Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
✔
24.7K subscribers
41.4K photos
347 videos
7 files
5.83K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኢትዮጵያ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ በመመረቅ፤ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ አዲስ ታሪክ የጻፈ ታላቅ እጥፋት አስመዝግባለች። ይህ ውጤት የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችንን ለማስፋፋት የወሰድነው ወሳኝ እርምጃ ምልክት ነው።

የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት በቴክኖሎጂ ለሚመራ ኢኮኖሚ ዋነኛው የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ መጠን፤ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ያላትን ርዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ ብቻ ሳትሆን ከፍ ያሉ ርዕዮቿን ለመፈፀም በቂ አቅም ያላት መሆኑንም በተግባር አሳይቷል።

#PMOEthiopia
❤8
የሐረር ጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ አዲስ ገፅታ በምስል
👍4
የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐርን አግኝቼ በቁልፍ የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

‎ከውይይታችን ጎን ለጎን በተካሄደው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ማህቀፍ ሥር የኢንቨስትመንት እና ኃብት አስተዳደር የቴክኒካል ትብብር የመግባቢያ ሥምምነት እና የሁለት የጋራ የልማት ስምምነቶች ፊርማ መርሃ ግብር ላይም ተገኝተናል።

እነዚህም የሁርሶ-አይሻ 400 ኪሎ ቮልትና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች ስምምነቶች ናቸው። እነዚህ ስምምነቶች ትብብርን በማጠናከር እና ስትራቴጂያዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ርምጃን የሚያሳዩ ናቸው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
❤7🥰2
“ወደቀይ ባህር መውጣት የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ለመከላከል ያስችላል”

- ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ
የቀድሞ ባህር ኃይል አባል
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለሷ ለደኅንነቷ መጠበቅና ታሪካዊ ጠላቶቿ የሚሸርቡትን ሴራ ለመከላከል ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት የቀድሞ የባህር ኃይል አባል ጁኒየር ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ ገለጹ።

ሌፍተናንት ኃለፎም መሠለ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የውስጥ አለመረጋጋትና የግጭት ምንጮች ከዓባይና ከቀይ ባህር ጋር የተያያዙ ሲሆን፣ ሀገሪቱ የታላቁ የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቋ አንደኛውን ሥጋት መቅረፍ ተችሏል።

ኢትዮጵያ ደኅንነቷን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ፣ የቀጠናውን ሰላም ለመጠበቅና ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ወደ ቀይ ባህር መውጣት እንዳለባትም አስረድተዋል።

ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት "ጓዳ ተከራይታ ሳሎን ላይ ያለ ነፃነት" እየተንቀሳቀሰች መሆኑን የጠቀሱት ሌፍተናንቱ፤ ይህ ሁኔታ ለሉዓላዊነትና ለእኩል ተጠቃሚነት ሳንካ በመሆኑ አጀንዳው እውን እንዲሆን የቀድሞ የባህር ኃይል አባላትና ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ መክረዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለሷ ተሰሚነቷን ከማጎልበት ባለፈ ለሀገራዊ ህልውና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ቀይ_ባህር #ኢትዮጵያ #የባህር_ኃይል #ሉዓላዊነት #የሀገር_ደኅንነት
👍3❤2