የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት
ውድ ኢትዮጵያዊያን
በዚህ ሳምንት ውዷ ሀገራችን በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ለመታደም የሚመጡ እህት ወንድም አፍሪካዊያንን ለመቀበል ልቧን ከፍታ-እጆቿን ዘርግታ ትቀበላለች። እነዚህ ወዳጆቻችን የሰንደቃችንን ቀለማት የሚጋሩ፣ ኢትዮጵያን እንደነፃነት ቀንዲል የሚመለከቱ ብሎም ሀገራችን የአኅጉሩ የፖለቲካ ርዕይ የማዕዘን ድንጋይ አድርገው የሚያከብሩ ናቸው።
ኢትዮጵያ ወደር በሌለው እንግዳ ተቀባይነቱ ለምን ልትከበር እንደበቃች በአቀባበላችን እናሳያቸው። እንደቤታቸው እንዲሰማቸው እናድርግ። በክብር እንቀበላቸው። በፍቅር እናቆያቸው። ተደምረን ሰንደቃችን የሚወክለውን የአፍሪካ አንድነትን መንፈስ እና የሚያያይዘንን የወል ህልም እናድርግ!

❤10👍5
"ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት አስጀምረናል።
ይህ አገልግሎት ዜጎች የፖሊስ አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነትና በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያገኙ ያስችላል።
በተጨማሪም አገልግሎቱ ለፖሊስ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውና የወንጀል መከላከል ስራውን የሚያቀላጥፈው ነው።
የዚህ አገልግሎት መጀመር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የህግ አስከባሪ አካላት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተጀመረው የሪፎርም ስራን ውጤታማነት የሚያሳድግ ይሆናል"
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

👍9❤7👏2
ዛሬ የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብዬ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል።
ውይይታችን በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትስስር በማስፋትና የወል ፍላጎቶቻችን በሆኑ ቀጣናዊና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

❤3
የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ መግለጫ
❤4👍4
ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ ዝግጅት ተደርጓል
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የመራጮች ምዝገባ ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም መራዘሙን ገልጸዋል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 7 እንደሚጀመር ተገልጾ የነበረው ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓም ተራዝሟል፡፡
ቦርዱ 2018 ዓም ለሚያከናውነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጮች ምዝገባና ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ማስገባቱን ገልጸው፤ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመላክ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ነው ብለዋል።
የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ለመክፈት የሚያስችሉ የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች ምዝገባ ቦርዱ ማካሄዱን ጠቁመው፤ በዚህም የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት መክፈት መቻሉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ቦርዱ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ቅጥር በማከናወን ለፖለቲካ ፓርቲዎች መላኩንም ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።
በአማን ረሺድ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ምርጫ ቦርድ

❤4👍2