Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ክብር ዘብ አሰላለልፍና ምልከታ በብሔራዊ ቤተመንግስት‼️

#PMOEthiopia
👍124
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ዛሬ ማለዳ 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ከፍ ባለ ሁኔታ ለማስተናገድ የመዲናችንን ቅድመ ዝግጅት ገምግመናል።

የአፍሪካዊያንና የዓለም የዲፕሎማቲክ ማዕከል፤ የህብረብሄዊነት አርማ የሆነችዉ ከተማችን አዲስ አበባ ይህንን ታሪካዊ ጉባኤ በደመቀ እና ባማረ መልኩ ለማስተናገድ ከወትሮ በተሻለ መልኩ እንግዶቿን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናት።

የከተማችን ነዋሪዎችም እንግዶችን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና እንገዳ ተቀባይነት ለመቀበል፣ በየአካባቢዉ ከወዲሁ ከተማችንን ውብ እና ፅዱ በማድረግ እንዲሁም በእንኳን ደህና መጣችሁልን መንፈስ ሃላፊነታችንን በመወጣት የሃገራችንን ስም እና ክብር ከፍ ለማድረግ ተባብረን እንስራ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
👍31👎1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
1🔥1
በሶማሌ ክልል በበጋ መስኖ ከ16 ሚልየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠብቃል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በሶማሌ ክልል በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት ከ16 ሚልየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ አህመድኑር አብዲ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ ለበጋ መስኖ ልማት ትኩረት በመስጠት በዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት ከ16 ሚልዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመግኘት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል።

በክልሉ የመስኖ ልማት በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋት አርብቶ አደር የነበረውን የአካባቢውን ማኀበረሰብ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት በመቀየር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በመስኖ ሊለማ የሚችል ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት መኖሩን አመላክተዋል፡፡

በሌላ በኩል በክልሉ በመኸር ወቅት ዝናብ የሚያገኙ ዞኖች ሁለት ብቻ ናቸው። በእነዚህ ሁለት ዞኖች በምርት ዘመኑ 246 ሺህ ሄክታር መሬት በማረስ 4 ሚሊዮን 900 ሺህ ኩንታል ምርት ተሰብስቧል ብለዋል።

በክብረአብ በለቸው
ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓም
👍72
የተዘነጉ ቅርሶችንና ወረቶችን- ሀብት ወደ ማፍራት ያሸጋገረ አዲስ ዕይታ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የሀገር በቀል ኢኮኖሚው ማሻሻያ ምሰሶ ናቸው ተብለው ከተለዩት አንዱ ቱሪዝም ነው። የቱሪዝም ኢንዱስትሪው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የቱሪስት መዳረሻዎችን የማስፋት፣ ቅርሶችን የመጠገንና የማደስ፣ ከተሞችን የማዘመን፣ ታሪካዊ ቦታዎችን ለቱሪስቶች ክፍት በማድረግ ወረትን ወደ ሀብት የመቀየር ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን የቅርስ ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ ይልማ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፤ ማንኛውም ሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገቱን የሚያስቀጥለው ባለው ሀብት ላይ ተመስርቶ ነው፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቅርስ ሀብት ያላት ሀገር ነች፤ ይህን ከፍተኛ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ቢቻል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይቻላል።

ለዘመናት ጥቅም መስጠት ሲገባቸው ከጎብኚዎች እይታ ተሰውረው የቆዩ ቅርሶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች አሉ። ቱሪዝም በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ሚና እንዲወጣ ሲታሰብ እነዚህን ሀብቶች ጥቅም ላይ ማዋል የግድ ይላል። ከቅርሶቹ ሀገር ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝ መደረጉም ተገቢነት......https://press.et/?p=143553
👍10🔥3