Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ድጋፍ አደረገ
******************
(ኢፕድ)
ጽህፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ፤ በጤናው ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሷል።

በዛሬው ዕለትም ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተለያዩ መድሀኒቶችን ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል፡፡
👍91👎1
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን አስተላለፈ
***********************
(ኢፕድ)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 41ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የ53 ነጥብ 3 ሚሊየን ኤስ.ዲ.አር እና ለፋይናንስ ዘርፍ ማጠንከሪያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የ525 ነጥብ 7 ሚሊየን ኤስ.ዲ.አር የፋይናንስ ድጋፍ እና ብድር ስምምነቶችን ለማጽደቅ በቀረቡ 2 ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡

ሁለቱም ብድሮች ከወለድ ነጻ፣ 0 ነጥብ 75 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልባቸው ሆኖ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍለው የሚጠናቀቁ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ ብድሮቹ ከሀገራችን የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ መሆኑን በማረጋገጥ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ቀጥሎም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብን ለማሻሻል በወጣ ደንብ ላይ ነው፡፡

የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517/2014 ተግባራዊ እየተደረገ ቢሆንም ደንቡ ከመውጣቱ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ በተለያዬ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች የአፈጻጸም ችግር እያጋጠማቸው ነው።

በመሆኑም የደንቡ ድንጋጌዎች ግልጽ እንዲሆኑ ለማድረግ የቀረበው ማሻሻያ ደንብ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደርን ለማፍረስ የቀረበ ረቂቅ ደንብ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ነው፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የፕራይቬታይዜሽን ስራዎች ወደ ዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ተላልፈው እንዲከናወኑ ለማስቻል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደርን በሕግ አፍርሶ መብቶቹንና ግዴታዎቹን ለኮርፖሬሽኑ ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
👍105👎1
ዶክተር ሳምሶን መኮንን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
**********************************
(ኢፕድ)
6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት በእጩነት ያቀረቧቸው ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ሹመትን አጽድቋል፡፡

ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኮሚኒኬሽን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ሹመቱን ምክር ቤቱም በውሳኔ ቁጥር 5/2017 በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
በማህሌት ብዙነህ
👍71
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የበጋ ስንዴ እርሻ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን አስታወቁ
*****************************
(ኢፕድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የበጋ ስንዴ እርሻችን በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
👍15👎3🔥1
ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ የ2025 የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመረጠች
****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው አሲያ ኽሊፋ የ2025 ሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመረጠች።

አሲያ አለምአቀፍ አምባሳደር ሆና መመረጧ ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መሰል ተሳትፎ ትልቅ ምዕራፍ ሲሆን ዲጂታል ቴክኖሎጂንና ፈጠራን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል። በሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር 2024 ፕሮግራም ስኬታማ ተሳትፎ በማድረጓ ነው ተብሏል።

እ.ኤ.አ. በ2025 በቻይና በሚካሄደው የአይሲቲ ታለንት ዲጂታል ጉብኝት እንድትሳተፍና የተግባር ልምድ እንድታገኝ፣ በሌሎች ትልልቅ አለም አቀፍ ዝግጅቶች ላይ ተገኝታ የቴክኖሎጂ ተግባራዊ እውቀት እንድትካፈል እድል ይሰጣታል።

ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር በዓለም ዙሪያ ያሉ ወጣት ተማሪዎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን አረዳዳቸውን ማሳደግ ነው።

የባህል ልውውጦች አስፈላጊነትና የስራ ፈጣሪነትን ማዳበር ላይም ትኩረት ያደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች መካከልም ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት ሴቶች በማድረግ የተለያዩ ልዩነቶችን ለማስተናገድና ለማካተት ቁርጠኛ ሆኖ ይሰራል።

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👍6👏62
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳትና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ነው። በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ በተለይ በክብር ለተሞሉት እንግዳ ተቀባይ የጎንደር ነዋሪዎች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለመግለጽ እወዳለሁ።

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👍12🤣31👏1
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

በሀሰተኛ የጉዞ ሰነድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ከ13 ሺህ በላይ ዜጎች ላይ አሰተዳደራዊ ርምጃ ተወስዷል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ፣ ተቋሙ ባለፋት ስድስት ወራት 10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከ16 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል።

በሐሰተኛና በተጭበረበሩ የጉዞ ሰነዶች አገልግሎት ለማግኘት ሲቀሳቀሱ የነበሩት 13 ሺህ 322 ዜጎች ላይ አስተዳድራዊ ርምጃዎችን ተወስዷል ሲሉ ገልጸዋል።

ከ721 ሺህ 623 በላይ ፓስፖርቶችን የማተም ስራ ተሰርቷል። ከታተመው 98 በመቶው ለተገልጋዮች ተሰጥቷል።

ለ14 ሺህ 367 ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የመስጠት ስራ ተከናውኗል። በዚህም ለ20 ግለሰቦች ዜግነት ተሰጧቸዋል ሲሉ አብራርተዋል።

ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሠው ሀይሉን የማጠናከር፤ አሰራሩን በቴክኖሎጂ የማገዝ ስራ ይሰራል።

በታደሠ ብናልፈው

ጥር 7 ቀን 2017 ዓም
👍9😁52👎1