Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኤርትራዊያን ስደተኞች ክፍያ እንደሚጠየቁና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው

👉 በርካታ ኤርትራዊያን በኮንትሮባንድ፣ ፍልሰተኞችን በማዘዋወር እና በሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲሳተፉ ተገኙ
*******
(ኢ ፕ ድ)

ኤርትራዊያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ያለአግባብ ክፍያና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በርካታ የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች የኮንትሮባንድና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ ተገኝተዋል ብሏል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ በርካታ የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በማስገባትና በማስወጣት የኮንትሮባንድና ሌሎች ህገወጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ተገኝተዋል።

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሐሰተኛ ማንነት በመያዝ እንደሚንቀሳቀሱም ተጠቁሟል፡፡

በተለይ ለውጭ አገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች ተሰማርተው እንደሚገኙና በርካታ ፍልሰተኞችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ መገኘታቸውን አመላክቷል።

ለሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች ማዘጋጀት ህገወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ መገኘታቸውን ጠቅሶ ከህግ ውጭ ሰነዶችን መጠቀምና የገንዘብ ዝውውር እንደሚያከናውኑ ገልጿል።

ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የአገሩቱን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስቧል።

ኢትዮጵያ የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ስደተኞችን ጨምሮ የበርካታ አገራት ዜጎች እንድሚገኙ ይታወቃል።

ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓም
👍142
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎች አሳለፈ
****
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ በ4ኛ መደበኛ ስብሰባው በአጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህ መሠረት፤

👉 የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎቻ ጤና፣ ፅዳትና ውበት ወሳኝና ጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

👉 በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፤ አፈፃፀም ቁጥጥር፤ ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

👉 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ ላይ በመወያየት በመንግስትና የግል አጋርነት እንዲተዳደሩ፣ በከተማዋ የመንግስትና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ አግልጋሎት እንዲሰጡና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ ይደረጋል።

👉 በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።

👉 ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት ህንፃዎች፣ የግልና የመንግስት ቢሮዎች የምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከልና የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓም
👍31
በሙስሊም ኤይድ የተደረገው ድጋፍ በሆስፒታሎች የሚታየውን የህክምና ግብዓት እጥረት ለመፍታት ያግዛል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ የተደረገው ድጋፍ እንደሀገር በሆስፒታሎች የሚታየውን የህክምና ግብዓት እጥረት ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ገለጹ፡፡

ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ እንደተናገሩት ዛሬ በሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ የተደረገው ድጋፍ ግምታዊ ዋጋቸው ከ750 ሚሊዮን ብር በላይ (6 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር) የሚሆን የኢመርጀንሲ ኪቶች ሲሆኑ ጥራታቸው በዓለም ጤና ድርጅት የተረጋገጡና የአውሮፓን ስታንዳርድ ያሟሉ ናቸው፡፡

ሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ ለአምስት ጊዜያት በኢትዮጵያ የተለያዩ አከባቢዎች በርካታ የህክምና መድኃኒቶችንና ግብዓቶችን ድጋፍ አድርጓል። ባለፉት ዓመታት ግምቱ 15 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የህክምና ቁሳቁሶችን መለገሳቸውን ጠቁመው የዛሬው ለሰባተኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በትራንዚት መዘግየት ምክንያት በጁቡቲ ወደብ ላይ አምስት ኮንቴነር መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች መኖራቸውን የገለጹት ዑስታዝ አቡበከር፤ ቁሳቁሶቹ ወደ ሀገር ሲገቡ ለተቀሩ አከባቢዎች እንደሚከፋፈል ተናግረዋል።

በቀጣይ ምክር ቤቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለማህበረሰብ የሚጠቅሙ ግብዓቶችን የማፈላለግ ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡ ሌሎች ለጋስ ድርጅቶችና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ፈለግ በመከተል ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

የሙስሊም ኤይድ ዩ.ኤስ.ኤ ግብረ ሰናይ ድርጅት ላደረገው ድጋፍ፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ቁሳቁሶቹ በአጭር ጊዜ እንዲደርሱ በማድረግ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ የጤና ሚኒስትር የጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ማብራቱ ማሴቦ እና ድጋፍ የተደረገላቸው ሆስፒታል ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በአማን ረሺድ

ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍4👎1
ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ስኬታማነት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ እየተገበረች ላለው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ውጤታማነት ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያ ስላሴ ጥሪ አቀረቡ።

የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሀና አርዓያ ስላሴ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ትግበራ ምዕራፍን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ80 በላይ የሚሆኑ የምክክር መድረኮች ተካሂደዋል። በውይይቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች መሳተፋቸውን ገልጸዋል።

የሽግግር ፍትህ ማስተግበሪያ ስልቶችን የሚተገብሩ ተቋማትን ለማቋቋም የህግ ረቂቆች መዘጋጀታቸውን ገልጸው በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከሚካሄዱ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮች በኋላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚጸድቁ ገልጸዋል፡፡

ፖሊሲው የወንጀል ተጠያቂነት፣ እውነትን ማውጣት፣ ቅድመ-ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ምህረት፣ ማካካሻና ተቋማዊ ማሻሻያ፣ የተፈጸሙ ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እልባት በመስጠት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ያመ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲ ይሰፍን ዘንድ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የልማት አጋሮች ለሀገሪቱ ሰላም የአምሳደርነት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍21
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጎነት መኖሪያ መንደርን ጎበኙ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የበጎነት መኖሪያ መንደን ዛሬ ጎብኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች በመኖሪያ መንደሩ በመገንባት ላይ ያሉ ተጨማሪ ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች ግንባታ ያለበትን ደረጃ  ተመልክተዋል።

በመንደሩ እስከ አሁን ሰባት የመኖሪያ ህንጻዎች ተጠናቅቀው ለልማት ተነሺዎች እና የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መተላለፋቸውን አመልክተዋል።

በመኖሪያ መንደሩ ለሚገኙ ነዋሪዎች የእንጀራ ፋብሪካን ጨምሮ ልዩ ልዩ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸውም ገልጸዋል።

በከተማ አስተዳደሩ እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ትብብር እየተገነቡ የሚገኙት ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለነዋሪዎች እንደሚተላለፉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👎21👍1🥰1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3