Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ፀደቀ
********
(ኢ ፕ ድ)
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባው የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ከመረመረ በኃላ በሙሉ የምክር ቤት አባላት ተወያይተው ነው አዋጁን ያደቁት፡፡

የምክር ቤቱ አባላት የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1361/ 17 መሬት መራቆት እንዳይኖር፣ የደንሽፋን እንዲስፋፋ የአዋጁ መውጣት ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚመደብ ፈንድን በስፋት አግኝቶ ለመጠቀም ከፍተረኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡

ለትግበራው ከመንግስት በጀት እንዲመደብ የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ደኖችን ለመንከባከብና ለማልማት የሚጠቅም ነው ሲሉም የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ 54 ሚዮን ሄክታር የተጎዳ መሬት መኖሩን የጠቆሙት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጅ፤ ከዚህ ውስጥ 11 ሚሊዮን ሄክታሩ ፈጣን ምላሽ የሚፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለትግበራው በቋሚነት እና በተቀናጀ አግባብ የፌደራል መንግስት የበጀት ድጋፍ የሚያደርግበት እንዲሆን፣ ክልሎችም የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ማድረግ በሚያስችል መልኩ እንዲደግገፉ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ በደን ዘርፍ ከልማት አጋሮችና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ሰጪ ምንጮች እና ከካርበን ግብይት ስርዓቶች የምታገኘውን ድጋፍና ጥቅም ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በዘላለም ግዛው
ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓም
4👍4👎1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍6🔥1
ለአካባቢው አርሶ አደሮች እፎይታን የሰጠው የሰላም ስምምነት
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በአካባቢያቸው ሰላም ባለመኖሩ ምክንያት አርሶና ምርትን አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ ይቅርና ወጥቶ መግባት ፈታኝ ነበር ፡፡

ይህም እንደምንም ለራስ ከመሆን ባለፈ ለሌሎች መትረፍ ሳይቻል ቆይቷል ይላሉ የሆሮጉ ዱሩ ወለጋ ዞን ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ አየለች በቀለ፡፡

በአካባቢው በነበረው ግጭት ምክንያት ሰዎች ወጥተው መግባት፣ አርሶ ማምረት ፈተና ሆኖ መቆየቱን የሚናገሩት ወይዘሮዋ፤ ወጥቶ የመቅረት ክስተቶችም እንደሚያጋጥሙ አውስተዋል፡፡

“ዛሬ ምን ይፈጠር ይሆን?” በሚል ስጋት ውስጥ ከወደቅን ዓመታት ተቆጥረዋል የሚሉት ወይዘሮ አየለች፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት ለአካባቢው ነዋሪዎች የሰላም እፎይታን...

https://press.et/?p=143618
👍5👏1😁1
#ኢትዮጵያና #ሶማሊያ

✍️ኢትዮጵያ ለአንካራው ስምምነት ተግባራዊነት ቁርጠኝኛ ናት፣

✍️ ሶማሊያ የአንካራው ስምምነት በተፋጠነ ሁኔታ እንዲተገበር ትሻለች፣

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋና የሶማሊያ ውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዲኤታ አሊ መሃመድ ኦማር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ሀገራቱ ተባብሮ መስራት፣ ችግሮች ሲጋጥሙም ተቀራርቦ መፍትሄ መሻት ይገባቸዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለአንካራው ስምምነት ተግባራዊ መሆን ቁርጠኛ ናት ያሉት አምባሳደር ምስጋኑ የሁለቱ ሃገራት ትብብር ማደግ ለቀጠናው ሰላምና እድገት ወሳኝ እንደሆነም አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እንደከፈለች አምባሳደር ምስጋኑ አስታውሰዋል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዲኤታ አሊ መሃመድ ኦማር በበኩላቸው ሶማሊያ የአንካራው ስምምነት በተፋጠነ ሁኔታ እንዲተገበር ትሻለች ሲሉ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ መገኘታቸውም ለስምምነቱ ተፈፃሚነት ሀገራቸው ያላትን ዝግጁነት ጠቅሰው ለጋራ እድገት የሶማሊያ መንግሰት ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።

በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ተቀራርበው እንደሚሰሩ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓም
👍153
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፈረንጆቹ የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
***
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላው ዓለም የፈረንጆችን የገና በዓል ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ፣ ለኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል። በዓሉ የሰላምና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓም
😁41👍1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
6🔥1
የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ምሥረታን ለማፋጠን
****************
(ኢ ፕ ድ)
የናይል ወንዝ የትብብር ማሕቀፍ ስምምነት ወደተፈጻሚነት ከገባ ሁለት ወር ሞልቶታል። ማሕቀፉ ሕግ ሆኖ መጽደቁ ኢትዮጵያን ጨምሮ በወንዙ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም ዙሪያ ጥያቄ ላላቸው የተፋሰሱ ሀገራት ታሪካዊ ድል እንደሆነ ይታመናል።

ግብጽና ሱዳን መጀመሪያ ላይ ድርድሩ ውስጥ የገቡት በቅኝ ግዛት የደለደሉትን ውሃ እውቅና እናሰጣለን በሚል ነበር። እንደተጀመረም አካባቢ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት እነርሱን የመደገፍ አዝማሚያ ያሳዩ ስለነበር የተሳካላቸው መስሏቸው ነበር።

በኋላ ላይ ግን የእነዚያ ሀገራት መሠረታዊ ፍላጎታቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ ያሰቡት ሳይሳካ ቀርቷል።

ሰባቱም የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት በኢትዮጵያ እየተመሩ ግብጽና ሱዳን ደግሞ አንድ ላይ ሆነው ድርድሩ ወደመቋጨቱ ሲቃረብ፤ ግብጽና ሱዳን ያቀዱት ስላልተሳካላቸው ስምምነቱን.......
https://press.et/?p=143687
👍6
የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ይካሄዳል - አቶ አደም ፋራህ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

በአንደኛው ታሪካዊ የብልጽግና ፓርቲ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎችን በመፈጸም በኩል አበረታች ሥራዎች መፈጸማቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል።

ባለፈው የፓርቲው ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ፣ በአሰባሳቢ ትርክት ማዳበር፣ በሰላም እና ደህንነት እና በመሰል ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመፈጸም ፓርቲው ለሕዝብ የገባቸውን ቃሎች በማክበር እና በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በኢኮኖሚው የሃገር በቅል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በተመተግበር ተጨባጭ ለውጥ የታየባቸው ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን ጠቅሰዋል።

የአቅም መገንባት ስራዎች መሰራታቸውን አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የማበረታቻ እና የእርምት እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ጠንካራ የፌደራል ስርዓት እንዲፈጠር መሰራቱን ጠቅሰዋል።
የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት አንጻርም አበረታች ሥራዎች መሰራታቸውን እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀርበው የሚነጋገሩበት ምህዳር መፈጠሩን አንስተዋል።

በሂደቱ ያጋጠሙ ከሰላም ከጽንፈኝነት ጋር የተያያዙ እና መሰል ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን በመቋቋም ሥኬቶች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል።

ለጉባኤው ዝግጅትም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን የፓርቲው መረጃ ያመለክታል።

ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓም
👍4👎4😁3
በኮሪደር ልማት የተሰሩ መንገዶች የትራንሰፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ የትራፊክ አደጋን መከከላከል አሰችሏል
******
(ኢ ፕ ድ)

በከተማዋ የተሰራው የመንገድ ኮሪደር ልማት የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥና አደጋን ከመከከላከል አንጻር መሰረታዊ ለውጥ ያመጣ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ በትራፊክ አደጋ ባለፉት ሶስት ወራት 107 ሰዎች ህይወትም አልፏል። ከ900 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያና የህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ በከተማዋ የነበሩ መንገዶች በይዘትም በጥራም ከተማዋን የማይመጥኑ ብሎም ለእግረኛ ሆነ ለተሸከርካሪ ምቹ አልነበሩም።

አሁን እየተሰሩ ያሉና የተሰሩ የመንገድ ኮሪደሮች የእግረኛና ተሸከርካሪ መንገድ የለዩ፣ ተሸከርካሪ ፕርኪንግ ቦታዎችን ያስቀመጡና የብስክሌት መንገዶችን ያካተቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህም ከከተማው ገጽታ ግንባታ ባሻገር የመንገድ ትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥና አደጋን ከመከከላከል አንጻር መሰርታዊ ለውጥ ያመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህም የመንገድ ኮሪደሩ በተጠናቀቀበት በአራዳ ክፍለከተማ በተለይም ፒያሣ አካባቢ በጥቅምትና ህዳር ወር ምንም አይነት የሞት አደጋ አለመሰከቱና ጤናማ የትራፊክ ፍሰት መኖሩ ለለውጡ አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በከተማዋ የትራፊት አደጋ በ2017 በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ ከዘጠኝ መቶ በላይ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ያደረሰ ብሎም የአንድ መቶ ሰባት ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ መሆኑን ጠቅሰው፤ የትሪፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጠጠር የወጡ ህጎችን አክብሮ በሀላፊነት በመንቀሳቀስ እራስን ከአደጋ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በማህሌት ብዙነህ

ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓም
👍6🥰1👏1😁1🤔1