Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.7K subscribers
41.4K photos
347 videos
7 files
5.83K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአፍሪካና የዓለም አቀፍ መሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጣችሁ በማለት፣ የአፍሪካን ታሪካዊ ዐሻራና ጽኑ ርዕይ አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

‎የአኅጉሩ ትልቁ ሀብት የተፈጥሮ ጸጋ ብቻ ሳይሆን፣ ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት፣ ፈጠራን የማሳደግና ለዘላቂ ልማት ያለው አስተዳደራዊ ችሎታ መሆኑን አሳስበዋል። በውኃ ልማት፣ በኢነርጂ፣ በምግብ ዋስትና እና በኢንዱስትሪ ልማት ረገድ እየታዩ ያሉ መሻሻሎችን በማንሳት፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ በስንዴ ምርት ራስን የመቻል ጥረትንና እየተስፋፉ ያሉ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶችን ለአፍሪካዊ መፍትሔዎችና ለጋራ ብልጽግና ማሳያ ምሳሌዎች አድርገው ጠቅሰዋል።

‎አኅጉሩ የደረሰበት ጠንካራ የዕድገት ጉዞ፣ የኢትዮጵያን የ10 ነጥብ 2 በመቶ ተጠባቂ ዕድገት፣ እንዲሁም የአኅጉሩን የስነ-ሕዝብ ብልጫ ለመጠቀም በወጣቶች፣ በጤና እና በትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያለውን አስፈላጊነት ገልጸዋል።

‎በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አማካኝነት የሚታየውን የአየር ንብረት መሪነት፣ በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ሥር እየተከናወነ ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታዩ ስኬቶችን እና የአኅጉራዊ ትስስር መስፋፋትን አጉልተዋል።

በመጨረሻም ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎችን የመቅረጽ አቅም ያለው እና ለሁሉም አፍሪካውያን የሚተርፍ፤ ልማትን፣ ዕድልንና ክብርን የሚያረጋግጥ በራሱ የሚተማመንና የተባበረ የአፍሪካ ሕብረት እንዲኖር ጥሪ በማቅረብ ንግግራቸውን አጠቃለዋል። #AUSummit #PMOEthiopia
“አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው”
- አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
++++++++++
ጋዜጣ_ፕላስ | አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና የታሪክ ስህተት መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ጸሐፊው፤ የአፍሪካ ጥንካሬ የሚመነጨው በራሱ በሚተማመን እና በተባበረ ሕብረት መሆኑን ተናግረዋል።

አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ የዓለም አቀፉን ተቋም ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል መሆኑን ጠቅሰው፤ ስለ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ውሳኔ በሚተላለፍበት ጠረጴዛ ዙሪያ አፍሪካ የግድ መገኘት እንዳለባት አጽንኦት ሰጥተዋል።

አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚገባትን ድምፅ እንድታገኝ የሚደረገውን ጥረት ድርጅታቸው እንደሚደግፍም አመልክተዋል።

በሄለን ወንድምነው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ተመድ #አፍሪካ_ሕብረት #የጸጥታው_ምክር_ቤት #አፍሪካ #አዲስ_አበባ #አጀንዳ2063
❤2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለሶስተኛ ጊዜ የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት እያልኩ የተሰማኝን ደስታ እገልጣለሁ።
‎
‎የባርቤዶስ ሕዝብ ላደረገው ስኬታማ የዴሞክራሲ ልምምድ እያደነኩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ ለባርባዶስ ሕዝብ እድገት፣ ብልጽግና እና ዘላቂ ልማት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም እድል እንዲገጥምዎ እመኛለሁ። ‎በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር እና ትብብራችንን ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን።
❤3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝደንት ታቦ ምቤኪ ጋር በአፍሪካ ልማት፣ በቀጠናዊ ትስስር እና አኅጉራዊ የቅድሚያ ጉዳዮች ላይ ያደረጉት ውይይት

#PMAbiyAhmed #ThaboMbeki #AfricaDevelopment #AUsummit #BilateralRelations #Ethiopia #GazettePlus #EPA
❤1
በሁለተኛው ቀን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን፤ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤6
"ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ቤት በመሆኑ ወደ ባህሩ መመለሳችን አይቀሬ ነው"

- ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ቤት በመሆኑ ወደ ባህሩ መመለሳችን አይቀሬ መሆኑን የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ብሩክ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት መረጃ እንዳመለከቱት፤ ቀይ ባህር የቀድሞው የኢትዮጵያ አካልና ቤቷ በመሆኑ ወደ ባህሩ መመለሳችን የታሪክ ግዴታ ነው።

ቀደም ሲል በተፈጸሙ ስህተቶች የሀገሪቱ ሕዝብና ኢኮኖሚ እየተጎዳ መቀጠል ስለሌለበት የቀይ ባህር ተደራሽነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ግብፅ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ሴራ እየሸረበች መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ግን ይህንን ሰንሰለት በመበጣጠስ ፍላጎቷን ማሳካቷ እንደማይቀር አብራርተዋል።

ኤርትራ ለኢትዮጵያ ጠላቶች መረማመጃ ከመሆን ወጥታ ከሰሜን እስከ ደቡብ ያሉ ተቃዋሚ ኃይሎችን መደገፍ ማቆም እንዳለባት ፕሮፌሰር ብሩክ አሳስበዋል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ቀይ_ባህር #የባህር_በር #ዲፕሎማሲ #ብሔራዊ_ጥቅም
❤8👎1
በሐረር ጥንታዊ ጀጎል ውስጥ የሚገኘው የቱርክዬ የቀድሞ ቆንስላ ጽ/ት ቤት ፤ የአሁኑ ሙዚየምና የባህል ማዕከል አሁናዊ ገፅታው በፎቶ
❤7