Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.7K subscribers
41.4K photos
347 videos
7 files
5.83K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሎጎ ሀይቅ ሪዞርት.....ገበታ ለትውልድ
❤7🥰4👍1
በአማራ ክልል 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይሳተፋሉ
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ _ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደሚሳተፉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሰታወቀ።

የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ለኢቢሲ እንደገለጹት ከለውጡ በኋላ በተዘረጋው አሳታፊ ምኅዳር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከመንግሥት ጋር በመቀናጀትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በመመደብ አዲስ የፖለቲካ አውድ መፍጠር መቻላቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የዲጂታል አገልግሎት አማካኝነት እየመዘገቡ መሆኑን አቶ ተስፋሁን ገልጸዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ ይሰራልም ብለዋል።

ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም አስገንዝበዋል።

#የኔ_ድምጽ #የምርጫ_ጊዜ #ሰላማዊ_ምርጫ #ዴሞክራሲ_ለኢትዮጵያ
❤3
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ መራዘምን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ‼️
❤3
የወሎ ህዝብ አክብሮትና ምስጋና
❤2
"ባሕር በር ለኢትዮጵያ እንደሳምባና የደም ስር የሚታይ ነው" - ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም

++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ባሕር በር ለኢትዮጵያ እንደ ሳምባና የደም ስር የሚታይ በመሆኑ ህልውናን ለማስጠበቅ የምንጠይቀውና የምናረጋግጠው ነው ሲሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ወለድ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ገለጹ።

ወደር የሌለው የኢትዮጵያ የጦር ሜዳ ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ ሁለንተናዊ እድገቷ ተገትቷል።

የባሕር በር ለኢትዮጵያ እንደ መተንፈሻ ሳምባና የደም ስር የሚታይ በመሆኑ የመኖርና ያለመኖርን ጉዳይ ነው፤ ጥያቄው የልመና ሳይሆን የመብትና የህልውና ጥያቄ ነው ብለዋል።

እንደብርጋዴልር ጀነራል ተስፋዬ ገለጻ፤ የባሕር በር አልባ መሆን ሀገሪቱን ለውጭ ጥቃት በቀላሉ ተጋላጭ ከማድረጉም በላይ ጠንካራ የባሕር ኃይል እንዳይኖራት፤ የኢኮኖሚ ጫና እንዲከሰትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ዋጋቸው እየናረ እንዲሄድ አድርጓል።

በወቅቱ የነበሩ መሪዎች በግድየለሽነት አሰብን አሳልፈው ለኤርትራ በመስጠታቸው ዛሬ ለደረስንበት መከራ መዳረጋችንን ጠቅሰው፤ ኤርትራ ስትገነጠል የባሕር በር ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ በውጭ ኃይሎች በኩል ግፊት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይህ ታሪካዊ ስህተት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የላብ፣ የደም፣ የአካልና የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉበትን ክብር ያሳጣ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የባህር በር ለማግኘት በመንግሥት በኩል የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ጥረቶች የሚደገፉ በመሆኑ፤ የእኛን መብት ሊያስከብርልን ማንም ከውጭ ስለማይመጣ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ ከመንግሥት ጎን ልንቆምና ልንሰለፍ ይገባል ብለዋል።

በዮሐንስ መልካሙ

#ጋዜጣ_ፕላስ #የባሕር በር #ኢትዮጵያ #የኢትዮጵያ አየር ወለድ #ዲፕሎማሲ
❤10🔥2