መሪዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፤ በአንዳንድ ጉዳዮች ልዩነቶች ይኖሯቸው ይሆናል፤ ስለ ሀገራቸው ያላቸው ዐቋምና ለሀገራቸው የሚያወጡት አቆም ግን አይቀየርም።

ወደ ዐድዋ የዘመቱ ጀግኖቻችን ሁሉ በሁሉም ነገር የተስማሙ አይደሉም። አንድ ዓላማ ነበራቸው እንጂ አንድ ዓይነት አልነበሩም። አንድ ሀገር ነበራቸው እንጂ አንድ ባህልና እምነት አልነበራቸውም።

በዚያ ጊዜ ሀገራቸውን ከድተው ከጠላት ጋር ያበሩ ባንዳዎች ነበሩ። ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ ዘላቂ የሀገራቸውን ጥቅም የሸጡ ምንደኞችም ነበሩ። ከባዳ ጋር ወግነው ወገናቸውን ያስማሙ ደላሎችም ነበሩ።

ጀግኖች እናቶቻችን እና አባቶቻችን የተዋጉት ከወራሪው የጣሊያን ጦር ጋር ብቻ አልነበረም። ከምንደኞች፣ ከባንዳዎች እና ከሀገር ደላሎች ጭምር እንጂ። ዐርበኝነት ማለት ባዳና ባንዳን ማሸነፍ ማለት ነው። ዐርበኝነት ማለት ለሀገር ጥቅም ሲባል የግል ጥቅምን ማሸነፍ ማለት ነው። ዐርበኝነት ማለት ለሀገር ክብር ሲባል የራስን ክብር መሠዋት ነው።

የዐድዋ ድል በዓል እነዚህን ሁሉ የምናስታውስበት ነው። የዐድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያንን ዐቅምና አቋም እንደገለጠው ሁሉ ዛሬም በጸና አቋም፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዐቅም የምንገልጥበት ጊዜ ነው። በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን እና በዲጂታል ሀገራችን ያላትን ዐቅም መግለጥ አለብን። የዐድዋን ድል በሁሉም ዘርፍ ለመድገም፣ የኢትዮጵያ ዐቅም ጽኑ መሠረት ሊኖረው ይገባል።

ሀገርን ዐቅም ያሳድጋታል፤ ዐቅም ይገነባታል። ሀገርን ዐቅም ይሠራታል። ዐቋም ያጸናታል። ሀገርን ዐቅም ያራምዳታል፤ ዐቋም ያሻግራታል።

የዐድዋ ድል በዓላችን የኢትዮጵያን ዐቅም ይበልጥ የምንገነባበትና የኢትዮጵያውያንን ዐቋም ይበልጥ የምናጸናበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
6
“የዓድዋ ድል ለጥቁር ህዝቦች የጥንካሬ ምንጭ ሆኗል”

- አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው
+++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ዓድዋ ለአፍሪካውያንና ለመላው የጥቁር ህዝብ የጥንካሬ ምንጭ ተደርጎ የሚወሰድ ድል ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ገለጹ፡፡

ቃል አቀባዩ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ከጋዜጣ ፕላስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣሊያ የተቃጣባትን የቅኝ ግዛት ወረራ በዓድዋ በመቀልበስ እና ድል በማድረግ ነጻነቷን አረጋግጣለች፡፡

የዓድዋ ድል በጥቁር ህዝቦች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታሪክ ነው ያሉት አምባሳደር ነቢያት፤ ድሉ ለአፍሪካውያን የጥንካሬ ምንጭ ተደርጎ የሚወሰድ ድል ብለዋል።

የዓድዋ ድል በጥቁር ህዝቦች ዘንድ ወራሪ ኃይልን መስበር ይቻላል የሚል እምነት የፈጠረ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

ዓድዋ በጸረ ቅኝ ግዛት ትግሉን በሚመሩ ልሂቃን መካከል የሚታወቅ ታሪክ እንደሆነ በመግለጽ፤ ድሉ ትልቅ የመንፈስ ስንቅና ጥንካሬ ሆኖ ለሌሎች ጸረ ቅኝ ግዛት ትግሎች እርሾ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የነጻነት ተጋድሎና ውጤቱ በኢትዮጵያ ተጀምሮ በኢትዮጵያ የሚያልቅ እንዳልሆነ የገለጹት አምባሳደር ነቢያት፤ ድሉ ለመላው አፍሪካውያንና ጥቁር ህዝቦች የነጻነት አርማና ማህተም ሆኖ ይኖራል ብለዋል።

ዓድዋ በየጊዜው ሲዘከር ብዙ ታሪክ የሚመዘዝለት እንደሆነና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚታወቅ ታሪካዊ ክስተት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በማርቆስ በላይ
+++++++++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት
@ጋዜጣ-ፕላስ
#ዓድዋ #ጥቁር_ሕዝቦች #አፍሪካ #ኢትዮጵያ #AdwaVictory #PanAfricanism
3
ዓመታዊ ባህል

የቅዱሱን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው የማኅበረሰባችን ክፍሎች የኢፍጣር መርሃ-ግብር አካሂደናል። የዛሬው ኢፍጣር በመተዛዘን፣ በፍቅር፣ በአንድነት እና ማኅበራዊ ዋጋን ከፍ በማድረግ ተከናውኗል።

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍82
ከዐድዋ ተራሮች እስከ ጉባ፤ ዐድዋ በልኩ ሲዘከር!

የዐድዋ ድል የጦር ሜዳ ድል ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በራሷ እንደምትወስን ለዓለም የታወጀበት አዋጅ ነበር።

መስዋዕትነታቸውን የምንዘክረው በትላንትናው ግርማ በመኖር ብቻ ሳይሆን፣ የዛሬውን አሻራችንን በመገንባት ነው። በዐድዋ መንፈስ እየተመራን የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ መቅረጻችንን እንቀጥላለን።

ከዐባይ ወንዝ የተነሳው 'ሁለተኛው ዐድዋችን' ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ያለፈውን ዘመን የምንዘክረው የአሁኑን ጊዜ በአሸናፊነት በመምራት መሆኑን ሕያው ምስክር ነው።

መደመርን ባነጸው በዐድዋ መንፈስ ስንመራ ሀገራችን የማታሳካው አንዳች ነገር አይኖርም። በአንድ ዓላማ በመሰለፍ በመደመር ስንጓዝ የኢትዮጵያ አቅም ከቶ ሊገታ አይችልም። ታላቅ የነበርን፤ ይበልጥም ታላቅ እንሆናለን!

#PMOEthiopia
🥰21