Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=143413
መልካም ቀን!
👏21👎1
“ግብጽን የሚያዋጣት ሕግ የሆነውን የናይል ትብብር ማሕቀፍ ስምምነት ፈርሞ መቀበል ነው”
- ተባባሪ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ (ዶ/ር) የታሪክ ምሁር
****
(ኢ ፕ ድ)

በአሁኑ ወቅት ግብጽን የሚያዋጣት ከወራት በፊት ተፈርሞ ሕግ የሆነውን የናይል ትብብር ማሕቀፍ ስምምነትን ፈርሞ መቀበል እንደሆነ የታሪክ ምሁር ተባባሪ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ኢትዮጵያ 130 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ይዛ ያለ ባሕር በር መኖር የማይታሰብ ነገር እንደሆነም አመልክተዋል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ አብላጫዎቹ የተፋሰሱ ሀገራት የናይል ትብብር ማሕቀፍ ስምምነትን መቀበላቸውን በፊርማቸው ከማረጋገጥም ባሻገር የሀገራቸው ሕግ አድርገው አጽድቀውታል።

የትብብር ማሕቀፍ ስምምነት በስድስት የተፋሰሱ ሀገሮች በመጽደቁም ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ሕግ መሆኑን ያስታወሱት የታሪክ ምሁሩ ፤ ለግብጽም መልካም የሚሆነው ማሕቀፉን ተቀብላ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብራ ብትሠራ እንደሆነ አመልክተዋል። ተባብራ መሥራቷም የበለጠ ተጠቃሚ ያደርጋታል ብለዋል ።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ በኢትዮጵያ በኩል ዋናው ቁም ነገር በአቋም መጽናት ነው። የትብብር ማሕቀፉ ሥራ ላይ እንዲውል በማድረጉ በኩል አሁን የመጣችበት መንገድ መልካም የሚባል ነው፤ ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል ተገቢ ነው።

በኢትዮጵያ ጉዳይ አርፋ መቀመጥን የማትወደዋ ግብጽ፣ እንዲሁ ከመድከም ባለፈ ምንም ማድረግ አልቻለችም ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ፣ የትብብር ማሕቀፉን ፈርማ በማጽደቅ ተጠቃሚ........https://press.et/?p=143416
👍12
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የሀገራቱን ግንኙነት ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል
*****
(ኢ ፕ ድ )
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሀገራቱን ግንኙነት ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያና ፈረንሳይ በዲፕሎማሲ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በባህልና በሌሎች ዘርፎች 126 ዓመታትን ያስቆጠረ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ለኢፕድ ገልጸዋል፡፡

የፈረንሳይ መንግስት በተለያዩ ምክንያቶች የተዘረፉ የአፍሪካ ቅርሶችን በመመለስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ጥገና ድጋፍ እያደረገ ሲሆን፤ ይህም ለሌሎች ሀገራት ትምህርት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን አጠናክረው ለማስቀጠል የተለያዩ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የሀገራቱን ግንኙነት ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያልም ብለዋል፡፡

በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ደረጃ ያሉ መሪዎች ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሀገሪቱ ተሰሚነት ማደጉን የሚያሳይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የሀገሪቱን ገጽታ ለመግባት እንዲሁም ሁለቱ ሀገራት በተለያየ ዘርፍ ያለቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እገዛ እንዳለው አስታውቀዋል፡፡

ፈረንሳይ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ከሚደግፉ ሀገራት አንዷ መሆኗንም አንስተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እአአ 2019 በመጋቢት ወር በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሀገራቱን ሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክሯል።

በሄለን ወንድምነው

ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓም
👍162👎1
ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት‼️
3👍1
የኢትዮጵያና የፈረንሳይ ዘርፈብዙ ግንኙነቶች‼️

✍️ ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ አምስተኛዋ የወጪ ንግድ መዳረሻ ሀገር ናት፣

✍️ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ጋር በሁለተኛ ደረጃ የንግድ ልውውጥ ታደርጋለች፣

✍️ እአአ በ2019 በሐምሌ ወር ከማርሴ - አዲስ አበባ አዲስ የጉዞ መስመር ተጀምሯል፣

✍️ ፈረንሳይ ለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዕድሳት ድጋፍ አድርጋለች፣

✍️ ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት በፈረንሳይ ይደገፋል፣

✍️ በወታደራዊ ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ጋር የሁለትዮሽ ትብብር አላት፤ የመከላከያ ትብብር ስምምነት ተፈርሟል፣

✍️ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን የባህር ኃይል መልሶ ለመገንባት ድጋፍ ታደርጋለች፣

ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓም
20👍7👎2😁2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ወንድሜና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፉት ስድስት አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ።

በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል። ክቡር ፕሬዚዳንት በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ፅኑ ነው።

ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓም
👍21👏5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ያደረጉት አቀባበል‼️
10
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በነበረን የሁለትዮሽ ውይይት ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።

ክቡር ፕሬዚዳንትና የፈረንሳይ መንግሥት በብሔራዊ ቤተመንግስትና በመካሄድ ላይ ባለው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ሥራዎች ላደረጉት አስተዋፅዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ።

በውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች የሚኖሩ ትብብሮችን የፈተሽን ሲሆን የፈረንሳይን ኢንቨስትመንት መጨመርን ብሎም በትምህርትና ባሕል ዘርፎች ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል።

ታሪካዊ ትስስራችንን ይበልጥ የመገንባትን አስፈላጊነትንም በውይይታችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ።

#EthiopiaFrance
👍153😁3
የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ወዳጅነት ምዕተ ዓመታትን የተሻገረ ነው
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነ
*
**
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያና ፈረንሳይ ወዳጅነት በጠንካራ የልማት ትብብር ምዕተ ዓመታትን ተሻግሯል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በኢትዮጵያ የተገኘውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ትብብር ከሚያደርጉልን ወዳጅ ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት ብለዋል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣትም ይህ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንድ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፈረንሳይ መንግስት በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያን እና በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት እድሳት ላደረገልን ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ በመምጣቶ ክብር ይሰማናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አዲሲቷን ኢትዮጵያን እንደ አዲስ ስለጎበኟትም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓም
👍5