“ወደቀይ ባህር መውጣት የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ለመከላከል ያስችላል”
- ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ
የቀድሞ ባህር ኃይል አባል
++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለሷ ለደኅንነቷ መጠበቅና ታሪካዊ ጠላቶቿ የሚሸርቡትን ሴራ ለመከላከል ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት የቀድሞ የባህር ኃይል አባል ጁኒየር ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ ገለጹ።
ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የውስጥ አለመረጋጋትና የግጭት ምንጮች ከዓባይና ከቀይ ባህር ጋር የተያያዙ ሲሆን፣ ሀገሪቱ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቋ አንደኛውን ሥጋት መቅረፍ ተችሏል።
ኢትዮጵያ ደኅንነቷን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ፣ የቀጠናውን ሰላም ለመጠበቅና ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ወደ ቀይ ባህር መውጣት እንዳለባትም አስረድተዋል።
ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት "ጓዳ ተከራይታ ሳሎን ላይ ያለ ነፃነት" እየተንቀሳቀሰች መሆኑን የጠቀሱት ሌፍተናንቱ፤ ይህ ሁኔታ ለሉዓላዊነትና ለእኩል ተጠቃሚነት ሳንካ በመሆኑ አጀንዳው እውን እንዲሆን የቀድሞ የባህር ኃይል አባላትና ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ መክረዋል።
ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለሷ ተሰሚነቷን ከማጎልበት ባለፈ ለሀገራዊ ህልውና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ቀይ_ባህር #ኢትዮጵያ #የባህር_ኃይል #ሉዓላዊነት #የሀገር_ደኅንነት

👍3❤2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ጥር 26 ቀን 2018 ዓም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ ይሰጣሉ።
የምክር ቤቱን ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ የፌስቡክ፣ የቴሌግራም፣ የቲክቶክና የኤክስ 𝕏 (ትዊተር) ገጾች በቀጥታ እንድትከታተሉን እንጋብዛለን፡፡ #PMOEthiopia #የጠሚሩምላሾች #PMAbiyResponds

👍2❤1
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸው ጥያቄዎች
👉 በአንዳንድ የአማራና የኦሮሚያ ክልል የሚስተዋሉ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ምን ተሰርቷል?
👉 7ኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ እንዲሆንና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት እንዳይስተጓጎል በመንግሥት በኩል እየተሰሩ ያሉ ጉዳዮች ላይ ምንድናቸው ?
👉ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆንና የቀጣይ የሀገሪቱ መጻሂ እድል ብሩህ እንዲሆን ከማን ምን ይጠበቃል?
👉 በተለያዬ ጊዜ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ምን እየተሰራ ነው?
👉 ህወሐት ለዓመታት ሲያደርግ እንደኖረው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለፖለቲካ እየተጠቀመ ድጋፍ እንዳይደረግና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ እያደረገ ይገኛል። ይህንን ሁኔታ ለመፍታት በመንግሥት በኩል ምን እየተሰራ ይገኛል?
👉 በትግራይ ክልል የህውሃት ክፋይ በሆነው የአዛውንቶች ቡድን ምክንያት በክልል ስርዓት አልበኝነትና የግጭት ድባብ ዳግም እንዲያንዣብብ፣ የትግራይ ህዝብም በውስብስብ ችግር ውስጥ ይገኛል፡፡ የትግራይ ክልል አሁናዊ የሰላም ሁኔታ ምን ላይ ይገኛል?
👉 የትግራይ ክልል በሃገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረውና 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማድረግ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችች ምንድናቸው?
5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ ይሰጣሉ።
#የጠሚሩምላሾች #PMAbiyResponds #Ethiopia #parlament

👍5❤2
"ኢትዮጵያ ቀይ ባህር አይገባትም የሚል አካል የተፈጥሮ ህግን የጣሰ ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ ቀይ ባህር አይገባትም የሚል አካል የተፈጥሮ ህግን የጣሰ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የኢትዮጵያና የቀይ ባህር ግንኙነት የሰው ልጅ ከውልደት እስከ ሞት ካለው ሂደት ጋር የተቆራኘ ነው፡፡
ቀይ ባህርና ኢትዮጵያ ያላቸው እውነታ ይህ በመሆኑ የማይነጣጠሉ ናቸው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቀይ ባህር አይገባትም የሚል አካል ከዚህ የተፈጥሮ ሕግ ጋር የሚቃረን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያም ቀይ ባህር ካለው በርካታ ሃብት ጥቂቱን መጠየቋን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጠቃሚነት አሁንም አብሮ በማደግ መርህና በዲፕሎማሲ መንገድ መጠየቋን ትቀጥላለች፡፡ ከቀይ ባህር የሚያግዳት አካል አይኖርም፡፡
በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ-ፕላስ#ቀይ ባህር#ኢትዮጵያ #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

❤4👍1
በቀጣይ አምስት ዓመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ይገነባሉ
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በቀጣይ አምስት ዓመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፤ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ አምስት ዓመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ለመገንባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ቤቶቹን በመንግስት፣ በግል፣ በመንግስትና በግል አጋርነት ለመገንባት ስራዎች መጀመራቸውን ጠቅሰው፣ የባንክ፣ ዲዛይን፣ የመሬትና የፖሊሲ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ብረት፣ ሲሚንቶና ሌሎች ግብዓቶችን ለማምረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በዳግማዊት አበበ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

❤10👍3
የሆራይዘን ፋይበር ኢንሼቲቭን እውን ለማድረግ የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ
+++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ_ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ጅቡቲ ቴሌኮም እና ሱዳቴል ግሩፕ የሆራይዘን ድንበር ተሻጋሪ የፋይበር መስመር ዝርጋታን እውን ለማድረግ የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት በዛሬው ዕለት በጅቡቲ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ከፍተኛ አቅም ያለው ድንበር ተሻጋሪ የኦፕቲካል ፋይበር መሠረተ ልማት ለመዘርጋትና የቀጣናውን ዲጂታል ትስስር ወደ ላቀና አስተማማኝ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በኢትዮ ቴሌኮም፣ በጅቡቲ ቴሌኮምና በሱዳቴል ግሩፕ መካከል የተደረገው የሦስትዮሽ ስምምነት፤ የጋራ የሆነ የዲጂታል አቅም ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል።
የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቭ ጠንካራና ከፍተኛ አቅም ያለው፣ አፍሪካን በዲጂታል የሚያስተሳስር የኮኔክቲቪቲ ኮሪደር ለመፍጠር የተወሰደ ወሳኝ እርምጃ ነው ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የጅቡቲን የባሕር ውስጥ የፋይበር ኬብሎች በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ ከሱዳን ጋር በማስተሳሰር፤ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስርን የሚያጠናክር፣ አስተማማኝ የየብስ መስመር ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ዋል።
“ይህን ፕሮጀክት እጅግ ልዩ የሚያደርገው አፍሪካዊ አጋርነትን ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ የዲጂታል መሠረተ ልማት ሀብትን በማቀናጀት፤ የአፍሪካ ኦፕሬተሮች ተጨባጭ የኮኔክቲቪቲ ተግዳሮቶችን በመፍታት ለደንበኞች፣ ለኢንተርፕራይዞችና ለግዙፍ የዳታ ኩባንያዎች አዲስ እሴት ለመፍጠር በትብብር መሥራት እንደሚቻል በተግባር እያሳየን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የጅቡቲ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር መሐመድ አሶዌ ቡህ በበኩላቸው፤ የሆራይዘን ፕሮጀክት ለአገራቱ የጋራ እድገትና ብልጽግና ባለን ራዕይ በቀጣናው የቴሌኮም መሠረተ ልማት ትስስር አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማትን በጋራ የመገንባት አቅማችንን የሚያሳይ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ያለንን ሚና ያጠናክራል።
የሱዳቴል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ማግዲ ኤም አብደላ ታሃ በበኩላቸው፤ "የሆራይዘን ፕሮጀክት ከመሠረተ ልማት ግንባታነት ባሻገር በአፍሪካ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች መካከል ለሚደረግ የፈጠራ አጋርነት ህያው ምስክር ነው" ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የጋራ ራዕይና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ሲጣጣሙ፣ ፉክክር በትብብር ሲተካ የሚገኘውን ውጤት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ሆራይዘን ለመላው የአፍሪካ አህጉር እንደ መልካም ተሞክሮ ሊወሰድ የሚችል ፕሮጀክት ነው ማለታቸውን ኢትዮ ቴሌኮም ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መረጃ አስታውቋል።
#ኢትዮቴሌኮም #ጅቡቲቴሌኮም #ሱዳቴልግሩፕ #የኦፕቲካልፋይበር #horizon #connectivity

❤2