በሐዋሳ ከተማ የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የኮማንዶ ትርኢት እየተካሔደ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማዘዣ በአምስት ሻለቃ ያሰለጠናቸው የኮማንዶ አባላት የልዩ ግዳጅ ትርኢት እያሳዩ ነው።
በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፓሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በትርኢቱ የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የአየር ወለድ አባላት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢ ከሔሊኮፒተር የፎቅ ዝላይ በማድረግ የጸረ ሽብርና ጥቃት ትዕይንት አሳይተዋል።
በቶጋ፣ በወንዶ ጢቃና በወንዶ ገነት አካባቢ የሜዳና የገደል ዝላይ፤ ከሒሊኮፒተር በፓራሹት በመውረድ ትዕይንቱን እያሳዩ ነው።
የልዩ ሀይል ፀረ ሽብር ስልታዊ ተኩስ ትርኢትም በዝግጅቱ እየታየ ይገኛል።
በሌላ በኩል በልዩ ዘመቻዎች ሀይል የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላት የባህር ላይ ትርኢት በልዩ ሁኔታ እያቀረቡ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማዘዣ በአምስት ሻለቃ ያሰለጠናቸውን የኮማንዶ አባላት ነገ እንደሚያስመርቅ ኢዜአ ዘግቧል።

የመንግሥትም ሆኑ የግል ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ብቻ እንደሚማሩ ተገለጸ
*******************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- የመንግሥትም ሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ከጥቅምት 30 ጀምረው በቀናት ፈረቃ ሰኞ፣ ረዕቡ እና ዓርብ ሌሎቹን ደግሞ ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ ብቻ እንደሚያስተምሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እንደተናገሩት፤ ትምህርት የሚጀመረው በሁለት ዙር ነው። የመጀመሪያው ዙር የ8ኛ ክፍል የክልል ፈተና፣ የ12 ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተናን ለማካሔድ ከጥቅምት 16 ቀን እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ያለፈረቃ ሳምንቱን ሙሉ የክለሳ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል። ይህ ለፈተና እንዲዘጋጁ ያመለጣቸውን እንዲማሩ ለማድረግ ነው።
ሁለተኛው ዙር ማለትም ቀሪዎቹ ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ የሚማሩ ሲሆን፤ ይህ የሆነው ከአዋጭነት አንፃር ታይቶ መሆኑን አስረድተዋል። ቀድሞ ጠዋትና ከሰዓት በሚል ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የቀናት ፈረቃ የተሻለ ይሆናል ተብሎ ውሳኔ የተላለፈው ምልልሱን፣ መውጣት መውረዱን፣ የትራንስረፖርት ሁኔታን፣ ወጪውን እና ለወላጆች ያለውን አመቺነት ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አብራርተዋል።
በቀሪዎቹ ቀናት ተማሪዎቹ ለብቻቸው ከንክኪ ነፃ ሆነው በቤታቸው መልመጃዎችን እና የቤት ሥራዎችን እንደሚሠሩ እንዲሁም ጥናት እንደሚያከናውኑ ታሳቢ መደረጉን ጠቅሰው፤ በፈረቃ ሲማሩ እንደየክፍሉ ስፋት በክፍል ውስጥ የሚኖራቸውን ንክኪ ለመቀነስ ቁጥራቸው ከ20 እስከ 25 ብቻ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
አቶ አዲሱ እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች ተራርቀው እንዲማሩ አሁን ባሉት ክፍሎች ላይ ተጨማሪ 2ሺህ 300 ክፍሎች እንደሚያስፈልጉ ታውቋል። ሆኖም በአዲስ አበባ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በትምህርት ቤቶች ግቢም ሆነ በአካባቢያቸው በቂ ይህን ያህል ክፍሎችን የመገንቢያ ቦታ ባለመኖሩ 1ሺህ 720 ክፍሎችን በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመገንባት ዲዛይኑ ተከናውኖ፤ ውል የተገባ ሲሆን፤ ግንባታውን እስከ ጥቅምት 30 ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
የከተማ አስተዳደሩ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ቢያንስ ሁለት ሁለት የሙቀት መለኪያ በልዩ ሁኔታ በቀጥታ ግዢ እንዲከናወን ውሳኔ ያስተላለፈበት ሁኔታ መኖሩንም ገልጸው፤ ከጤና ቢሮ ጋር በመግዛት ለትምህርት ቤቶች ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል። አያይዘውም ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክፍለ ከተማ እና ከትረስት ፈንድ በማፈላለግ እያንዳንዱ ተማሪ ማስክ እንዲያገኝ ጥረት መደረጉን በመጠቆም፤ ማስኩ ለሁሉም እንደሚዳረስ አመልክተዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ዩኒፎርም መስጠት እና ምገባ ማከናወን እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ዕድሳት ላይ በመሥራት ታሪካዊ ውሳኔዎች ተላልፈዋል በማለት ያስታወሱት አቶ አዲሱ፤ ዘንድሮ ደግሞ ትምህርቱ ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ የትምህርት ጤና (school health) ፕሮግራም እንደሚተገበር ጠቁመዋል።
በትምህርት ዘርፉ ላይ የተማሪዎች የጤና ክትትልን ለማካሄድ በካቢኔው ልዩ ውሳኔ 2ሺህ 52 በአካባቢ ጥበቃ እና በጤና ላይ የሚሠሩ ነርሶች በኮንትራት እንዲቀጠሩ በመፈቀዱ ቅጥር እየተፈፀመ ነው ብለዋል።
ውሳኔው ጤናማ ተማሪዎች በጤናማ አካባቢ እንዲማሩ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ የከተማው አስተዳደር ከሁሉም ጉዳይ በላይ ለትምህርት ትኩረት ሰጥቶ እየደገፈ በመሆኑ ትምህርቱን እየዘመነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 13/2013
ምህረት ሞገስ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/ethpress
ለአጫጭር ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ የትዊተር አካውንታችን ይከተሉ
https://twitter.com/home?lang=en
በጋዜጦቻችን የወጡ ዜና፣ አርቲክልና ኤክስክሉሲቭ ቃለ መጠይቆችን ዌብሳይታችን ላይ ያገኛሉ
https://www.press.et/️

Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጪው ሳምንት ይጀመራል፡፡
--------------------------------------------
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30 /2013 ዓ.ም በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የፈተና ምዝገባ ሂደቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማካሄድ በተዘጋጀው ሶፈትዌር “Enrollment Kit” ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የአይ ሲ ቲ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በየክልል ከተሞች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በመላው ሀገሪቱ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሷል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በመላው ሀገሪቱ ዛሬ (ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም) ከረፋዱ 5 ሰአት ጀምሮ ለተወሰኑ ሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሷል።
የኃይል ማመንጫዎችን ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር መልሶ የማገናኘት ሥራው በስኬት በመጠናቀቁ ደረጃ በደረጃ ሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ተደርጓል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ህድብ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ትችት እያስከተለባቸው ነው
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ምሽት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ህድብ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ከተለያዩ ወገኖች ትችት እያስከተለባቸው ነው።
የዴሞክራት ፓርቲ ኮንግረስማን የሆኑት የኮሎራዶው ጃሶን ክሮው በትዊተር ገፃቸው ፕሬዝዳንቱ ግድቡን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ ሀላፊነት የጎደለው እና መረጃ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል::
ሚስተር ክሮው በዚሁ መልዕክታቸው አሜሪካ ሚዛናዊ አደራዳሪ በመሆን ዛላቂ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈጠር መስራት እንዳለባት በመጥቀስ የውጭ እርዳታን ማገድ የለባትም በማለት የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተችተውታል።

"ማንም ገዝቶን አያውቅም። ወደፊትም ማንም አይገዛንም። ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም። ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም"
- ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ በፍጣሪዋ ታምና በሕዝቧ አንድነትና ጽናት የቆመች ሀገር ናት። ጥቂት ሰጥተው ብዙ ሊያዟት በሚሞክሩ ተማምና አታውቅም። ሕይወታቸውን ሰጥተው ሊታዘዟት በተዘጋጁ ልጆቿ እንጂ። ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ነው። የገነቧት ደግሞ ልጆቿ ናቸው። እነዚህ ልጆቿ በከፈሉት መሥዋዕትነት ዓለምን ጉድ ያሰኙ ታሪኮችን ሠርታለች። እነዚህን አስደናቂ ታሪኮችን ስትሠራ አብረዋት ታሪክ የሠሩ ወዳጆች ነበሯት። የከዷት ወዳጆችም ነበሩ። ይህ ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም።
ነገር ግን የዓለም ታሪክ ያረጋገጣቸው ሁለት ሐቆች አሉ። ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም የሚለው ቀዳሚው ነው። ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለአንድ ዓላማ ከቆሙ ድል ማድረጋቸው አይቀርም የሚለው ደግሞ ሁለተኛው። የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ግድብ ነው። ኢትዮጵያውያን፣ አሰቡት፤ ኢትዮጵያውያን ጀመሩት፤ ኢትዮጵያውያን ገነቡት፤ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ይጨርሱታል። አይቀሬ ነው።
የሚያዋጣን ኅብረት አንድነታችን ነው። ለእኛ ያለነው እኛ መሆናችንን ዐውቀን ስለ እኛ ጉዳይ እኛው ራሳችን ኢትዮጵያን አለንሽ እንበላት። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን ለኢትዮጵያ እንቁም። ከባዱ ፈተና ከውጭ የሚመጣው አይደለም። ከባዱ ፈተና ተለያይተን ችግሩን ከተጋፈጥነው ነው።
ማንም ገዝቶን አያውቅም። ወደፊትም ማንም አይገዛንም። ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም። ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም።
ክንዳችንን እናበርታ። ትከሻችንን እናስፋ። ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር።
በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ እንቀርም። ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም። አንድ ሆነን የምንይዘው ጋሻ ኃያላኑን ሁሉ ሲመክት የኖረ ነው። ዛሬም ያንን ጋሻ በአንድነት እናንሣ። ሁላችንም፣ በየቦታችን፣ 24 ሰዓት፣ ለኢትዮጵያ እንቁም።

በዚህ አመት 5 ሚሊዬን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል:- ትምህርት ሚኒስቴር
------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በBiometric Digital Registration በመጪው ሰኞ እንደሚጀመር አስታውቃል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ የመጀመሪያዎቹ 450ሺ ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ እንደሚኖራቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ገለፀዋል።
በዚህ አመት ደግሞ 5 ሚሊዬን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል ብለዋል።
የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማድረግ አንዱ አካል ነው።

ኢትዮጵያውያን በፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር አይሸበሩም ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያውያን በፕሬዝዳንት ትራምፕ የትናንት ምሽት ንግግር ፈጽሞ አይሸበሩም ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ የትናንት ንግግር ሀላፊነት የጎደለው ነው ሲሉም ነው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የተናገሩት።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለሚናገሩት ጉዳይ ግንዛቤ እንደሌላቸው አቶ ኃይለማርያም ገልጸዋል።
አቶ ኃይለማርያም በዚሁ መልዕክትቸው፤ "ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን እንዲህ ባለ ሀላፊነት በጎደለው ንግግር አይሸበሩም፤ ታሪክ ሁሉንም ያስተምራል" ሲሉም ሀሳባቸውን ቋጭተዋል።

የፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ለግብጽ የወገነና ኢትዮጵያዊያንን በአግባቡ ካለማወቅ የተሰነዘረ ነው ሲሉ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አስታወቁ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አስተያየት ለግብጽ ወገንተኝነት የታየበት፣ ስለግደቡ ትክክለኛ መረጃ እንደሌላቸው እና ኢትዮጵያዊያንን በአግባቡ እንደማያውቁ የተያበት ነው ሱሉ የታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን የትናንት ምሽት ንግግር ተከትሎ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ የሰጡት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ እንደተናገሩት፤ የፕሬዝዳንቱ አስተያየት አሜሪካ ለግብጽ ያላትን ወገንተኝነት ዳግም በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል።
የፕሬዝዳንቱ ንግግር ከአንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚጠበቅ አይደለም ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ንግግራቸው ለግብጽ ያላቸውን ወገንተኝነት በግልጽ ያሳየ ነው። ይሄ ደግሞ የሆነው አገራቸው ከእስራኤል እና ከግብጽ ጋር ካላት ግንኙነት ጋር ይያያዛል ሲሉም ነው ያብራሩት።
"ግድቡ የተጀመረውና እዚህ የደረሰው በህዝብ ድጋፍ ነው፤ ዳር የሚደርሰውም በህዝብ ድጋፍ ነው፤ አሁንም ከተባበርን ይሄን አይደለም ሌላ ግድብ መስራት እንችላለን” ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ለግድቡ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ በአግባቡ እንዳልተረዱት ንግግራቸው ያሳያል ብለዋል።
ኢትዮጵያን የወረረው ጣሊያን አድዋ ላይ ድል የተነሳው በኢትዮጵያዊያን ትብብር እንጂ በውጭ ሀይል ድጋፍ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ አሁንም ከ70 በመቶ በላይ የደረሰን ግድብ ለማጠናቀቅ የሚያቆመን ምንም አይነት ሀይል የለም ሲሉ ነው የመንግስትንና የህዝቡን የትብብር መንፈስ ያስረዱት።
አንድ አንዱ ንግግራቸው ኢትዮጵያን በውል ካለማወቅ የመነጨና ኢትዮጵያዊያንም አገራቸውንና ድንበራቸወን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ካለመገንዘብ የተነሳ የሰጡት ሃሳብ ስለሆነ እንደ እርሳቸው አይነት ካላ ፕሬዝዳንት የሚጠቅ ንግግር ነው ሲሉም ነው ዶ/ር አረጋዊ
የተናገሩት።
ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ የጀመረችው ለጋራ ተጠቀሚነት መሆኑ እየታወቀ የዚህ አይነት ማስፈራሪያ መሰንዘር ፋይዳ የሌለው መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር አረጋዊ፤ ኢትዮጵያዊያን በዛቻና ማስፈራሪያ የማይንበረከኩ መሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል ሲሉም ነው የፕሬዝዳንቱን ንግግር የተቹት።
“በውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ተበብረን ግድቡን ከዳር ለማድረስ መፍትሄው በእጃችን ነውና አሁን ካለውም በላይ መተባበር አለብን” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት ሲፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ አመት ያህል የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት ሲፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የሀይል ስርቆቱ ሲፈፀም የቆየው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ዮቴክ ኮንስትራክሽን ህንጻ አካባቢ ነዉ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ እንዳስረዱት፤ ተጠርጣሪው ግለሰብ በእንጀራ ንግድ ላይ የተሰማራ ሲሆን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንብ እና አሰራር ውጪ የኤሌክትሪክ ሃይል ከቀጥታ መስመር በመቀጠል ለ አንድ አመት ያለአግባብ ሲጠቀም ቆይቷል፡፡
ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ እና መረጃው ከፖሊስ የደረሳቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቁጥጥር ሰራተኞ ወደቦታው ሄደው ባደረጉት ማጣራት ግለሰቡ በገንዘብ ሲተመን 55 ሺ 668 ብር ከ05 ሳንቲም በድርጅቱ ላይ ጉዳት ማድረሱን እና ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ ገልፀዋል፡፡
ድርጊቱ አስከ 5 አመት በሚደርስ እስራት እና እስከ 20ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተገልጿል።

እገዳ የተጣለበት ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት:- ትምህርት ሚኒስቴር
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመከተል እና ወላጆች ባቀረቡት ተደጋጋሚ ቅሬታ እገዳ ከተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የግሪክ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት፡፡
እገዳው የተነሳው ትምህርት ሚኒስቴር ባቋቋመው ቡድን ባደረገው የሱፐርቪዝን ስራ መሰረት ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን መስተካከያ በማድረጉ እና ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት በማጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ትምህርት ቤቱም ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስራውን ማከናውን እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ሌሎች ትመህርት ቤቶችም ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያ በመከተል የመማር ማስተማር ሄደቱን ማስቀጠል እንዳለባቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በሰባት ቀናት ውስጥ ድርድር በማካሄድ በቀጣይ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከስምምነት ለመድረስ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በሰባት ቀናት ውስጥ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ የድርድሩ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ ስምምነት ለመድረስ ከመግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ።
ሀገራቱ ላይ ልዩነት ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ልዩነቶችን ለማጥበብ እና ውጤቱንም ለውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀጣይ ስብሰባ ለማቅረብም ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ቀደም ብሎ በጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሃገራቱ በጻፉት ደብዳቤ እና ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓም በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂደዋል፡፡
ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እየተካሄደ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክሯል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲይርል ራማፎዛ ቀደም ብሎ በጥቅምት መጀመሪያ ከኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች ጋር በስልክ ባደረጓቸው ውይይቶች በተደረሰው መግባባት እና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ድርድሩን ለመቀጠል ስምምነት ተደርሷል።
ሀገራቱ በሰባት ቀናት ውስጥ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ የድርድሩ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ ስምምነት መድረስ፣ ሀገራቱ ላይ ልዩነት ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ልዩነቶችን ለማጥበብ እና ውጤቱንም ለውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀጣይ ስብሰባ ለማቅረብ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
የመጀመሪያው የቴክኒክ ስብሰባም በሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትር ሰብሳቢነት እደሚከናወን ይጠበቃል ሲል ያስታወቀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ነው።

"የዶናልድ ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ለሚመጣ ነገር ሁሉ አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን"
"24 ሰዓት ዓይናችን የህዳሴው ግድብ ላይ ነው"
-የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ
ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ
***********************************
(ኢ ፕ ድ)
የአሜሪካን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር በአገር ሉአላዊነት ላይ የተቃጣ በመሆኑ ይህንን ተከትሎ ለሚመጣ ነገር ሁሉ አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዝግጁ መሆኑን አስታወቀⵆ
የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ የፕሬዝዳንት ትራንፕ ንግግር ሀያል አገርን እመራለሁ ከሚል ፕሬዝደንት የሚጠበቅ አይደለም። የአንድን አገር ሉአላዊነት በንግግርም ቢሆን መጣስ ከባድ ጥፋት በመሆኑ ይህንን ተከትሎ ሊመጣ የሚችል ማንኛውንም አይነት ጥቃት ለመመከት አየር ሃይሉ ሙሉ ዝግጁነት አለውⵆ
እንደ ሜጀር ጀነራል ይልማ ገለጻ፤ ለፕሬዝዳንቱ ንግግር የአገር መሪዎችና ዲፕሎማቶች በዲፕሎማሲው መድረክ መልስ እንደሚሰጡ ሁሉ፤ አየር ሃይሉ ደግሞ ፕሬዝደንቱ ለጎሰሙት የጦርነት ነጋሪት አስፈላጊውን መልስና እርምጃ ይወስዳልⵆ
“ከአባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ጭቅጭቅ እያነሱ ያሉ አካላት ከ 2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው በእግረኛ ጦር ይዋጋሉ ብለን አናስብም፤ በመሆኑም ወደ ግጭት ከተገባም ግጭቱ በቀጥታ ከአየር ሃይል ጋር እንደሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ደረጃ እነሱ ምንድን ነው ያላቸው? የመሳሪያ የቴክኖሎጂያቸው፤ የሰው ሃይል ብቃት የስልጠና ደረጃቸው ምን ይመስላል? የሚለውን ለይተን እናውቃለን። ከዚህም ባሻገር 24 ሰዓት ዓይናችን የህዳሴው ግድብ ላይ ነው” ብለዋል አዛዡ።
የኢትዮጵያን የአየር ሃይልብቃት እኛ ከምናውቀው በላይ እነሱ ጠንቅቀው ያውቁታል፤ ስለወደዱን ወይም አቋማችንን ስለተቀበሉ ሳይሆን ሁኔታዎች ወዴት ሊሄዱ እንደሚችሉ ጠንቅቀው ያስለሚያውቁም ጭምር የሚፈጠር ጉዳይ አይኖርም ያሉት ሜጀር ጀነራል ይልማ፤ አየር ሃይሉም ለ24 ሰዓታት ለሰባት ቀናት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌለው ሀብት ላይ ቆጥቦ እየገነባው ያለው ፕሮጀክቱ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ቢሆንም፤ አየር ሃይሉ ግን በጠቅላላው የአገሪቷን መሰረተ ልማቶች የፖለቲካ የኢኮኖሚ እንዲሁም ወታደራዊ ማዕከሎችን በንቃት እንደሚጠብቅም አረጋግጠዋልⵆ
ከሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ በዝርዝር እናቀርባለን።
በእጸገነት አክሊሉ

"በራስ ሀብት መጠቀምና በጋራ መቆም እንደምንችል ዓለም ያውቀዋል፤ የተዘናጉ ካሉ ልናስታውሳቸው ይገባል''
- ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
************************
(ኢ.ፕ.ድ)
"በራስ ሀብት መጠቀምና በጋራ መቆም እንደምንችል ዓለም ያውቀዋል፤ የተዘናጉ ካሉ ልናስታውሳቸው ይገባል'' ሲሉ የአዲስ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
ምክትል ከንቲባዋ የ1495ኛውን የነብዩ መሐመድ የልደት በዓልን በማስመልከት በታላቁ አንዋር መስጂድ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዓሉ ከዚህ በፊት እንደነበረው እንዳይከበር ኮሮና ምክንያት ሆኗል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፣ አዲስ አበባ የሃይማኖት መቻቻል፣ የአብሮነት እና የአንድነት ከተማ እንድትሆን ሕዝበ ሙስሊሙ ላደረገው ተግባር ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።
ባለፈው ክረምት ሕዝበ ሙስሊሙ በኮሮና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በሐሳብ፣ በገንዘብ ባደረገው ድጋፍ የብዙዎችን ሕይወት መታደግ መቻሉን ነው የገለጹት።
ምክትል ከንቲባዋ "በራሳችን ሀብት ለመጠቀም እና ሉዓላዊነታችንን ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ በጋራ ልንቆም የሚገባበት ጊዜ ነው" ሲሉም መልክእት አስተላልፈዋል።
በሃይማኖት ሊከሰቱ የሚችሉ የግጭት አጀንዳዎችን በማክሸፍ፣ በማውገዝ እና ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ሕዝበ ሙስሊሙ እና የእምነቱ መሪዎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
"ኢትዮጵያ ለዘመናት ጸንታ የኖረችው እና ዛሬ ላይ መቆም የቻልነውም በአንድነት እና በአብሮነት ስለቆምን ነው፤ በዚህ የሚመጣብንን ምንም ክፍተት ልንሰጠውና ችላ ልንለው አይገባም" ሲሉም አክለዋል።
"የሀገራችንን ሉዓላዊት ለመዳፈር የሚሞክሩ፣ በገዛ ሀብታችን እና ንብረታችን የሚፎክሩ አንዳንድ ማስተዋል የሌላቸው መሪዎችን መስማት ጀምረናል" ያሉት ከንቲባዋ፣ በራሳችን ሀብት ለመጠቀም እና ሉዓላዊነታችንን ለማስጠበቅ ኢትዮጵያውያን ምንጊዜም የማይዘናጉበት፣ ወደ ኋላ የማይሉበት መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የፋይናንስ ተቋማት በቁጥር እንጂ በአቅም እንዳላደጉ ተጠቆመ
*******************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት በቁጥር እንጂ በአቅም እድገት አለማሳየታቸውን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ገለፁ።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶክተር ሞላ አለማየሁ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የፋይናስ ተቋማቱ አደጉ ሲባል በቁጥር እና በመጠን ነው።
በመጠን ሲባል አንድ ተቋም የሚያበድረው እና ለብድር ዝግጁ የሆነ ገንዘብ ብዛት ፣ተቋሙ ያለው ካፒታል ፣ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ሀብት፣ ያለው የሰው ሀይል የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው። በዚህም በአገሪቱ ያሉት ፋይናንስ ተቋማት በቁጥር እንጂ በአቅም አለማደጋቸው ታይቷል።
‹‹በኢትዮጵያ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለሕዝብ ተወካዮች ሲያቀርቡ ተቋማቱ አድገዋል ያሉት በቁጥር ነው›› ያሉት ዶክተር ሞላ፤ ይህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፋይናንስ ተቋማት ተደራሽነት እየጨመረ መምጣቱ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል። የባንኮች ቅርንጫፍ መብዛት እንዲሁም ከሃያ በላይ ባንኮችም መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው ወቅት መናገራቸውን ጠቅሰዋል።
የተቋማቱ ዕድገት ከመጠን አኳያ ሲታይ ግን ውስንነት እንዳለ ጠቅሰው፤ ከዚህ ቀደም ከአስር ዓመት በፊት የተከፈቱ ባንኮች አብዛኞቹ በአንጻራዊነት በመጠን የተደራጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይህ ማለት ግን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚፈልገውን ሀብት የመሸከም አቅም አላቸው ማለት አለመሆኑ አስረድተዋል።
እንደ ዶክተር ሞላ አባባል፤ ከሰሀራ በታች ባሉ አገራት የባንክን ደረጃ የሚያወጣ አንድ ድርጅት በሚያወጣው ሪፖርት አንዳቸውም የኢትዮጵያ ባንኮች ደረጃ ይዘው አያውቁም፤ ንግድ ባንክም ቢሆን በሪፖርቱ ከሚወጡ አንድ መቶ ባንኮች ደረጃ ውስጥ ቢካተትም የሚይዘው ደረጃ ግን ወደ መጨረሻዎቹ ነው።
መስፈርቱም የተደራሽነት፣ የተጠቃሚውን ፍላጎት ሟሟላት ሲሆን ይህም በብድር ፣በቁጠባ በሌሎችም ባንኩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ምን ያህል ሙሉ ነው የሚል ሲሆን ሌላው ደግሞ ብድር የማስመለስ አቅሙ ያደገ ሲሆን አንድ የፋይናንስ ተቋም አድጓል ይባላል።
የፋይናንስ ተቋማት በቁጥርም እና በመጠን ማደግ ለአገር ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ በመሆኑ መንግስት ገንዘብ ሲፈልግ ከእነዚሁ ተቋማት መበደር እንደሚችል ጠቁመዋል። ስለዚህም የፋይናንስ ተቋማቱ በቁጥር ብቻ ሳይሆን በአቅም መጎልበት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የኢኮኖሚክስ መምህሩ እና የተለያዩ ተቋማትን በምጣኔ ሀብት አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ፍስሐጽዮን መንግስቱ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ የፋይናንስ ተቋማት ዕድገት ሲባል የተቋማት በቁጥር የመጨመር ሂደት ብቻ ሳይሆን በሰው ሃብት ረገድ የሚያሳዩት እመርታም ነው።
የፋይናንስ ተቋማት ዕድገት ለአገር ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው የጠቀሱት ፕሮፌሰር ፍስሐጽዮን፤ የተለያዩ አገራት ተሞክሮ ሲታይ ተቋማቱ የሰበሰቡት አንድ ትሪሊየን ብር በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል።
አንዳንዶቹ የፋይናንስ ተቋማት አነስተኛ አቅም እንዳላቸውና እነዚህ ጥቂት አቅም ያላቸው ባንኮች በሕብረት ቢደራጁ እንደ አሜሪካው ሲቲ ባንክ፣ እንደ እንግሊዙ ቻርተር ባንክ እና እንደ ጀርመኑ ደች ባንክ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እና ለአገሪቱም ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ይናገራሉ።
እንደ ፕሮፌሰር ፍስሐጽዮን ገለጻ የፋይናንስ ተቋማት ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንዲሆን ተቋማቱ በቁጥር ብቻ ሳይሆን በመጠንም ሊበለጽጉ እንደሚገባ ተናግረዋል። አሁን ባለው ሁኔታ በአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት በቁጥር እንጂ በአቅም ብዙ እንደሚቀራቸው አመልክተዋል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 19/2013

“ወደ ግጭት ከተገባ ግጭቱ በቀጥታ ከአየር ኃይል ጋር እንደሆነ እናውቃለን” ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ
*********************************
(ኢፕድ)
ቢሾፍቱ ፦ ወደ ግጭት ከተገባ ግጭቱ በቀጥታ ከአየር ኃይል ጋር እንደሆነ እናውቃለን ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ አስታወቁ። አየር ኃይሉ የ24 ሰዓታት ዝግጁነት እንዳለው አመለከቱ ፡፡
ጀነራል ይልማ መርዳሳ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣ ከአባይ ውሃ ጋር በተያያዘ ጭቅጭቅ እያነሱ ያሉ አካላት ከ 2ሺ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው በእግረኛ ጦር ይዋጋሉ ብለን አናስብም ብለዋል ።
ወደ ግጭት ከተገባ ግጭቱ በቀጥታ ከአየር ኃይል ጋር እንደሆነ እናውቃለን ፤ ለዚህም የመሳሪያ፣ የቴክኖሎጂ ፣የሰው ኃይል ብቃት እና የስልጠና ደረጃቸው ምን ይመስላል? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ከማግኘት ጀምሮ 24 ሰዓት ዓይናችን ህዳሴው ግድብ ላይ ነው ብለዋል ።
በእኔ እምነት የኢትዮጵያን አየር ኃይል እኛ ከምናውቀው በላይ እነሱ ጠንቅቀው ያውቁታል ያሉት ሜጀር ጀነራል ይልማ ፣ እስከ አሁንም ዝም ያሉት ስለወደዱን ወይም አቋማችንን ስለተቀበሉ ሳይሆን ሁኔታዎች ወዴት ሊሄዱ እንደሚችሉም ጠንቅቀው ስለሚያውቁ እንደሆነ አመልክተዋል ።
የፕሬዚዳንቱ ንግግር በዓለም ኃያል ከሆነ ሀገር መሪ የሚጠበቅ እንዳልሆነ አመልክተዋል ። የአንድን አገር ሉዓላዊነት በንግግርም ቢሆን መጣስ ከባድ ጥፋት እንደሆነም ገልጸዋል። ይህንን ተከትሎ ሊመጣ የሚችልን አደጋ ለመመከት አየር ኃይሉ የ24 ሰዓታት ዝግጁነት እንዳለው አመልክተዋል።
መሪዎቻችንና ዲፕሎማቶቻችን በዲፕሎማሲው መድረክ መልስ እንደሚሰጡ ሁሉ አየር ኃይሉ ደግሞ ፕሬዚዳንቱ ለጎሰሙት የጦርነት ነጋሪት አስፈላጊውንመልስና እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል ።
ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሌለው ላይ ቆጥቦ እየገነባው ያለው በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሻ የጠቆሙት አዛዡ ፣ አየር ኃይሉ በጠቅላላው የአገሪቷን መሰረተ ልማቶች የፖለቲካ ፣የኢኮኖሚ እና ወታደራዊ ማዕከሎችን በንቃት እንደሚጠብቅ አረጋግጠዋል።
አያይዘውም ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ፖለቲከኞች ሕገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ተወያይተው፣ተደራድረው፣ ምርጫ አካሂደው ወደስልጣን ሲመጡ ሰራዊቱ ይታዘዛል። ሆኖም ኢ- ሕገመንግስታዊ በሆነ መንገድ በግርግር ወደስልጣን እመጣለሁ ለሚለው አካል የሚታዘዝ ሰራዊት እንደሌለም አስታውቀዋል ።
መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት አለበት ብሎ ወስኖ ለ40 ዓመት በባእድ አገር ተሰደው የነበሩ፣ በአገር ውስጥም ያሉ በትጥቅ ትግል ላይም የነበሩትን ሁሉ ወደ አገራቸው እንዲገቡ አድርጓል ፤ ይህ ለእኔ በጣም ትልቅ ድል ነው ፤ ይህንን ደግም ሕዝቡም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊረዱት ይገባል ብለዋል።
አሁን እየታየ ያለው የዚህ ተቃራኒው ነው ያሉት ሜጀር ጀነራል ይልማ ፤ “ግርግር ለሌባ ያመቻል “ እንደሚባለው በዚህም በዛም መንግስትን ወጥረን ኢ - ሕገመንግስታዊ በሆነ መንገድ ስልጣን እንቀበላለን፤ ይህ ካልሆነ ደግሞ አገሪቷ ትፈርሳለች ማለትም እጅግ አስነዋሪ መሆኑን አመልክተዋል።
“እንደዚህ የሚሉ ሰዎች ያልገባቸው ነገር የኢትዮጵያ ሕዝብ በማይበጠስ ገመድ የተሳሳረ መሆኑ ነው። ማንም ተነስቶ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ስላለ የሚፈጠር ነገር የለም ፤ ሆኖም ግን እነዚህ አካላት ከእኩይ ተግባራቸው የማይመለሱ ከሆኑ ሰራዊት ምላሹ ይሰጣል” ብለዋል። ከዚህ አንጻር ሕዝቡ ፍጹም መረጋጋት እንዳለበትና እንደሚሉትም ሆነ እንደሚያስቡት የሚሆን ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል ።
“አሁን ላይ ሰራዊቱ ባልደረሰበት አካባቢ ግጭትን እየለኮሱ ብሔር ከብሔር ሃይማኖት ከሃይማኖት ሊያጋጩ ይችላሉ፤ ግን ደግሞ ይህ ሁኔታም በሂደት እየተስተካከለ ይሄዳል። ከዚህ በላይ አልፎ ለሚመጣ ደግሞ ጠንካራና ሕዝባዊ ሰራዊት አለን “ ብለዋል።

“ለሰላም በአንድነት መቆም ይገባል” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
***********************************
(ኢፕድ))
አዲስ አበባ፦ አንዱ አንዱን መግደል ሊቆም፤ መጠፋፋት ሳይሆን ለሰላም በአንድነት መቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ አሳሰቡ ።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በዛሬው እለት የሚከበረውን 1 ሺህ 495ኛው የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ፣ ነብዩ መሐመድ በምድር ቆይታቸው በጎ ነገሮችን ሰርተው ማለፋቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን መተዛዘን፣ አብሮ መብላት እና መረዳዳት እንጂ መገዳደል ባህላቸው እንዳልሆነም አመልክተው ፣ከዚህ አንጻርም አንዱ አንዱን መግደል ሊቆም፤ መጠፋፋት ሳይሆን ለሰላም በአንድነት መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል ።ለሀገር ሰላም የሚበጀው መጠፋፋት ሳይሆን መቀራረብና ይቅር መባባል መሆኑንም መክረዋል ። ጠላትን ለመመከት አንድ መሆን ፣ ለሃገሪቱ ልማት መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።
ማንም ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ የነብያችንን አደራ፣ አመራርና መልካም ፀባይ ሊከተል እንደሚገባውም አሳስበዋል።
በሀገሪቱ ላይ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና ሌሎችንም ፈተናዎች ለመሻገር የዜጎች አንድነት ወሣኝ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሰው ከኃጥያት እስካልተቆጠበ ድረስ ወደፊት ከአንበጣ በተጨማሪ ሌላ መከራ ሊመጣ እንደሚችል ያስጠነቀቁት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር፥ የእምነቱን አስተምህሮ በመከተል ከሙስና፣ ከሌብነትና በደል ራስን ማራቅ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በመግለጫቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት አውግዘዋል።የፕሬዚዳንቱ አስተያየት ተቀባይነት እንደሌለውም አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎዴ - ቀላፎ ፣ የጎዴ-ሐርጌሌ ሎት-1 እና የያአሌ-ደነን መንገዶችን ግንባታ ስራን ዛሬ በይፋ አስጀመሩ
*************************
(ኢፕድ)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጎዴ - ቀላፎ ፣ የጎዴ-ሐርጌሌ ሎት-1 እና የያአሌ-ደነን መንገዶችን ግንባታ ስራን ዛሬ በይፋ አስጀመሩ።
በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ በተካሄደው የመንገዶቹ ግንባታ ጅማሮ መርሃ ግብር ላይ የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ።፣የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ፣የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ፣ የብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱ አለም የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በድምሩ 277.6 ኪ. ሜ እርዝማኔ ያላቸው እነዚህ ሶስት የመንገድ ፕሮጀክቶችን በአስፋልት ደረጃ መገንባት ከሀገርም አልፎ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ቀጠናዊ የንግድ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ከማሳደግ አንጻር ፋዳቸው የጎላ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
በተለይም የሀገራችን ከፍተኛ ወጪ ገቢ ንግድ የሚስተናገድበት ጅቡቲ ወደብ ሆነ በኮሪደሩ ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ ጫና ከመቀነስ አኳያ ፕሮጀክቶቹ ሁነኛ አማራጭ ይሆናሉም ብለዋል ።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ለአመታት የዘለቀውን የክልሉን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ መንግስ እየሰራ ያለውን ስራ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ ከክልሉም አልፍ የሃገሪቱን የወጪ ገቢ ንግድን በማቀላጠፍ የጎላ ሚና አላቸው ብለዋል።
የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ 4.5 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚደረግባቸው የጎዴ - ቀላፎ ፣ የጎዴ-ሐርጌሌ ሎት-1 እና የያአሌ-ደነን መንገዶች ግንባታ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እና የጥራት ደረጃ ለማጠናቀቅ ከመንገድ ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ በመንገዶቹ ክልል ውስጥ ያሉ ንብረቶች በቶሎ ማንሳት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው።
የሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሮጀክቶቹ ካላቸው ኢኮኖሚያዊ እና መህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር የመንገድ ግንባታ ስራውን የሚያከናውኑት የስራ ተቋራጭ ድርጅቶች እና ጥራቱን የሚቆጣጠሩት አማካሪ ድርጅቶች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበው።
የባለስልጣኑ መ/ቤትም አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።በዛሬው እለት የመንገድ ግንባታ ስራቸው በይፋ የተጀመሩት የጎዴ - ቀላፎ ፣ የጎዴ-ሐርጌሌ ሎት-1 መንገዶች በጠጠር መንገድ ደረጃ ያሉ ሲሆን ሎላኛውና የመንገድ ግንባታ ስራው በዛሬው እለት የተጀመረው የያአሌ - ደነን መንገድ ከዚህ ቀደም ምንም አይንት የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበረው አካባቢ ሲሆን በቀጣይ ሁሉም መንገዶች ደረጃቻቸውን ከፍ በማድረግ በአስፋልት የሚገነቡ ይሆናል።
የጎዴ ቀላፎ መንገድ ፕሮጀክት 94.8 ኪ ሜ እርዝማኔ አለው ፡፡
መንገዱን ለመገንባት ጨረታውን በብር አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ ሚሊዮን ብር (1 ,530,000 ,000.00 ) አሸንፎ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር የውል ስምምነት የተፈራረመው ቻይና ሬል ዌይ ስቨን ግሩፕ ነው።
የምህንድስና እና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ እስታድያ ኢንጅነሪንግ ስራዎች ከጂ እና ዋይ አማካሪ ድርጅት ጋር በጋራ ያከናውኑታል ፡፡
የጎዴ - ሀርገሌ ሎት 1 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 100 ኪ .ሜ እርዝማኔ አለው ፡፡
ለአጠቃላይ ግንባታው መንግስት አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ሺ ሶስት መቶ ሰማኒያ ስድስት .ከሰባ አራት ሳንቲም 1,893,759,386.74 ወጪ መድቦለታል፡፡
መንገዱን ለመገንባት ጨረታውን አሸንፎ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር የውል ስምምነት የተፈራረመው አገር በቀሉ የሥራ ተቋራጭ ፋል ጀነራል ኮንትራክተር ነው፡፡
መንገዱ በውል ስምምነት መሰረት አራት ዓመት የግንባታ ግዜ ተሰጥቶታል፡፡
ሶስተኛው መንገድ ዮአሌ-ደናን ሎት 3 ሲሆን የፊቅ ሰገግ ገርቦ ደነን ፕሮጀክት አካል ነው፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ 82.84 ኪሜ ርዝመት አለው ።
መንገዱን በአስፋልት ደረጃ የሚገነባው የሥራ ተቋራጭ አገር በቀሉ ክሮስ ላንድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ነው፡፡
የኮንትራት ውሉ 1,119,417,453.44 አንድ ቢሊዮን አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ አስራ ሰባት ሺ አራት መቶ ሀምሳ ሶስት ከ አርባ አራት ሳንቲም ብር ነው ፡፡
የመንገዱ ስራ በ3 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል፡
ሳባ ኢንጂነሪንግ መንገዱን በማማከር እና በመቆጣጠር ተሳታፊ ይሆናል፡፡
የሶስቱ መንገድ ፕሮጀክቶች የጎን ስፋት በገጠራማው ክፍል 10 ሜትር ፣በቀበሌ 12 ሜትር ፣ በወረዳ 19 ሜትር እንዲሁም በዞን 21.5 ሜትር ነው፡፡
መንገዶቹ ሲጠናቀቁ ሁለተናዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳዎችን የሚያጎናፅፉ ናቸው።

አሜሪካ በቀጣይ በዓባይ ጉዳይ የአደራዳሪነት ሚና ሊኖራት እንደማይገባ ተገለፀ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የምትሰራው ግድብ የጋራ ፕሮጀክት ካለመሆኑም በላይ በሀገሪቷ ክልል ውስጥ የሚገኝና በሕዝቦቿ ገንዘብ የሚገነባ በመሆኑ ወደ ውይይት የመግባት ግዴታ እንዳልነበረባት ተጠቆመ ።
የጂኦግራፊ ምሁር እንዲሁም በውሃ ፖለቲካና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉት አቶ ብርሃኑ በላቸው ፤ከሰሞኑ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓባይ ግድብን አስመልክተው የተናገሩት ያልተገባ ንግግር ፍፁም ስህተት ነው ብለዋል። አሜሪካ በቀጣይ በዓባይ ጉዳይ ላይ የአደራዳሪነት ሚና ሊኖራት እንደማይገባ አመልክተዋል ።
“አንዴ ሌባ ካሉት ቢቆርብም አያምኑት” ነው ተረቱ ያሉት አቶ ብርሃኑ፤ ከዚህ በኋላ አሜሪካንን ማመን አስቸጋሪ እንደሚሆን ተናግረዋል። አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ እያሳደረች ያለው ተፅዕኖ የቅኝ ገዥዎች መንፈስ የሚንጸባረቅበት እንደሆነም አስታውቀዋል ።
አካሄዱ በዚሁ ከቀጠለ ለቅኝ ግዛት የማይንበረከኩ ኢትዮጵያውያን እንዲህ አድርገናል የሚል ኃይል ይፈጠራል። ከዚህም ባለፈ ይህ አካሄድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አደጋ ሊሆን እንደሚችል አመልክተው ፣ እና ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ ሀገራት መጥፎ አርአያ እንዳንሆን መጠንቀቅ እንደሚገባን አመልክተዋል።
ከጅምሩ አሜሪካ በዓባይ ጉዳይ ላይ ሶስተኛ ወገን ሆና መግባት አልነበረበትም ያሉት አቶ ብርሃኑ፤ በየደረጃው ያሉ ሰዎች ድርድር እያደረጉ ባሉበት ወቅት የአሜሪካ መንግስት በታዛቢነት እንዲገባ መፈቀዱ የመጀመሪያው ስህተት እንደነበር አስታውሰዋል። ታዛቢ ሆና የተሰየመችው አሜሪካ ማደራደር መጀመሯም ሌላው ስህተት ነበር ። ከማደራደር አልፋም ውሳኔ ሰጪ ስትሆን ማስቆም እንደሚገባ አስታውቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=40679

www.press.et
አሜሪካ በቀጣይ በዓባይ ጉዳይ የአደራዳሪነት ሚና ሊኖራት እንደማይገባ ተገለፀ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት