Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጎነት መኖሪያ መንደርን ጎበኙ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የበጎነት መኖሪያ መንደን ዛሬ ጎብኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች በመኖሪያ መንደሩ በመገንባት ላይ ያሉ ተጨማሪ ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች ግንባታ ያለበትን ደረጃ  ተመልክተዋል።

በመንደሩ እስከ አሁን ሰባት የመኖሪያ ህንጻዎች ተጠናቅቀው ለልማት ተነሺዎች እና የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መተላለፋቸውን አመልክተዋል።

በመኖሪያ መንደሩ ለሚገኙ ነዋሪዎች የእንጀራ ፋብሪካን ጨምሮ ልዩ ልዩ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸውም ገልጸዋል።

በከተማ አስተዳደሩ እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ትብብር እየተገነቡ የሚገኙት ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለነዋሪዎች እንደሚተላለፉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👎21👍1🥰1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል። በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባውን የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀን ከፍተናል። ማዕከሉ ወላጅ የሌላቸውንና በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናትን ከማሳደግ ባሻገር የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ትብብር ማሳያ ነው።

ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓም
👍13👎2
#ዓድዋን በዜማ፣ #ዓባይን በቅኔ........‼️

✍️ ሙዚቀኛ፣የግጥምና የዜማ ደራሲ፣ ዓድዋን በዜማ፣ ዓባይን በቅኔ የገለጠች፣

✍️ እኤአ በኖቬምበር 22 2024 በተለቀቀው ግላዲያተር ሁለት ማጀቢያ ሙዚቃ ላይ ተሳትፋለች፣

✍️ “ኢትዮጵያ”፣ “ዓባይ”፣ “ካህኔ”፣ “ናፈቀኝ” ሥራዎቿ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ጥልቅ ስፍራን ይዘው ይገኛሉ፣

✍️ “ዓድዋ” የተሰኘው ሙዚቃዋ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት የከፈሉትን መሥዋዕትነት አሳይታበታለች፣
🥰1611👍6🎉2