Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.7K subscribers
41.4K photos
347 videos
7 files
5.83K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ዛሬ የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብዬ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል።

‎ውይይታችን በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትስስር በማስፋትና የወል ፍላጎቶቻችን በሆኑ ቀጣናዊና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
❤3
የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ መግለጫ
❤4👍4
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች የአፍሪካ ሀገራት
ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ ዝግጅት ተደርጓል
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የመራጮች ምዝገባ ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም መራዘሙን ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 7 እንደሚጀመር ተገልጾ የነበረው ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓም ተራዝሟል፡፡

ቦርዱ 2018 ዓም ለሚያከናውነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጮች ምዝገባና ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ማስገባቱን ገልጸው፤ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ነው ብለዋል።

የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ለመክፈት የሚያስችሉ የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች ምዝገባ ቦርዱ ማካሄዱን ጠቁመው፤ በዚህም የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት መክፈት መቻሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ቦርዱ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ቅጥር በማከናወን ለፖለቲካ ፓርቲዎች መላኩንም ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።

በአማን ረሺድ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ምርጫ ቦርድ
❤4👍2
በመደመር መንፈስ ኢትዮጵያ ከጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር በመተባበር ሁለተኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ የካቲት 6፣ 2018 በአዲስ አበባ በማስተናገድ በጣሊያንና በአፍሪካ መካከል ድልድይ ሆናለች፡፡

የሰው ዘር መገኛ እንደመሆናችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነቶችን ለማጠናከር በመላው አፍሪካ የንግድ፣ የፈጠራ እና የኢንቨስትመንት ሥራዎችን ለማሳደግ ለጋራ እድገት እንሰባሰባለን፡፡
‎
‎የጉባዔው ተሳታፊ ልዑካንና እንግዶቻችን፣ የመነሻ መሰረታችንና የነገ ዘላቂ አጋርነቶች ወደ ሚገነቡባት ሁለተኛ ቤታችሁ ወደሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣችሁ! #MeetInEthiopia #PMOEthiopia
❤2👍2
While you are here for the #AUSummit, think #InvestInEthiopia.

Through our Homegrown Economic Reform Agenda, we have built an investor-first ecosystem, anchored in a transparent #FDI framework, modern Special Economic Zones, and seamless access to #AfCFTA and African and global markets.

Driven by strategic, sustainability-focused leadership and powered by the GERD, Ethiopia offers 98%+ renewable energy, expanding digital infrastructure, enhanced telecommunications, and a skilled workforce ready to deliver sustainable returns across agritech, manufacturing, fintech, e-commerce, mining, beyond strengthening regional value chains and advancing Africa’s shared prosperity.

#EconomicReform #AfricanIntegration #PMOEthiopia
❤1
ኢትዮጵያ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ የምታጋራቸው ተሞክሮዎች
ኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እየፈጠረች ነው
+++++++++++++++++
ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁልፍ ከሆኑ ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እየፈጠረች መሆኑን የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ብሩክ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት መረጃ እንዳመለከቱት፤ የሀገር መሪዎች ጉዞ ብሔራዊ ጥቅምን መሠረት ያደረገ በመሆኑ በቅርብ ጊዜያት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሀገሪቱን ተቀባይነት የሚያሳይ ነው።

የተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን የቀጣናው ስትራቴጂካዊ አጋር አድርገው እየሠሩ መሆናቸው ሀገሪቱ በቀጣናው ያላትን ጉልህ ቦታ ያረጋግጣል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የዓለም ሀገራት ጋር እየፈጠረች ያለው ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች የጎላ ጠቀሜታ እንዳለውና አሁን ያለውን የዓለም የኃይል አሰላለፍ ያገናዘበ የውጭ ፖሊሲ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑንም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ከሁሉም ጋር የተጣጣመና ከጊዜው ጋር የሚሄድ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን አመልክተዋል።

በክብረአብ በላቸው

@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ዲፕሎማሲ #ብሔራዊ_ጥቅም #ስትራቴጂካዊ_አጋርነት #ዓለም_አቀፍ_ግንኙነት
❤3
ኢትዮጵያ ያሰናዳችው 2ተኛው የጣሊያን -አፍሪካ ጉባዔ ተሳታፊ መሪዎች ወደ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ሲገቡ
#ItalyAfricaSummit #Italy_Africa  #Ethiopia  #Italy #GazettePlus #EPA
👏1
ኢትዮጵያ ያሰናዳችው 2ተኛው የጣሊያን -አፍሪካ ጉባዔ ተሳታፊ መሪዎች ወደ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ሲገቡ
#ItalyAfricaSummit #Italy_Africa #Ethiopia #Italy #GazettePlus #EPA
👏1