የሆራይዘን ፋይበር ኢንሼቲቭን እውን ለማድረግ የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ
+++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ_ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ጅቡቲ ቴሌኮም እና ሱዳቴል ግሩፕ የሆራይዘን ድንበር ተሻጋሪ የፋይበር መስመር ዝርጋታን እውን ለማድረግ የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት በዛሬው ዕለት በጅቡቲ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ከፍተኛ አቅም ያለው ድንበር ተሻጋሪ የኦፕቲካል ፋይበር መሠረተ ልማት ለመዘርጋትና የቀጣናውን ዲጂታል ትስስር ወደ ላቀና አስተማማኝ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በኢትዮ ቴሌኮም፣ በጅቡቲ ቴሌኮምና በሱዳቴል ግሩፕ መካከል የተደረገው የሦስትዮሽ ስምምነት፤ የጋራ የሆነ የዲጂታል አቅም ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል።
የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቭ ጠንካራና ከፍተኛ አቅም ያለው፣ አፍሪካን በዲጂታል የሚያስተሳስር የኮኔክቲቪቲ ኮሪደር ለመፍጠር የተወሰደ ወሳኝ እርምጃ ነው ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የጅቡቲን የባሕር ውስጥ የፋይበር ኬብሎች በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ ከሱዳን ጋር በማስተሳሰር፤ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስርን የሚያጠናክር፣ አስተማማኝ የየብስ መስመር ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ዋል።
“ይህን ፕሮጀክት እጅግ ልዩ የሚያደርገው አፍሪካዊ አጋርነትን ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ የዲጂታል መሠረተ ልማት ሀብትን በማቀናጀት፤ የአፍሪካ ኦፕሬተሮች ተጨባጭ የኮኔክቲቪቲ ተግዳሮቶችን በመፍታት ለደንበኞች፣ ለኢንተርፕራይዞችና ለግዙፍ የዳታ ኩባንያዎች አዲስ እሴት ለመፍጠር በትብብር መሥራት እንደሚቻል በተግባር እያሳየን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የጅቡቲ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር መሐመድ አሶዌ ቡህ በበኩላቸው፤ የሆራይዘን ፕሮጀክት ለአገራቱ የጋራ እድገትና ብልጽግና ባለን ራዕይ በቀጣናው የቴሌኮም መሠረተ ልማት ትስስር አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማትን በጋራ የመገንባት አቅማችንን የሚያሳይ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ያለንን ሚና ያጠናክራል።
የሱዳቴል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ማግዲ ኤም አብደላ ታሃ በበኩላቸው፤ "የሆራይዘን ፕሮጀክት ከመሠረተ ልማት ግንባታነት ባሻገር በአፍሪካ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች መካከል ለሚደረግ የፈጠራ አጋርነት ህያው ምስክር ነው" ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የጋራ ራዕይና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ሲጣጣሙ፣ ፉክክር በትብብር ሲተካ የሚገኘውን ውጤት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ሆራይዘን ለመላው የአፍሪካ አህጉር እንደ መልካም ተሞክሮ ሊወሰድ የሚችል ፕሮጀክት ነው ማለታቸውን ኢትዮ ቴሌኮም ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መረጃ አስታውቋል።
#ኢትዮቴሌኮም #ጅቡቲቴሌኮም #ሱዳቴልግሩፕ #የኦፕቲካልፋይበር #horizon #connectivity

❤2
ኢትዮጵያ በጉባኤው ብሄራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በቂ ዝግጅት አድርጋለች - አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው
✍️ ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ 179 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች ስልጠና ወስደዋል
++++++++++++++++
#ጋዜጣ-ፕላስ_ ከየካቲት ሰባት እስከ ስምንት 2018 ዓ.ም በሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በቂ ዝግጅት ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የዘንድሮው የህብረቱ መሪ ቃል በውኃ ሀብት አጠቃቀምና በንፅህና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
ጉባኤውን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳሰታወቁት፣ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በቂ ዝግጅት አድርጋለች። የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከየካቲት አራት እስከ አምስት 2018 ዓ.ም 41ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባና ከየካቲት ሰባት እስከ ስምንት 2018 ዓ.ም ድረስ 39ኛው የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። ጉባኤውን በስኬት ለማጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ ጉባኤው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የይዘትና የሎጅስቲክ ዝግጅቷን አጠናቃለች። የአገርን ገፅታ ለመገንባትና ለማስተዋወቅ ጉባኤው ልዩ ጠቀሜታ እንዳለውም ቃለ አቀባዩ ገልጸዋል።
ለዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ 179 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን አምባሳደሩ ጠቅሰዋል። ለጉባኤው የሚያስፈልገውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
#የዲፕሎማሲከተማ #ጋዜጣ_ፕላስ #ምክክር #AfricaUnion #NationalDialogue

❤3
በአማራ ክልል 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይሳተፋሉ
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ _ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንደሚሳተፉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሰታወቀ።
የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ለኢቢሲ እንደገለጹት ከለውጡ በኋላ በተዘረጋው አሳታፊ ምኅዳር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከመንግሥት ጋር በመቀናጀትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በመመደብ አዲስ የፖለቲካ አውድ መፍጠር መቻላቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የዲጂታል አገልግሎት አማካኝነት እየመዘገቡ መሆኑን አቶ ተስፋሁን ገልጸዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ ይሰራልም ብለዋል።
ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም አስገንዝበዋል።
#የኔ_ድምጽ #የምርጫ_ጊዜ #ሰላማዊ_ምርጫ #ዴሞክራሲ_ለኢትዮጵያ