Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ህዝባዊ_የድጋፍ_ሰልፍ_በአማራ_ክልል

በአማራ ክልል በላሊበላ፤ በደባርቅ፣ በደብረታቦር፣ በደብረ ማርቆስ ኮምቦልቻ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ ከተማና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ጦርነት ይብቃ ሰላም ይስፈን፤ ሰላምን እንፈልጋለን፣ግጭትና ጦርነት ይብቃ በማለት ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄ ይገኛል።

በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በሰልፈኞች የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል፤

👉መንግሥት ሰላም ለማስከበር የሚሠራውን ሥራ እንደግፋለን

👉 መንግስት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን

👉 ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን

👉 መንግስት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን

👉 ንፁሀንን በግፍ እየገደሉ በአስከሬናቸው መነገድ አረመኔያዊነት ነው

👉 ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላም እና ልማት ነው

👉 ፅንፈኛና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወጥተው የሰላምን አማራጭ ሊከተሉ ይገባል

👉 ሰላም የጋራ ሀብት ነው፤ በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል

👉 መንግስት ህግ በማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል

👉 ፅንፈኛው ሀይል በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ግድያ፣ ማገትና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል

👉 መከላከያ ሰራዊታችን፣ የፌዴራልና የክልላችን የፀጥታ ሀይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን

ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓም
👍21👎2🍌21
እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=143273
መልካም ቀን!
👍3
‹‹መንግሥት የሽግግር ፍትሕን ለማስፈን በቁርጠኝነት እየሠራ ነው´ – ኤርሚያስ የማነ ብርሃን (ዶ/ር) የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ
************************
(ኢ ፕ ድ)
በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ችግሮችን ለማከም የሚያስችል የሽግግር ፍትሕን ለማስፈን መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነ ብርሃን (ዶክተር) አስታወቁ።

የፍትሕ ዘርፉን ዘመናዊ፤ ቀልጣፋ እና የሕዝብ አመኔታን ያተረፈ እንዲሆን የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አመለከቱ።

ሚኒስቴር ዴኤታው ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ፣ የቀጠሉ፣ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የሚያስችል የሽግግር ፍትሕ ለማስፈን የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።

በእውነት፣ በእርቅ፣ በምሕረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ …

https://press.et/?p=143290
👍6🤣3
አየር መንገዱ ወደ እሥራኤል የሚያደርገው በረራ የሀገራቱን የጠበቀ ግንኙነት የሚያሳይ እንደሆነ ተገለጸ
*************************************
(ኢ ፕ ድ )
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሁኔታዎች ሳይገደብ ወደ እሥራኤል የሚያደርገው በረራ የሁለቱን ሀገራት የጠበቀ ግንኙነት የሚያሳይ መሆኑን የእሥራኤል ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሸረን ሜሬየም ኸስኬል ገለጹ።

ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሸረን ሜሬየም ኸስኬል ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ በርካታ አየር መንገዶች ወደ እሥራኤል የሚያደርጉትን በረራ ባቋረጡበት ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እሥራኤል የሚያደርገውን በረራ ባለማቋረጡ አመስግነዋል።

አየር መንገድ በሁኔታዎች ሳይገደብ ወደ እሥራኤል የሚያደርገው በረራ የሀገራቱን የጠበቀ ግንኙነትና ለጋራ ጥቅም አብሮ መሥራትን ያሳየ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያና እሥራኤልን ለረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት፣ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር እና የሚጋሯቸው ሃይማኖታዊ እሴቶች አሏቸው ያሉት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ይህም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የጠበቀ እንዲሆን ማስቻሉን ገልጸዋል።

በእሥራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዲቪዥን ቢሮ ኃላፊ ኖአ ፉርማን በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ወደ እሥራኤል የሚያደርገውን በረራ ለማስቀጠል ያሳየውን…

https://press.et/?p=143289
8👍3👎1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍61
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

በቅርብ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜይክ ጋር በልዩ ልዩ የትብብር መስኮች ዙሪያ በሚኖረን የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ተወያይተናል።

በትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ በተመሰረተው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲሁም የፈረንሳይ መንግስት በከተማችን በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ዙሪያ ስለሚያደርገው ድጋፍ ከአምባሳደር ላሜይክ ጋር የተወያየን ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች ጋር ያላትን የጠበቀ ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያም ተነጋግረናል፡፡

ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
👍11👎3🔥2
የምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት ‼️

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ የብረት ኢንዱስትሪ መንደር የሚገኘውን ስቲሊ አር. ኤም. አይ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር (STEELY RMI P.L.C) የብረታብረት ማምረቻ ፋብሪካን ጎብኝተናል።

ፋብሪካው ዘመናዊ የዲጂታል አሠራርን እና የታዳሽ ኃይልን በመጠቀም ከዚህ ቀደም ይጣሉ የነበሩ የብረት ቁርጥራጮችን መልሶ ጥቅም ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡ በዚህም ለተለያዩ የግንባታ ግብዓት የሚውሉ የብረታብረት ምርቶችን እያመረተ መሆኑ የሚደነቅ ነው።

የብረታብረት ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ረገድ አበረታች ውጤቶች እያመጣ እንዳለም ተመልክተናል፡፡

መንግሥት የብድር፣ የመሠረተ ልማትና የአሠራር ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የግሉ ዘርፍ ለኢኮኖሚ ዕድገቱ ዋና አንቀሳቃሽ (ሞተር) እንዲሆን የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።

ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
👍117👎4
እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=143341
መልካም ቀን!
👍8
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3
በኦሮሚያ ክልል ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል የአቮካዶ ምርት ተሰበሰበ
**********************
(ኢ ፕ ድ )
በ2017 የምርት ዘመን ሰባት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እስካሁን ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል የአቮካዶ ምርት መሰብሰቡን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ። በክልሉ 165 ሺህ 321 አርሶ አደሮች በአቮካዶ ልማት መሠማራታቸው ተጠቁሟል፡፡

በቢሮው የፍራፍሬ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተገኝ ኢራና ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በክልሉ የአቮካዶ ማሳ ሽፋን 55 ሺህ 112 ሄክታር መሬት የደረሰ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 30 ሺህ 145 ሄክታር የሚሆነው መሬት ላይ የተተከለው የአቮካዶ ዛፍ ምርት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ባለፈው ዓመት ስድስት ነጥብ አምስት ኩንታል የአቮካዶ ምርት ማግኘት መቻሉን አውስተው፤ በዘንድሮው የምርት ዘመን ሰባት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁንም ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል የአቮካዶ ምርት መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በ21 ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 185 ወረዳዎች በአንድ ሺህ 751 ክላስተር በማደራጀት አቮካዶ መተከሉን የገለጹት አቶ ተገኝ፤ 165 ሺህ 321 ወንድና ሴት አርሶ አደሮች በአቮካዶ ማልማት ሥራ ተሠማርተው….

https://press.et/?p=143334
👍5👏2