የኢትዮጵያና የፈረንሳይ ዘርፈብዙ ግንኙነቶች‼️
✍️ ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ አምስተኛዋ የወጪ ንግድ መዳረሻ ሀገር ናት፣
✍️ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ጋር በሁለተኛ ደረጃ የንግድ ልውውጥ ታደርጋለች፣
✍️ እአአ በ2019 በሐምሌ ወር ከማርሴ - አዲስ አበባ አዲስ የጉዞ መስመር ተጀምሯል፣
✍️ ፈረንሳይ ለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዕድሳት ድጋፍ አድርጋለች፣
✍️ ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት በፈረንሳይ ይደገፋል፣
✍️ በወታደራዊ ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ጋር የሁለትዮሽ ትብብር አላት፤ የመከላከያ ትብብር ስምምነት ተፈርሟል፣
✍️ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን የባህር ኃይል መልሶ ለመገንባት ድጋፍ ታደርጋለች፣
ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓም

❤20👍7👎2😁2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ወንድሜና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፉት ስድስት አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ።
በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል። ክቡር ፕሬዚዳንት በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ፅኑ ነው።

👍21👏5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ያደረጉት አቀባበል‼️
❤10
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በነበረን የሁለትዮሽ ውይይት ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።
ክቡር ፕሬዚዳንትና የፈረንሳይ መንግሥት በብሔራዊ ቤተመንግስትና በመካሄድ ላይ ባለው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ሥራዎች ላደረጉት አስተዋፅዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ።
በውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች የሚኖሩ ትብብሮችን የፈተሽን ሲሆን የፈረንሳይን ኢንቨስትመንት መጨመርን ብሎም በትምህርትና ባሕል ዘርፎች ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል።
ታሪካዊ ትስስራችንን ይበልጥ የመገንባትን አስፈላጊነትንም በውይይታችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ።
#EthiopiaFrance

👍15❤3😁3
የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ወዳጅነት ምዕተ ዓመታትን የተሻገረ ነው
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
***
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያና ፈረንሳይ ወዳጅነት በጠንካራ የልማት ትብብር ምዕተ ዓመታትን ተሻግሯል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በኢትዮጵያ የተገኘውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ትብብር ከሚያደርጉልን ወዳጅ ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት ብለዋል፡፡
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣትም ይህ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንድ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የፈረንሳይ መንግስት በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያን እና በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት እድሳት ላደረገልን ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ በመምጣቶ ክብር ይሰማናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አዲሲቷን ኢትዮጵያን እንደ አዲስ ስለጎበኟትም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓም

👍5
"በኢትዮጵያና ፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት በትላልቅ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ የተመሰረተ ነው"
- የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን
******
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያና ፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት በታሪክ ሂደትና በትላልቅ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ገለጹ።
የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ፕሮጀክትንም ሰርተን ዛሬ የሚያኮራ እውነታ ሆኖ እየታየ ነውም ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ማክሮን በኤክስ ገጻቸው በአማርኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ለሰው ልጅ መገኛነት የመጀመሪያ አሻራ ያላት ሀገር ናት ብለዋል።
በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት በታሪክ ሂደትና በትላልቅ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ የተመሰረተ ነው።
እ.ኤ.አ በ2019 መሰረታዊ የሆኑ የባህልና የቅርስ ጥበቃን ከሳይንሳዊ ፕሮግራም ጋራ አያይዘን ለመስራት ወስነን ተነስተናል ያሉት ማክሮን፤ በላሊበላም የሰራነው በዓለም ላይ ልዩ የሆነ የቅርስ ጥበቃ ፕሮጀክት በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ፍጻሜውን የሚያገኝ ይሆናል።
ወደፊትም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዘመንን ለመደገፍ እና በትግራይ የሰላምና የመረጋጋት መሰረት የሆነውን የፕሪቶሪያ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ትብብር እናደርጋለን ብለዋል።
የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር @AbiyAhmedAli የወደፊቷ የኢትዮጵያ ተስፋ የብልጽግናና የሰላም እንደሚሆን ፈረንሳይ እምነቷ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

👍11❤1