የኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተከበረ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የመስራታ በዓል በምስል
❤11👍3
በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል፤ ያሉንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ስራ ዋነኛው ነው። ከዚህ ቀደም ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ ቦታዎች አሁን ላይ በመስኖ ወደ ግብርና ልማት ማዕከልነት እየተቀየሩ ነው።
የብላቴ ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ ደግሞ ለዚህ ተጠቃሽ አብነት ነው። በአካባቢው የግል ባለሃብቶችን በማሳተፍ ሰፋፊ የፍራፍሬ ልማቶች እየተከናወኑ ይገኛል። ይህም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ ነው።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

❤6👍2
ኢንስቲትዩቱ በከተሞች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በዘንድሮው የበልግ ወቅት በሚኖረው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በከተሞች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።
በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በበልግ ወቅት ከሚኖረው ከፍተኛና ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ የተነሳ በተለይም በቆላማ ስፍራዎችና በከተሞች ቅጽበታዊ ጎርፍ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው።
አዲስ አበባን ጨምሮ በደቡብና ምሥራቅ ትግራይ፣ በምሥራቅ አማራ፣ በአፋርና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እንደሚጠበቅ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ በጉጂ፣ በቦረና፣ በሲዳማና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስከ 55 በመቶ የሚደርሰው ዓመታዊ የዝናብ መጠን የሚስተዋለው በዚህ ወቅት መሆኑን አሳምነው (ዶ/ር) አስረድተዋል።
የበልግ ዝናብ ተለዋዋጭነቱ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ችግሩን ለመከላከል የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ማከናወንና ኢንስቲትዩቱ የሚያወጣቸውን የትንበያ መረጃዎች በመጠቀም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአማን ረሺድ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ሚቲዎሮሎጂ #ጎርፍ #ከተሞች #ዝናብ #የበልግ #አካባቢ_ጥበቃ

❤1
የትግራይ ወጣት የተደቀነውን አጥፊ ጦርነት በማክሸፍ ሰላም እንዲያሰፍን ጥሪ ቀረበ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የታጠቀውም ሆነ ያልታጠቀው የትግራይ ወጣት የተጋረጠውን አጥፊ ጦርነት በመቃወም እጁን ለሰላም እንዲዘረጋ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ጥሪ አቀረቡ።
ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በክልሉ የተጋረጠውን የጦርነት ሥጋት ማስቀረት የሚቻለው ጦርነትና እልቂትን "እምቢ" በማለትና በአንድነት በመሰለፍ ብቻ ነው።
ወጣቱ ዓላማ ቢስ ወደሆነ ጦርነት ከመግባት ይልቅ የመኖር መብቱን ሊያስጠብቅ እንደሚገባ ያሳሰቡት ወይዘሮ ኬርያ፤ የታጠቀው ወጣትም "ለማን ዓላማና ምኞት ነው ሕይወቴን የምገብረው?" ብሎ ራሱን ሊጠይቅ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የተሳሳተ የትግራይ ወጣት ማለት ከታሪካዊው የሕዝብ ጠላት ሕወሓት ጋር ተሰልፎ ጥቁር ታሪክ ለማስመዝገብ የሚዘጋጅ መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ኬርያ፤ ወጣቱ በስሜት ሳይሆን በብስለትና በስሌት በመራመድ ሕዝቡንና ሀገሩን ከጥፋት ሊታደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አሁን ላይ የዳግም ጦርነት ሥጋት መግዘፉን ጠቁመው፤ ይህንን ጥፋት በምኞት ሳይሆን ጦርነትን በመጸየፍና በሰላማዊ መንገድ በመታገል ብቻ ማስቀረት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
በሔርሞን ፍቃዱ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰላም #ወጣቶች #ኬርያ_ኢብራሂም #ኢትዮጵያ #ጦርነትን_አይሆንም

❤7👎1
በአሜሪካ የምሥራቃዊ ግዛቶች በጣለው ከባድ በረዶ ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰረዙ
++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በአሜሪካ የምሥራቃዊ ግዛቶች በጣለው ታሪካዊና ከፍተኛ የበረዶ ዝናብ ምክንያት ከ5 ሺህ 700 በላይ በረራዎች መቋረጣቸውንና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፍተኛ የትራንስፖርት መስተጓጎል መዳረጋቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት (NWS) አስታወቀ።
የብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እንዳስታወቀው፤ በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ የተከሰተው ከባድ ማዕበል፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የበረዶ ዝናብ በማምጣቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለችግር ዳርጓል፡፡
በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ሲሆን፣ ኒው ጀርሲ እና ማሳቹሴትስ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል።
በአንዳንድ የሮድ አይላንድ እና የማሳቹሴትስ ክፍሎች ወደ 37 ኢንች (94 ሳ.ሜ) የሚጠጋ የበረዶ ዝናብ፤ በኒውዮርክ ሲቲ ሴንትራል ፓርክ ደግሞ ከ19 ኢንች በላይ በረዶ ወርዶ የታዬ ሲሆን የኒውዮርክ ግዛት የአደጋ ጊዜ ቢሮም የጣለው በረዶ "ለጉዞ የማይቻል" ሁኔታ ፈጥሯል ብሏል፡፡
የማሳቹሴትስ አስተዳዳሪ ማውራ ሄሊ (ገዥ) በሰጡት መግለጫ፣ መንገዶች እጅግ አደገኛ በመሆናቸውና የነፍስ አድን ሠራተኞች ለመድረስ ስለሚቸገሩ ዜጎች ከቤታቸው እንዳይወጡ በጥብቅ አሳስበዋል።
"ኋይት-አውት" (White-out) በተሰኘው እጅግ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት አሽከርካሪዎች መንገዱን ማየት የማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ከአውሮፕላን በረራ ክልከላ በተጨማሪ ከአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎቶች ውጭ ማንኛውም የየብስ ጉዞ እንዳይደረግም እገዳ ተጥሏል።
የክረምት ማዕበል ማስጠንቀቂያ ከሰሜን ካሮላይና እስከ ሰሜናዊ ሜይን ድረስ የተዘረጋ ሲሆን፣ አንዳንድ ማስጠንቀቂያዎች ደግሞ በምስራቃዊ ካናዳ ክፍሎችም ጭምር ተሰጥተዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
በታደሠ ብናልፈው
++++++++++
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት @ጋዜጣ-ፕላስ #ጋዜጣ_ፕላስ #አሜሪካ #የበረዶ_ማዕበል #በረራ #ኒውዮርክ #ሮድ_አይላንድ

❤7👍1
ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። የኢትዮጵያ እና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ተመስርተን ትብብራችንን የምናሳድግባቸውን መንገዶች ተመልክተናል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍4❤1