Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ አራት ሺህ 700 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት እየተሠራ ነው
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በሐረሪ ክልል ከአራት ሺህ 700 ሄክታር መሬት በላይ በበጋ መስኖ ለማልማት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ በሄክታር ከ42 እስከ 45 ኩንታል ምርት መስጠት የሚችል አዲስ የማሽላ ዝርያ በማልማት 36ሺ ኩንታል መሰብሰቡን ተጠቁሟል፡፡

የሐረሪ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እና የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ዑመር ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በክልሉ የበጋ መስኖ ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

ዘንድሮም ከአራት ሺህ 700 ሄክታር መሬት በላይ በበጋ መስኖ ለማልማት እየተሠራ ይገኛል።

በክልሉ በዓመት ሁለትና ሦስት ጊዜ የሚመረትበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመው፤ አርሶ አደሩ የመኸሩን ምርቱን ሰብስቦ በማጠናቀቁ በበጋ መስኖ ለማልማት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኘ ገልጸዋል፡፡

በክልልሉ በ2016/17 የምርት ዘመን 11 ሺህ 774 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ሙሉ ለሙሉ መልማቱን ጠቅሰው፣ ከዚህም ውስጥ 800 ሄክታሩ መሬትም በማሽላ፤ 450 ሄክታሩ በስንዴ በክላስተር እርሻ ኢንሼቲቭ እንዲለማ መደረጉን አስታውቀዋል።

በክልሉ በኩታ ገጠም (በክላስተር) ዘዴ የለማው የማሽላ ዝርያ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምርምር ያገኘው መሆኑን አውስተው...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=143848
2👍2😁1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍1
የግብርና ምርምር – ለዘርፍ አስተማማኝ እድገት
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
የግብርናው ዘርፍ የአስር ዓመት መሪ እቅድ ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ በምርምር የሚገኙ ውጤቶችን ተግባራዊ ማድረግን ከተቀዳሚ ዓላማዎቹ መካከል አድርጓል።

መሪ እቅዱ የምርምር ውጤቶች የአርሶና አርብቶ አደሩን ገቢ የሚያሳድጉ፣ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሊሆኑ እንደሚገባም ያስቀምጣል።

በገበያ ተፈላጊ የጥራት ደረጃን ለማሟላት እንዲችሉ ተስማሚ የቴክኖሎጂና ሳይንሳዊ የአሰራር ዘዴ አማራጮችን ማቅረብ ይፈልጋል፡፡

ብሎም በተጠቃሚው ዘንድ ተቀባይነት ኖሯቸው በአግባቡ ተተግብረው ተጠባቂውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ ይጠበቃል። በጥቅሉ ሀገሪቷ የግብርና ዘርፍ አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው እድገት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ…..

https://press.et/?p=143831
1👍1😱1
የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ በመወሰኑ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተጠቃሚ እየሆኑ ነው
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
መንግሥት ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ተከትሎ በተለይ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ምንዛሪ ግብይት በገበያ ዋጋ እንዲወሰን በመደረጉ የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ተጠቃሚ መሆኑን ገለጸ።

ዩኒየኑም በበጀት ዓመቱ ባለፉት ወራት አንድ ሺህ 730 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ 10 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱ ተጠቁሟል።

የዩኒየኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ዳዲ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ኅብረት ሥራ ማህበራት በሕጋዊ መንገድ ምርታቸውን ለውጭ ገበያ አቅርበው የሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ በባንኮች ወቅታዊ የምንዛሪ ዋጋ በሕገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያው ከሚመነዘረው በእጥፍ ባነሰ……….
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=143829
👍9😁1
"ዛሬ ጠዋት እየተከናዋኑ ባሉ ጥረቶች ላይ ለመወያየት የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጀምረናል"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍10👎21
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍51🔥1
የሰሜን ወሎ ዞን የጸጥታ ሁኔታ መሻሻሉ ለተረጂዎች ድጋፍ ለማድረስ እንዳስቻለ ተገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የሰሜን ወሎ ዞን የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱ ለቡግና ወረዳ እና ለአካባቢው ተረጂዎች የአልሚ ምግብ፣ የጤና አገልግሎት እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስን ተደራሽ ለማድረግ እያስቻለ መሆኑን የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ገለጸ።

ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችለውም ኮሚሽኑ ወደ እርሻ ሥራዎች መግባቱን አስታውቋል።

በአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፍቅሬ ሙሉጌታ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የሰሜን ወሎ ዞን የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱ በቡግና ወረዳና አካባቢው የአልሚ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸው በችግር ውስጥ ለነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ለማድረግ አስችሏል።

ቡግና ወረዳ በሰቆጣ ዲክላሬሽን ስር ታቅፈው የአልሚ ምግብ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ወረዳዎች አንዱ መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ ፍቅሬ፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች አልሚ ምግቦችን ማድረስ ባለመቻሉ....

https://press.et/?p=143920
👍175😁1
“ሁሉም ወገን አማራጭ ለማይገኝለትና አትራፊ ለሆነው ሠላም እጁን መዘርጋት አለበት”
– አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) የቀድሞው የሕወሓት ታጋይና የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር
*******
(ኢ ፕ ድ)

የቅርቡም ሆነ የሩቁ ታሪክ እንደሚያሳየው ችግሮችን በጦር መሣሪያ ለመፍታት መነሳት ኪሳራ እንጂ ትርፍ ስለሌለው ሁሉም አማራጭ ለማይገኝለት ሠላም እጁን መዘርጋት እንዳለበት የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ እና የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የቀድሞ የሕወሓት ታጋይና የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ እስከ አሁን ድረስ ብዙ ጠመንጃ ተመዟል፤ ብዙ ጦርነት ተካሂዷል፡፡ ብዙ ሕዝብ አልቋል፤ ብዙ ንብረት ወድሟል፡፡ በልማት ላይ መዋል ይችል የነበረ ብዙ ሀብት ተቃጥሎ በኖ ቀርቷል። ይህ የሚያሳየው ጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለውም። በዚህ መነሻነትም ምንም አማራጭ ለማይገኝለትና አትራፊ ለሆነው ሠላም እጁን መዘርጋት አለበት፡፡

ጦርነት መግደል ወይም መሞት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለሀገርም ሆነ ለሕዝብ ኪሳራ ነው፡፡ በጦር መሣሪያ የሚፈታ ችግር ስለሌለ ሠላምን መፈለግ ይሻላል ብለዋል። ይህንን ያሉት ከቅርብ ከራሳቸው ተሞክሮ መሆኑን የተናገሩት አረጋዊ (ዶ/ር) ፤ መሣሪያ ይዞ መዋጋት ያለ እልቂት ያመጣው ምንም ፋይዳ እንደሌለው.....https://press.et/?p=143962
👍133🔥1🙏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍7👎21👏1