Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በጎንደር የጥምቀት በዓል የሚከበርበት ስፍራ የእድሳት ስራ መጠናቀቁን የከተማው ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ
****
(ኢ ፕ ድ)

በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል የሚከበርበት የፋሲለደስ መጠመቂያ ስፍራ የእድሳት ስራ ተጠናቆ ለበዓሉ ዝግጁ መደረጉን የከተማው ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ተወካይ ኃላፊ አቶ ልዕልና አበበ እንደገለጹት፤ የጥምቀተ ባሕሩን የውኃ ስርገት ለመከላከል የሚያስችል የጥገና ስራ መከናወኑንና አሁን ላይም ከ10 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ የመሙላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በጥምቀተ ባሕሩ መንበረ ታቦታቱ የሚያርፉባቸው ስፍራዎችን የማጽዳትና ለምዕመናኑ ምቹ የማድረግ ስራዎች በአብዛኛው መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በበዓሉ የሚታደሙ የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎችን ጨምሮ ለታላላቅ እንግዶች የሚውሉ የማረፊያ ስፍራዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መንገድ ዝግጁ መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

እስከ 400 እንግዶችን ማስተናገድ የሚያስችሉ የብረት አግዳሚ ወንበሮች ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ተሰርተው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውንም አመልክተዋል፡፡

ክብረ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ለሀገር ውስጥና ለመላው ዓለም ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ጊዜያዊ የቴሌቪዠን ማሰራጫ ስቱዲዮዎች የሚተከሉባቸው ስፍራዎች መደራጀታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ጊዜያዊ መፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ የኤሌክትሪክ፣የውኃና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን የማሟላት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው፤ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና መስጫ ቦታዎችም ተዘጋጅተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዘንድሮ በከተማው በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶችን ጨምሮ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👍4👏1
#ጎንደር_የፋሲል ቤተመንግስት ዕድሳት‼️

የፋሲለደስ ዕድሳት እጅግ ውብ፣ የከተማዋን ታሪካዊነት በሚያጎላና የቱሪስት መዳረሻነቷን በሚያሳድግ ሁኔታ በመሰራት ላይ ይገኛል። የፋሲለደስ የዕድሳት ስራ አሁናዊ ገፅታ‼️

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👏4👍3
የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ (UNFSS+4) በአዲስ አበባ ይካሄዳል
****
(ኢ ፕ ድ)

በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) የዘላቂ ልማት ግቦች ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፋኖስ ፎቲዩ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ከሐምሌ 21 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ መደረግ ስላለበት የቅድመ ዝግጅት ስራ፤ ለጉባዔው ዝግጅት የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተዋል።

የዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ የረጅም ጊዜ ፈተናዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ፋኦ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ጉባዔውን እንደሚያዘጋጅ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👍6👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ጎንደር ጎንደርን መስላ አየኋት" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍3😁1
በምዕራብ ጎንደር ዞን 23 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ጥጥ እየተሰበሰበ መሆኑ ተገለፀ
****
(ኢ ፕ ድ)

በምዕራብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት 23 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ጥጥ በጥራት እየተሰበሰበ መሆኑ ተገለጸ።

በዞኑ ግብርና መምሪያ  የሰብል ልማትና ጥበቃ ባለሙያ አቶ ደግሰው አየለ ፤ እየተሰበሰበ ያለው የጥጥ ምርት  በጥራት ተሰናድቶ ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት እንደሚቀርብ ለኢዜአ ተናግረዋል።

በመኸሩ ወቅት በጥጥ ከለማው አጠቃላይ መሬት ውስጥ 12 ሺህ 300 ሄክታር የሚጠጋው በባለሃብቶች፤ ቀሪው ደግሞ በአርሶ አደሮች የለማ መሆኑን  አስረድተዋል።

የምርት አሰባሰቡ ሂደት  እስከ ተያዘው  ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዶ ርብርብ እየተደረገ  መሆኑን አመልክተው፤ አጠቃላይ  ከለማው መሬት ከ422 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከተገነቡ የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካዎች እና የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ጥጡ የሚቀርብ መሆኑን ገልጸዋል።

በመኽር ወቅቱ 4 ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ  የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ የተናገሩት ደግሞ በመተማ ወረዳ ኮኪት ቀበሌ  አርሶ አደር ቢሰጥ አየናቸው ናቸው።

ባለፉት ዓመታት በጥጥ ምርት ላይ የገበያ ችግር እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ግን ጥጥን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋታቸው ተፈላጊነቱ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

በዚሁ ወረዳው የደለሎ ፋና ቀበሌ  አርሶ አደር ደሴ አሻግሬ፤ በመኽር ወቅት በጥጥ ከሸፈኑት 3 ሄክታር መሬት ውስጥ 1 ሄክታር የሚሆነውን መሰብሰባቸውን ገልጸዋል።

ካለሙት መሬት ከ50 ኩንታል በላይ የጥጥ ምርት እንደሚጠብቁ ጠቅሰው፤ከምርት ሽያጭም የተሻለ ጥቅም አገኛለሁ ብለዋል።

ጥር 8 ቀን 2017 ዓም
👍8
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
2
በፈታኝ ሁኔታዎች አመርቂ የዲኘሎማሲ ስኬቶች ተመዝግበዋል - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

👉 በተለያዩ ሃገራት በችግር ውስጥ የነበሩ 33ሺህ ዜጎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል፣

👉 ለ968 የአጎራባች ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የከፍተኛ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷል፣
*****
(ኢ ፕ ድ)

ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩት የውጭ ግንኙነት ስራዎች በፈታኝ ሁኔታዎች አመርቂ ስኬቶች መመዝገባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሰታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ ባለፉት ስድስት ወራት በውጭ ግንኙነት የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎችን እና ወቅታዊ የዲኘሎማሲ እንቅስቃሴዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማራመድ ተጨባጭ ውጤቶችን ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትስስር የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው በቀጣናው ሰላም ማስከበር ያላት ሚና እውቅና እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል።

ከሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር ያስቻሉ ከ128 በላይ የከፍተኛ ባለስልጣናት ጉብኝቶች መደረጋቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅሞችና ወቅታዊ አቋሞች ለማስረፅ ያስቻሉ እንደሆኑም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት ሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ ባለፉት ስድሰት ወራት ከነበሩ ስኬቶች አንዱ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ነብያት፤ ይህም በባለብዙ ወገን ዲኘሎማሲ መስክ የኢትዮጵያን ሚና ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

ከተለያዩ ሃገራት ጋር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር በርካታ ስራዎች መሰራታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለ968 የአጎራባች ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የከፍተኛ የትምህርት ዕድል መስጠቷንም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በተለያዩ ሃገራት በችግር ውስጥ የነበሩ 28 ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ ታቅዶ 33ሺህ ዜጎችን መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ጥር 8 ቀን 2017 ዓም
2👍2👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የጎንደር_ከተማ_አዲሱ_ዕይታ

"አረጀች እያሉ ሰዎቹ ሲያሙሽ፤ ሙሽራ ነሽ ጎንደር ይሰፋል ልብስሽ"

#PMOEthiopia
👍6😁2
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et