Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት

ዛሬ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር የጎንደር የኮሪደር ልማትና የፋሲለደስ ግንብ እድሳት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተናል።

የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራና የፋሲለደስ እድሳት እጅግ ውብ፣ የከተማዋን ታሪካዊነት ይበልጥ በሚያጎላና የቱሪስት መዳረሻነቷን በሚያሳድግ ሁኔታ በመሰራት ላይ ነዉ።

በዚህ የለውጥ ዘመን የኢትዮጵያ ከተሞች የተሰጣቸው ትኩረት እጅግ ትልቅ ሲሆን፣ በተለይም ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ውብ እንዲሁም ለቱሪስት መስህብ መሆናቸውን እጅግ የሚጨምር ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👏6👍53😁1
በጎንደር የጥምቀት በዓል የሚከበርበት ስፍራ የእድሳት ስራ መጠናቀቁን የከተማው ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ
****
(ኢ ፕ ድ)

በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል የሚከበርበት የፋሲለደስ መጠመቂያ ስፍራ የእድሳት ስራ ተጠናቆ ለበዓሉ ዝግጁ መደረጉን የከተማው ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ተወካይ ኃላፊ አቶ ልዕልና አበበ እንደገለጹት፤ የጥምቀተ ባሕሩን የውኃ ስርገት ለመከላከል የሚያስችል የጥገና ስራ መከናወኑንና አሁን ላይም ከ10 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ የመሙላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በጥምቀተ ባሕሩ መንበረ ታቦታቱ የሚያርፉባቸው ስፍራዎችን የማጽዳትና ለምዕመናኑ ምቹ የማድረግ ስራዎች በአብዛኛው መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በበዓሉ የሚታደሙ የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎችን ጨምሮ ለታላላቅ እንግዶች የሚውሉ የማረፊያ ስፍራዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መንገድ ዝግጁ መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

እስከ 400 እንግዶችን ማስተናገድ የሚያስችሉ የብረት አግዳሚ ወንበሮች ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ተሰርተው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውንም አመልክተዋል፡፡

ክብረ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ለሀገር ውስጥና ለመላው ዓለም ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ጊዜያዊ የቴሌቪዠን ማሰራጫ ስቱዲዮዎች የሚተከሉባቸው ስፍራዎች መደራጀታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ጊዜያዊ መፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ የኤሌክትሪክ፣የውኃና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን የማሟላት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው፤ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና መስጫ ቦታዎችም ተዘጋጅተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዘንድሮ በከተማው በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶችን ጨምሮ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👍4👏1
#ጎንደር_የፋሲል ቤተመንግስት ዕድሳት‼️

የፋሲለደስ ዕድሳት እጅግ ውብ፣ የከተማዋን ታሪካዊነት በሚያጎላና የቱሪስት መዳረሻነቷን በሚያሳድግ ሁኔታ በመሰራት ላይ ይገኛል። የፋሲለደስ የዕድሳት ስራ አሁናዊ ገፅታ‼️

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👏4👍3
የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ (UNFSS+4) በአዲስ አበባ ይካሄዳል
****
(ኢ ፕ ድ)

በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) የዘላቂ ልማት ግቦች ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፋኖስ ፎቲዩ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ከሐምሌ 21 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ መደረግ ስላለበት የቅድመ ዝግጅት ስራ፤ ለጉባዔው ዝግጅት የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተዋል።

የዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ የረጅም ጊዜ ፈተናዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ፋኦ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ጉባዔውን እንደሚያዘጋጅ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👍6👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ጎንደር ጎንደርን መስላ አየኋት" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍3😁1