Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.2K subscribers
40.9K photos
334 videos
7 files
5.8K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የትግራይ ወጣት የተደቀነውን አጥፊ ጦርነት በማክሸፍ ሰላም እንዲያሰፍን ጥሪ ቀረበ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የታጠቀውም ሆነ ያልታጠቀው የትግራይ ወጣት የተጋረጠውን አጥፊ ጦርነት በመቃወም እጁን ለሰላም እንዲዘረጋ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ጥሪ አቀረቡ።

ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በክልሉ የተጋረጠውን የጦርነት ሥጋት ማስቀረት የሚቻለው ጦርነትና እልቂትን "እምቢ" በማለትና በአንድነት በመሰለፍ ብቻ ነው።

ወጣቱ ዓላማ ቢስ ወደሆነ ጦርነት ከመግባት ይልቅ የመኖር መብቱን ሊያስጠብቅ እንደሚገባ ያሳሰቡት ወይዘሮ ኬርያ፤ የታጠቀው ወጣትም "ለማን ዓላማና ምኞት ነው ሕይወቴን የምገብረው?" ብሎ ራሱን ሊጠይቅ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የተሳሳተ የትግራይ ወጣት ማለት ከታሪካዊው የሕዝብ ጠላት ሕወሓት ጋር ተሰልፎ ጥቁር ታሪክ ለማስመዝገብ የሚዘጋጅ መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ኬርያ፤ ወጣቱ በስሜት ሳይሆን በብስለትና በስሌት በመራመድ ሕዝቡንና ሀገሩን ከጥፋት ሊታደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አሁን ላይ የዳግም ጦርነት ሥጋት መግዘፉን ጠቁመው፤ ይህንን ጥፋት በምኞት ሳይሆን ጦርነትን በመጸየፍና በሰላማዊ መንገድ በመታገል ብቻ ማስቀረት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

በሔርሞን ፍቃዱ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰላም #ወጣቶች #ኬርያ_ኢብራሂም #ኢትዮጵያ #ጦርነትን_አይሆንም
6👎1
በአሜሪካ የምሥራቃዊ ግዛቶች በጣለው ከባድ በረዶ ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰረዙ
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በአሜሪካ የምሥራቃዊ ግዛቶች በጣለው ታሪካዊና ከፍተኛ የበረዶ ዝናብ ምክንያት ከ5 ሺህ 700 በላይ በረራዎች መቋረጣቸውንና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፍተኛ የትራንስፖርት መስተጓጎል መዳረጋቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት (NWS) አስታወቀ።

የብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እንዳስታወቀው፤ በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ የተከሰተው ከባድ ማዕበል፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የበረዶ ዝናብ በማምጣቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለችግር ዳርጓል፡፡

በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ሲሆን፣ ኒው ጀርሲ እና ማሳቹሴትስ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል።

በአንዳንድ የሮድ አይላንድ እና የማሳቹሴትስ ክፍሎች ወደ 37 ኢንች (94 ሳ.ሜ) የሚጠጋ የበረዶ ዝናብ፤ በኒውዮርክ ሲቲ ሴንትራል ፓርክ ደግሞ ከ19 ኢንች በላይ በረዶ ወርዶ የታዬ ሲሆን የኒውዮርክ ግዛት የአደጋ ጊዜ ቢሮም የጣለው በረዶ "ለጉዞ የማይቻል" ሁኔታ ፈጥሯል ብሏል፡፡

የማሳቹሴትስ አስተዳዳሪ ማውራ ሄሊ (ገዥ) በሰጡት መግለጫ፣ መንገዶች እጅግ አደገኛ በመሆናቸውና የነፍስ አድን ሠራተኞች ለመድረስ ስለሚቸገሩ ዜጎች ከቤታቸው እንዳይወጡ በጥብቅ አሳስበዋል።

"ኋይት-አውት" (White-out) በተሰኘው እጅግ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት አሽከርካሪዎች መንገዱን ማየት የማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ከአውሮፕላን በረራ ክልከላ በተጨማሪ ከአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎቶች ውጭ ማንኛውም የየብስ ጉዞ እንዳይደረግም እገዳ ተጥሏል።

የክረምት ማዕበል ማስጠንቀቂያ ከሰሜን ካሮላይና እስከ ሰሜናዊ ሜይን ድረስ የተዘረጋ ሲሆን፣ አንዳንድ ማስጠንቀቂያዎች ደግሞ በምስራቃዊ ካናዳ ክፍሎችም ጭምር ተሰጥተዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

በታደሠ ብናልፈው

++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት @ጋዜጣ-ፕላስ #ጋዜጣ_ፕላስ #አሜሪካ #የበረዶ_ማዕበል #በረራ #ኒውዮርክ #ሮድ_አይላንድ
7👍1
ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። የኢትዮጵያ እና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ተመስርተን ትብብራችንን የምናሳድግባቸውን መንገዶች ተመልክተናል።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍41
21 የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርገው ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በአፋር ክልል በአፍዴራና ዳሎል አካባቢ ላሉ የጨውና ፖታሽ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም 21 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ የኃይል መስመር ግንባታ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ፕሮጀክቱ በጠቅላላው ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ፕሮጀክት ነው።

ከዚህ ውስጥ 16 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ 84 ሚሊዮን 627 ሺህ 401 ብር ደግሞ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸፈን መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል።

ፕሮጀክቱ 375 ኪሎ ሜትር የመካከለኛና 93 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታን እንዲሁም የ85 ትራንስፎርመሮችን ተከላ ያካተተ ነው።

እስካሁን ባለው አፈጻጸም 8 መንደሮችና አንድ ፋብሪካ ተጠቃሚ መሆናቸውንና አጠቃላይ የሥራው አፈጻጸም 84.46 በመቶ መድረሱን ተቋሙ አስታውቋል።

ይህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 14 ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፤ በአካባቢው ለሚገኙ ከ200 በላይ ወጣቶችም የሥራ ዕድል መፍጠሩ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም በቀጣይ 17 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የግብዓት ግዥ የተፈጸመ ሲሆን፤ ሥራው በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተመልክቷል።

በሄለን ወንድምነው
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኤሌክትሪክ_ኃይል #አፋር #አፍዴራ #ዳሎል #ኢንዱስትሪ #ኢትዮጵያ #ልማት
5
በቀጣይ ቀናት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ ሙቀት ይጠበቃል
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በቀጣይ ቀናት በጋምቤላ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ ሙቀት እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስከ 39.9 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊደርስ ይችላል።

በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን እንደሚጨምር የጠቆመው ኢንስቲትዩቱ፤ በተለይም በቀጣይ ሳምንት የመጨረሻ ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው የስምጥ ሸለቆና አዋሳኝ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ትንበያው አመልክቷል።

የሚኖረው እርጥበት የበልግ እርሻ እንቅስቃሴን ቀድመው ለሚጀምሩ አካባቢዎች ለማሳ ዝግጅትና ዘር ለመዝራት ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ከፍተኛ ሙቀት በሚጠበቅባቸው አካባቢዎች የሚገኘው ማኅበረሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

በዳግማዊት አበበ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ሜቲዎሮሎጂ #የአየር_ንብረት #ሙቀት #ዝናብ #በልግ #ኢትዮጵያ
8
የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል፤ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ ይታያል። ይኅው ላቅ ያለው የሁለቱ ሀገራት ቅርርብን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ ሄዳር አሊዬቭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል። በዚህኛው ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል።

#PMOEthiopia
6👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለልዑካቸው በአዘርባጃን ባኩ የተደረገ አቀባበል