ኢትዮጵያ በጉባኤው ብሄራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በቂ ዝግጅት አድርጋለች - አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው
✍️ ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ 179 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች ስልጠና ወስደዋል
++++++++++++++++
#ጋዜጣ-ፕላስ_ ከየካቲት ሰባት እስከ ስምንት 2018 ዓ.ም በሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በቂ ዝግጅት ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የዘንድሮው የህብረቱ መሪ ቃል በውኃ ሀብት አጠቃቀምና በንፅህና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
ጉባኤውን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳሰታወቁት፣ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በቂ ዝግጅት አድርጋለች። የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከየካቲት አራት እስከ አምስት 2018 ዓ.ም 41ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባና ከየካቲት ሰባት እስከ ስምንት 2018 ዓ.ም ድረስ 39ኛው የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። ጉባኤውን በስኬት ለማጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ ጉባኤው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የይዘትና የሎጅስቲክ ዝግጅቷን አጠናቃለች። የአገርን ገፅታ ለመገንባትና ለማስተዋወቅ ጉባኤው ልዩ ጠቀሜታ እንዳለውም ቃለ አቀባዩ ገልጸዋል።
ለዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ 179 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን አምባሳደሩ ጠቅሰዋል። ለጉባኤው የሚያስፈልገውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
#የዲፕሎማሲከተማ #ጋዜጣ_ፕላስ #ምክክር #AfricaUnion #NationalDialogue

❤3
በአማራ ክልል 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይሳተፋሉ
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ _ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደሚሳተፉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሰታወቀ።
የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ለኢቢሲ እንደገለጹት ከለውጡ በኋላ በተዘረጋው አሳታፊ ምኅዳር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከመንግሥት ጋር በመቀናጀትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በመመደብ አዲስ የፖለቲካ አውድ መፍጠር መቻላቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የዲጂታል አገልግሎት አማካኝነት እየመዘገቡ መሆኑን አቶ ተስፋሁን ገልጸዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ ይሰራልም ብለዋል።
ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም አስገንዝበዋል።
#የኔ_ድምጽ #የምርጫ_ጊዜ #ሰላማዊ_ምርጫ #ዴሞክራሲ_ለኢትዮጵያ