የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️
ዛሬ ማለዳ 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ከፍ ባለ ሁኔታ ለማስተናገድ የመዲናችንን ቅድመ ዝግጅት ገምግመናል።
የአፍሪካዊያንና የዓለም የዲፕሎማቲክ ማዕከል፤ የህብረብሄዊነት አርማ የሆነችዉ ከተማችን አዲስ አበባ ይህንን ታሪካዊ ጉባኤ በደመቀ እና ባማረ መልኩ ለማስተናገድ ከወትሮ በተሻለ መልኩ እንግዶቿን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናት።
የከተማችን ነዋሪዎችም እንግዶችን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና እንገዳ ተቀባይነት ለመቀበል፣ በየአካባቢዉ ከወዲሁ ከተማችንን ውብ እና ፅዱ በማድረግ እንዲሁም በእንኳን ደህና መጣችሁልን መንፈስ ሃላፊነታችንን በመወጣት የሃገራችንን ስም እና ክብር ከፍ ለማድረግ ተባብረን እንስራ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

👍3❤1👎1
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
❤1🔥1
በሶማሌ ክልል በበጋ መስኖ ከ16 ሚልየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠብቃል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በሶማሌ ክልል በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት ከ16 ሚልየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ አህመድኑር አብዲ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ ለበጋ መስኖ ልማት ትኩረት በመስጠት በዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት ከ16 ሚልዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመግኘት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል።
በክልሉ የመስኖ ልማት በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋት አርብቶ አደር የነበረውን የአካባቢውን ማኀበረሰብ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት በመቀየር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በመስኖ ሊለማ የሚችል ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት መኖሩን አመላክተዋል፡፡
በሌላ በኩል በክልሉ በመኸር ወቅት ዝናብ የሚያገኙ ዞኖች ሁለት ብቻ ናቸው። በእነዚህ ሁለት ዞኖች በምርት ዘመኑ 246 ሺህ ሄክታር መሬት በማረስ 4 ሚሊዮን 900 ሺህ ኩንታል ምርት ተሰብስቧል ብለዋል።
በክብረአብ በለቸው
ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓም

👍7❤2
የተዘነጉ ቅርሶችንና ወረቶችን- ሀብት ወደ ማፍራት ያሸጋገረ አዲስ ዕይታ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የሀገር በቀል ኢኮኖሚው ማሻሻያ ምሰሶ ናቸው ተብለው ከተለዩት አንዱ ቱሪዝም ነው። የቱሪዝም ኢንዱስትሪው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የቱሪስት መዳረሻዎችን የማስፋት፣ ቅርሶችን የመጠገንና የማደስ፣ ከተሞችን የማዘመን፣ ታሪካዊ ቦታዎችን ለቱሪስቶች ክፍት በማድረግ ወረትን ወደ ሀብት የመቀየር ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን የቅርስ ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ ይልማ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፤ ማንኛውም ሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገቱን የሚያስቀጥለው ባለው ሀብት ላይ ተመስርቶ ነው፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቅርስ ሀብት ያላት ሀገር ነች፤ ይህን ከፍተኛ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ቢቻል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይቻላል።
ለዘመናት ጥቅም መስጠት ሲገባቸው ከጎብኚዎች እይታ ተሰውረው የቆዩ ቅርሶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች አሉ። ቱሪዝም በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ሚና እንዲወጣ ሲታሰብ እነዚህን ሀብቶች ጥቅም ላይ ማዋል የግድ ይላል። ከቅርሶቹ ሀገር ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝ መደረጉም ተገቢነት......https://press.et/?p=143553

👍10🔥3
ኢትዮጵያና ጅቡቲ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን ለመግታት የጋራ ግብረ-ኃይል ለማቋቋም ተስማሙ
********
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የጅቡቲ ሪፐብሊክ የሴኪዩሪቲ ዶክመንቴሽን ሰርቪስ በሁለቱ ሀገራት ድንበሮች አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን ለመግታት ከሚያደርጉት የመረጃ ልውውጥ ባሻገር የጋራ ግብረኃይል አቋቁመው ስምሪት ለማከናወንና ወንጀለኞችንም አሳልፎ ለመስጠት መስማማታቸውን ገለፁ።
በጅቡቲ ሪፐብሊክ የሴኪዩሪቲ ዶክመንቴሽን ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ሐሰን ሰይድ ካይራ የተመራ የልዑክ ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በጅቡቲ ሪፐብሊክ የሴኪዩሪቲ ዶክመንቴሽን ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ሐሰን ሰይድ ካይራ ከተመራው የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በጸጥታ፣ በደኅንነትና በተያያዥ መስኮች ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚረዳ ምክክር ማድረጋቸውን መረጃው ገልጿል፡፡
የሁለቱን ሀገራት የጋራ ስጋቶች መመከት የሚያስችሉ እንዲሁም ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማምጣት የሚረዱ ጉዳዮች ዋንኛ የምክክሩ አጀንዳዎች እንደነበሩ የጠቆመው የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ፤ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተለይም ሕገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት፤ ሕገ-ወጥ ስደተኞችንም ለመከላከል የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውን አመልክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ በኩል የምታከናውነው የወጪ ገቢ ንግድ ላይ የሚስተዋሉ የደኅንነት ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ውይይት መካሄዱንም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡

👍8
አዋሽ ወልደያ መቀሌ የባቡር መንገድ ግንባታ ፕሮጄክትን ለማጠናቀቅ ፋይናንስ የማፈላለግ ሥራ ይከናወናል
******
(ኢ ፕ ድ)
አዋሽ ወልደያ ሀራ ገበያና ሀራገበያ መቀሌ የባቡር መንገድን ግንባታን ለማጠናቀቅ ፋይናንስ የማፈላለግ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ግዛው (ኢ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፣ አዋሽ ወልደያ፣ ሀራገበያና ከሀራገበያ መቀሌ የባቡር መንገድ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ ፋይናንስ የማፈላለግ ሥራ እየተሰራ ይገኛል።
አዋሽ ወልደያ ሀራ ገበያ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት 99 በመቶ ደርሶ እንደነበር ጠቅሰው፣ በሰሜኑ ጦርነት በመሰረተ ልማቶች ላይ በደረሰ አደጋ ሳቢያ ወደ ኋላ መመለሱን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የሰላም ሁኔታው እየተረጋጋ በመሆኑ የወደቡ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመስራትና የባቡር መንገዶቹን ለማጠናቀቅ የፋይናንስ አማራጮች እየተፈለጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በማርቆስ በላይ
ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...

👍8👏3😁1
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ስብሰባ ጀምረናል።
ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

❤8👍2
ኢትዮጵያ የአንካራውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ቁርጠኛ ነች- አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የአንካራውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እልባት ለመስጠት በተርክዬ አሸማጋይነት ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የአንካራውን ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐመድ ፈርመውታል።
የአንካራውን ስምምነት በማፅናት በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር የተመራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።
የሶማሊያ የልዑካን ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተመራ ልዑክ ጋር ውይይት አድርጓል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እንዳሉት፤ የሶማሊያ ልዑክ የስራ ጉብኝት ከአንካራው ስምምነት በኋላ የመጀመሪያው ነው።
የአንካራውን ስምምነት ገቢራዊ በማድረግ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።
የሶማሊያ ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም መሆኑን ገልጸው፥ ሽብርተኝነትን በመከላከል በቀጣናው ሰላም ለማስፈን ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
የሶማሊያ የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር ከወንድሜ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ከአንካራው ስምምነት በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝታቸው መሆኑን ገልጸው፥ ስምምነቱን ገቢራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ተናግርዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

👍6❤3