Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.7K subscribers
41.4K photos
347 videos
7 files
5.83K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የሐረር ጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ አዲስ ገፅታ በምስል
👍4
የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐርን አግኝቼ በቁልፍ የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

‎ከውይይታችን ጎን ለጎን በተካሄደው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ማህቀፍ ሥር የኢንቨስትመንት እና ኃብት አስተዳደር የቴክኒካል ትብብር የመግባቢያ ሥምምነት እና የሁለት የጋራ የልማት ስምምነቶች ፊርማ መርሃ ግብር ላይም ተገኝተናል።

እነዚህም የሁርሶ-አይሻ 400 ኪሎ ቮልትና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች ስምምነቶች ናቸው። እነዚህ ስምምነቶች ትብብርን በማጠናከር እና ስትራቴጂያዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ርምጃን የሚያሳዩ ናቸው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
❤7🥰2
“ወደቀይ ባህር መውጣት የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ለመከላከል ያስችላል”

- ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ
የቀድሞ ባህር ኃይል አባል
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለሷ ለደኅንነቷ መጠበቅና ታሪካዊ ጠላቶቿ የሚሸርቡትን ሴራ ለመከላከል ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት የቀድሞ የባህር ኃይል አባል ጁኒየር ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ ገለጹ።

ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የውስጥ አለመረጋጋትና የግጭት ምንጮች ከዓባይና ከቀይ ባህር ጋር የተያያዙ ሲሆን፣ ሀገሪቱ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቋ አንደኛውን ሥጋት መቅረፍ ተችሏል።

ኢትዮጵያ ደኅንነቷን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ፣ የቀጠናውን ሰላም ለመጠበቅና ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ወደ ቀይ ባህር መውጣት እንዳለባትም አስረድተዋል።

ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት "ጓዳ ተከራይታ ሳሎን ላይ ያለ ነፃነት" እየተንቀሳቀሰች መሆኑን የጠቀሱት ሌፍተናንቱ፤ ይህ ሁኔታ ለሉዓላዊነትና ለእኩል ተጠቃሚነት ሳንካ በመሆኑ አጀንዳው እውን እንዲሆን የቀድሞ የባህር ኃይል አባላትና ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ መክረዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለሷ ተሰሚነቷን ከማጎልበት ባለፈ ለሀገራዊ ህልውና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ቀይ_ባህር #ኢትዮጵያ #የባህር_ኃይል #ሉዓላዊነት #የሀገር_ደኅንነት
👍3❤2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ጥር 26 ቀን 2018 ዓም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ ይሰጣሉ።

የምክር ቤቱን ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ የፌስቡክ፣ የቴሌግራም፣ የቲክቶክና የኤክስ 𝕏 (ትዊተር) ገጾች በቀጥታ እንድትከታተሉን እንጋብዛለን፡፡ #PMOEthiopia #የጠሚሩምላሾች #PMAbiyResponds
👍2❤1
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸው ጥያቄዎች

👉 በአንዳንድ የአማራና የኦሮሚያ ክልል የሚስተዋሉ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ምን ተሰርቷል?

👉 7ኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ እንዲሆንና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት እንዳይስተጓጎል በመንግሥት በኩል እየተሰሩ ያሉ ጉዳዮች ላይ ምንድናቸው ?

👉ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆንና የቀጣይ የሀገሪቱ መጻሂ እድል ብሩህ እንዲሆን ከማን ምን ይጠበቃል?
👉 በተለያዬ ጊዜ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ምን እየተሰራ ነው?

👉 ህወሐት ለዓመታት ሲያደርግ እንደኖረው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለፖለቲካ እየተጠቀመ ድጋፍ እንዳይደረግና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ እያደረገ ይገኛል። ይህንን ሁኔታ ለመፍታት በመንግሥት በኩል ምን እየተሰራ ይገኛል?

👉 በትግራይ ክልል የህውሃት ክፋይ በሆነው የአዛውንቶች ቡድን ምክንያት በክልል ስርዓት አልበኝነትና የግጭት ድባብ ዳግም እንዲያንዣብብ፣ የትግራይ ህዝብም በውስብስብ ችግር ውስጥ ይገኛል፡፡ የትግራይ ክልል አሁናዊ የሰላም ሁኔታ ምን ላይ ይገኛል?

👉 የትግራይ ክልል በሃገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረውና 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማድረግ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችች ምንድናቸው?

5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ ይሰጣሉ።

#የጠሚሩምላሾች #PMAbiyResponds #Ethiopia #parlament
👍5❤2