Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቻይናዋ ጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ ጋር ተወያዩ
***************
(ኢፕድ)
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች ቤቤ ከቻይናዋ ጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ሹ ኩንሊን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አስተውቀዋል።

ከንቲባው ጉብኝቱን ያደረጉት ሚስተር ሹ ኩንሊን የጂያንግሱ ግዛትን እንዲጎበኙ በቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በጉብኝታችን ወቅት ከጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ እና አመራሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ጠቅሰው፤ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፎች ላይ ግንኙነታችንን ለማጠናከር መግባባት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም በትብብር ለመስራት ተግባብተናል ብለዋል።

ከንቲባዋ፣ በጂያንግሱ ግዛት በነበራቸው ቆይታ ሚስተር ሹ ኩንሊን ላደረጉላቸው መስተንግዶ አመሥግነዋል፡፡
👍24
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት የገና ስጦታ አበርክተዋል።
👏1910👍6👎5
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍10👏5
የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ተመረቀ
************
(ኢፕድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀን 30 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለውን የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቱ መርቀው ከፈቱ፡፡

ከንቲባ አዳነች እንደገለጹት፤ የዚህ ፕሮጀክት መመረቅ የከተማችንን የፍሳሽ ማጣራት አቅም ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት በቀን 48 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ወደ በቀን 233 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ከፍ ማድረግ አስችሎናል::

ማጣሪያ ጣቢያው ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማጣሪያ ስርዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ ፕሮጀክቱ ከለዉጡ ወዲህ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምሮ የመጨረስ አንዱ ማሳያ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

ለአንድ ከተማ ወሳኝ ከሆኑ መሰረተ ልማቶች መካከል የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓትን ማዘመን ትልቅ ስራ ነው ያሉት ክቲባ አዳነች፣ ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ከመፍጠር አኳያ ያለው ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ይህ የፍሳሽ ማጣሪያ ስራ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓታችንን የሚያዘምን፣ የከተማችን ነዋሪዎችን እና በአጎራባች አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎት የረዥም ጊዜ ቅሬታን ምላሽ የሚሰጥ ፣ከተማችንን ከብክለት የጸዳች፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ እዉን የሚያደርግ ነዉ ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች፤ ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጉት የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኮንትራክተርና አማካሪ ድርጅት፣ ለክፍለከተማውና ከምንም በላይ በፈቃደኝነት ለልማት ከቦታው ለተነሱ አርሶ አደሮች በነዋሪው እና በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል፡፡
👍7👎1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍51
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ሳቢያ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ
***********************
(ኢፕድ)
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ግዛት በሎስ አንጀለስ አካባቢ በደረሰው ከባድ ሰደድ እሳት ሳቢያ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው የሀዘን መግለጫ፤ በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ግዛት በሎስ አንጀለስ አካባቢ በደረሰው ከባድ ሰደድ እሳት የሰው ህይወት በመጥፋቱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው በመፈናቀላቸው እና ንብረት በመውደሙ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት በሎስ አንጀለስ አካባቢ ለሚኖሩ የአሜሪካ ህዝብና መንግስት እንዲሁም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
👍8🤣5