Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ዩጋንዳ ገቡ
******************
(ኢፕድ)
ፕሬዝደንቱ ዩጋንዳ የገቡት በአፍሪካ አስተማማኝ የግብርናና የምግብ ስርዓት መገንባት በሚል መሪ ሃሳብ በድህረ ማላቦ አጠቃላይ የአፍሪካ ግብርና ልማት ፕሮገራም አፈጻጸም ላይ የሚመክር የአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባኤ ለመካፈል ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ታዬ በኢንተቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
👍8
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
*************
ለኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል።

ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅም እና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይዎን ያፍሱ።
7👍5😱1
አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቱሪስቶች ክልሉን ጎብኝተዋል
*****************************
(ኢፕድ)
በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች የአማራ ክልል መጎብኘታቸውን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

በዚህም ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ቢሮው ጨምሮ ገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አባይ መንግስቴ ለጋዜጣ ፕላስ እንዳስታወቁት፤ ባለፉት ስድስት ወራት አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቱሪስቶች የክልሉን የተለያዩ ቦታዎች ጉብኝተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ጎብኚዎች አራት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ነው ያሉት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ በክልሉ የቱሪስት የቆይታ ጊዜ የሚያራዝሙና የታቀደውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ በርካታ ምቹ ሁኔታዎች አሉ ብለዋል፡፡

የልደት በዓልን ጨምሮ በቀጣይ በክልሉ በጥር ወር የሚከበሩ ሐይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ይበልጥ እንደሚያሳድግ አብራርተዋል፡፡

ልጅዓለም ፍቅሬ
👍18🤣65😱3
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍52🥰1
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ድጋፍ አደረገ
******************
(ኢፕድ)
ጽህፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ፤ በጤናው ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሷል።

በዛሬው ዕለትም ጉድ ኔበርስ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተለያዩ መድሀኒቶችን ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል፡፡
👍91👎1
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን አስተላለፈ
***********************
(ኢፕድ)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 41ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የ53 ነጥብ 3 ሚሊየን ኤስ.ዲ.አር እና ለፋይናንስ ዘርፍ ማጠንከሪያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የ525 ነጥብ 7 ሚሊየን ኤስ.ዲ.አር የፋይናንስ ድጋፍ እና ብድር ስምምነቶችን ለማጽደቅ በቀረቡ 2 ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡

ሁለቱም ብድሮች ከወለድ ነጻ፣ 0 ነጥብ 75 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልባቸው ሆኖ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍለው የሚጠናቀቁ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ ብድሮቹ ከሀገራችን የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ መሆኑን በማረጋገጥ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ቀጥሎም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብን ለማሻሻል በወጣ ደንብ ላይ ነው፡፡

የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517/2014 ተግባራዊ እየተደረገ ቢሆንም ደንቡ ከመውጣቱ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ በተለያዬ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች የአፈጻጸም ችግር እያጋጠማቸው ነው።

በመሆኑም የደንቡ ድንጋጌዎች ግልጽ እንዲሆኑ ለማድረግ የቀረበው ማሻሻያ ደንብ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደርን ለማፍረስ የቀረበ ረቂቅ ደንብ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ ነው፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የፕራይቬታይዜሽን ስራዎች ወደ ዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ተላልፈው እንዲከናወኑ ለማስቻል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደርን በሕግ አፍርሶ መብቶቹንና ግዴታዎቹን ለኮርፖሬሽኑ ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
👍105👎1
ዶክተር ሳምሶን መኮንን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
**********************************
(ኢፕድ)
6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት በእጩነት ያቀረቧቸው ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ሹመትን አጽድቋል፡፡

ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኮሚኒኬሽን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ሹመቱን ምክር ቤቱም በውሳኔ ቁጥር 5/2017 በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
በማህሌት ብዙነህ
👍71
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የበጋ ስንዴ እርሻ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን አስታወቁ
*****************************
(ኢፕድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የበጋ ስንዴ እርሻችን በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
👍15👎3🔥1