Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.9K photos
334 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለልዑካቸው በአዘርባጃን ባኩ የተደረገ አቀባበል
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዘርባጃን ባኩ በዛጉልባ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት የተደረገ አቀባበል
#PMOEthiopia
3
በአዘርባጃን ባደረግኩት የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ላደረጉልኝ ሞቅ ያለ እና የተከበረ አቀባበል ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

‎ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአቪዬሽን ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በነፃ የንግድ ቀጣናዎች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአዘርባጃን አቻው መካከል በተደረጉ የኢኮኖሚ ትብብሮች ላይ በመመስረት አጋርነታችን በየጊዜው እያደገ መጥቷል። እነዚህ የትብብር ዘርፎች ለሁለትዮሽ ግንኙነታችን መጠናከር መሠረት የጣሉ ሲሆን፣ ዛሬ ባደረግነው ጥልቅ ውይይትም ግንኙነታችንንና ትብብራችንን ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተናል።

‎በዛሬው ዕለትም በመከላከያና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተናል።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
5
በአዘርባጃን ባኩ ዛጉልባ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከተካሄደው ውይይት በመቀጠል፣ ሁለቱ መሪዎች በመከላከያና በበርካታ መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነዶች የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

‎ከተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶች መካከል 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ (COP32) ማዘጋጀት፣ በግብርና፣ በሚዲያ ልማትና ልምድ ልውውጥ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና በጸረ-ሙስና ትብብር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው።

‎በሌላ በኩል የአዘርባጃንን የአገልግሎት ዘርፍ ዝመናን በግንባር ቀደምትነት እየመራ የሚገኘው ተቋም "አሳን" (ASAN) እና በኢትዮጵያ የመሶብ አገልግሎት መካከል በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

‎እነዚህ ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ እና እንደሚያሰፋፉ ይጠበቃል። #PMOEthiopia
1