Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️

የርዕደ መሬት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነታችንና የምላሽ ሁኔታችን ባለን ቴክኖሎጂ፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ ትንተናና የትንበያ አቅም የሚወሰን ነው፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ባደረግነው ጉብኝት በርዕደ መሬት ነክ ሳይንሳዊ ምርምር አበረታች ስራዎችን አይተናል።

ባለፈው ሳምንት ባካሄድነው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በርዕደ መሬት ክስተት ዙሪያ ባስቀመጥነው አቅጣጫ መሰረት ወደ ተጠናከረ ተግባር ተገብቷል፡፡

አደጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የመሠረተ-ልማት፣ የጊዜያዊ መጠለያ፣ የሰብአዊ ድጋፍ፣ የሳይንሳዊ ትንተና እና ትንበያ ቡድኖችን በማደራጀት በዕቅድ ላይ የተመሰረተ ሥራ እየተከናወነ ነው።

መንግሥት የአጭርና የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት የጥናትና ምርምር ተቋማት ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂና ብቁ የሰው ኃይል ጠንካራ ቁመና እንዲፈጥሩ ድጋፍ ያደርጋል።

ጥር 8 ቀን 2017 ዓም
👍4😁1
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ ማሳሰቢያ

በካናዳ የሥራና ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት ህጋዊ ውክልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ የተሰጣቸው በማስመሰል ህገ ወጥ ደብዳቤ አዘጋጅተው እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን ተገንዝበናል።

የሚኒስትሩ ስም ተጠቅሶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያ አውታሮች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እንዲህ አይነት የወንጀል ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ጋር እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።
👍114
ዳያስፖራው ለሀገሩ ልማትና እድገት የበኩሉን ሚና ለመወጣት ዝግጁ ነው - ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላ
*

(ኢ ፕ ድ)

ዳያስፖራው በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ላለው እድገትና ልማት የበኩሉን ሚና ለማበርከት ዝግጁ መሆን እንዳለበት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ገለፁ።

ፕሬዝዳንቱ በኒውዮርክ እና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያውያኑ በታደሰው ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ባደረጉት ጉብኝት እያንዳንዱ የቤተ መንግሥቱ የሕንጻ ክፍል የኢትዮጵያን አስደናቂ ታሪክ በጥልቀትና በስፋት እንደሚመሰክር በኤክስ ገጻቸው ገልጸዋል።

ጥር 8 ቀን 2017 ዓም
👍2
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ማምሻውን የጥምቀት በዓልን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ተወያይተናል።

የጥምቀት በዓል የተለመደውን ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ ከሃይማኖቱ አባቶች ጋር የተወያየን ሲሆን ሁላችንም በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱንና የቱሪስት መስህብነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ተባብረን በጋራ እንስራ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
👍14😱1
#ለከተራና_ለጥምቀት በዓል

ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓም ድረስ ጃንሜዳና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

👉 ከ6 ኪሎ አደባባይ - ምኒልክ ሆስፒታል

👉 ከምኒልክ ሆስፒታል - መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ

👉 ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ - 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ

👉 ከዋልያ ቢራ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል

👉 ከአቃቂ ዋናው መንገድ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል

👉 ከ08 - አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ይሆናሉ።
👍1
"የሠላም አማራጮችን በመቀበል ለሚመጡ የመንግስት የሰላም በር ዛሬም ክፍት ነው" - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር )
******
(ኢ ፕ ድ)

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፣ መንግስት ባለፉት አመታት ሠላም ለማስጠበቅ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች ውጤት ተመዝግቦባቸዋል።

በቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ እንዲሁም በአፋርና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የተገኙት ውጤቶች ማህበረሠቡ ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴው እንዲገባ አስችሏል።

በቅርቡም በኦሮሚያ ክልል በትጥቅ ትግል ውስጥ የነበሩ ወደሠላማዊ እንቅስቃሴ አየተመለሱ ናቸው።

በአማራ ክልልም በሺዎች የሚቆጠሩ የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ስልጠና ወስደው ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ የገቡ ሲሆን። ሌሎችም በሺዎች የሚቆጠሩ በአሁኑ ወቅት በስልጠና ለይ ይገኛሉ። አብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢዎችም ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል።

በመንግስት በኩል እነዚህ ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን ዛሬም የሠላም አማራጮችን በመቀበል ለሚመጡ የመንግስት በር ዛሬም ክፍት ነው ብለዋል ።

በተጨማሪም በኢኮኖሚውም ዘርፍ የብር ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሠን መደረጉ ኢመደበኛና የኮንትሮባንድ ንግድና አጠቃለይ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ወደህጋዊ መስመር እንዲገቡ አስችሏል።

ብሔራዊ ባንክ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ከፍተኛ ወርቅ ለመቀበልም ችሏል። የተፈጠረው ሠላምና እየተከናወኑ ያሉ የከተማ ልማት ስራዎችም የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በነዳጅ አቅርቦት ረገድ የሚታዩ ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን ለማስቆምም የተጀመሩ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።

በራስወርቅ ሙሉጌታ

ጥር 9 ቀን 2017 ዓም
👍31
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢራን ሪፐብሊክ መንግስት ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ከሚመራው ልዑካን ቡድን ጋር በብሔራዊ ቤተ-መንግስት በፎቶ‼️
3👍3
#ጎንደር #ጥምቀት

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለጥምቀት ክብረ በዓል ጎንደር ገቡ

አዲስ አበባ ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉና የጎንደር ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኜው እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ጥር 10 ቀን 2017 ዓም
👍41