በሐረር ጥንታዊ ጀጎል ውስጥ የሚገኘው የቱርክዬ የቀድሞ ቆንስላ ጽ/ት ቤት ፤ የአሁኑ ሙዚየምና የባህል ማዕከል አሁናዊ ገፅታው በፎቶ
❤7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ረጀብ ጣይፕ ኤርዶጋን በ9ኛው የቱርክ-ኢትዮጵያ የጋራ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ስምምነት ሰነድ እንዲሁም በኢነርጂ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
እነዚህ ስምምነቶች በኢትዮጵያና በቱርክዬ መካከል እየተጠናከረ የመጣውን አጋርነት ይበልጥ የሚያጎለብቱ ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረቱ መስኮች፤ ያላቸውን የሥራ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አመላካች ነው።
#EthiopiaHosts #EthiopiaDelivers #PMOEthiopia

❤3
"ዛሬ በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የለማ የሙዝ እርሻ ከባቢን ጎብኝቻለሁ። አርሶአደሮች በፍጹም ጽናት፣ ቅንጅት እና ትብብር አካባቢያቸውን በቀየረ ስራ በመመልከቴ ደስ ብሎኛል።
የተመለከትነው የእርሻ ስራ፤ የአካባቢ መሬትን እና የውኃ ኃብትን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው። ባህላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በመጠቀም እና በቅርብ ያለ ኃብትን በሚገባ ጥቅም ላይ በማዋል ማኅበረሰቡ ውጤታማ እና ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከል መፍጠር ችሏል።
በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት የአርሶአደሮችን ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ የፈጠረውን እድል መመልከት እጅግ የሚያበረታታ ነው። ይኽ እድገት የልማት ጥረቶች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ፍላጎት እና አቅም ጋር በቅርበት ሲናበቡ ሊገኝ የሚችለውን ውጤት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

❤1🥰1
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ በድሬዳዋ ልትከፍት ነው
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ በድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ ልትከፍት መሆኑን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ላብራቶሪው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶችና ዘይቶች የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ማሟላታቸውን ለመፈተሽ የሚያስችል ነው።
አገልግሎቱ በቅርበት መሰጠቱ አምራች ድርጅቶችና ተቋማት በተቀላጠፈ መንገድ ጥራት ማረጋገጥ እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለዚህም ዘመናዊ መሣሪያዎችና የሰለጠኑ ባለሙያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ተቋሙ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳና በባሕር ዳር ተጨማሪ የፍተሻ ላብራቶሪዎችን በማደራጀት ላይ እንደሚገኝም ነው ያስገነዘቡት።
በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ነዳጅ #ጥራት_ምዘና #ድሬዳዋ #ኢትዮጵያ #ኢኮኖሚ #ላብራቶሪ

የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነው።
በምዕራብ ወለጋ ገንጂ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና የግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተሠራ የሚገኝ ነው። ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ፕሮጀክቱ ለትምህርት፣ የመንገድ ልማት፣ የጤና ተቋማትና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታን የማነቃቃት አቅም አለው።
በጉብኝታችን ወቅት እንደተመለከትኩት የፕሮጀክቱ ፋይዳ በአንድ የተወሰነ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ማኅበረሰብ የበለጠ ለልማት በማነሳሳት ከፍ ያለ ሚናውን እንደሚያስቀጥል እምነቴ የፀና ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)