Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ዛሬ ከቀትር በኋላ አንካራ ቱርክ ገብተዋል። ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጽሕፈት ቤታቸው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
👍26😁5
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ
******
(ኢ ፕ ድ)

በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት ተጠናቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ተወያይተዋል። ሁለቱ መሪዎች ውይይቱን ካደረጉ በኋላም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርኪዬ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ከፍተኛ አስታዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ በበኩላቸው፤ የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት አይዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት ሰነድ ትብብርን፣ የኢኮኖሚ እድገትንና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓም
7👍4
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቱርክ ስኬታማ ቆይታ‼️
👍5
ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ 100 ኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ወደብ ላይ ደርሰዋል
*******
(ኢ ፕ ድ)
የመዲናዋን የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ያሳድጋሉ የተባሉ 100 ኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ግዥ ተከናውኖ ወደብ ላይ መድረሳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 16 ባቡሮች ወደ አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉንም ተጠቁሟል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ከኢፕድ እንደገለጹት፤ የትራንስፖርት ዘርፍ ያለው የብዙሃን ትራንስፖርት አቅም በተሟላ ሁኔታ ከመጠቀም አኳያ ችግር አለበት። ችግሩን ለመፍታት የከተማ አውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትን በአደረጃጀት፣ በአሰራር፣ በመመሪያ፣ በሰው ኃይልና በሌሎችም ግብዓቶች ሲሻሻል በመሆኑ ሪፎርም እየተደረገ ነው።

የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ያሉትን አውቶቡሶች ወደ ስምሪት ውስጥ እንዲያስገባና አገልግሎቱ እንዲሻሻል የማድረግ ስራ መስራቱን የገለጹት ቢሮ ኃላፊው፤ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ካሉት በተጨማሪ 149 አውቶቡሶች ወደ ስምሪት........https://press.et/?p=142822
5👍4🔥2👏2
በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረገው ውይይት የሁለትዮሽ ትብብር እንዲኖር ያስችላል - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል በቱርክ የአንካራ የተደረገው ውይይት በአገራቱ መካከል ጠንካራ የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ትብብር መፍጠር የሚያስችል ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በአፍሪካ ቀንድና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንዲሰሩ ያለው ፋይዳም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በተርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አቀራራቢነት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት ሁለቱን አገራት በሚያግባባ ስምምነት በስኬት መጠናቀቁ ይታወቃል።

ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓም
15👍5😁2👏1🖕1
ኢትዮጵያ በአማካኝ ከሚያስፈልጋት 12 የልብ ህክምና ማዕከላት ያላት አንድ ብቻ ነው

✍️ ከሰባት ሺህ በላይ ዜጎች የልብ ህክምና ለማግኘት ወረፋ ይጠብቃሉ፣

✍️ በ11 ወራት ለ542 ህሙማን ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ተሰጥቷል፣

✍️ ማዕከሉ በዓመት አንድ ሺህ 300 የሚደርሱ ታካሚዎችን ይቀበላል፣
****
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ በአማካኝ ከሚያስፈልጋት 12 የልብ ህክምና ማዕከላት ያላት አንድ ብቻ መሆኑ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ፡፡

ያለው የልብ ህክምና ማዕከልም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ከ50 በመቶ በታች እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ዋና ስራ አስፈጻሚ ህሩይ አሊ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ለ10 ሚሊዮን ህዝብ በአማካኝ አንድ የልብ ህክምና ማዕከል እንደሚያስፈልግ በቅርቡ የተጠና ዓለም አቅፍ ጥናት ያመለክታል፡፡

በ10 ሚሊዮን ህዝብ አንድ የልብ ህክምና ማዕከል ቢያስፈልግም ያለው አንድ ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በሀገሪቱ ያለው የልብ ህክምና ማዕከል አንድ ብቻ መሆኑ ዜጎች አገልግሎቱን በተገቢው ጊዜና ቦታ እንዳያገኙ አድርጓል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ከሰባት ሺህ በላይ ዜጎች የልብ ህመም ህክምና ለማግኘት ወረፋ ይጠብቃሉ።

እኤአ በ2024 11 ወራት ለ542 ህሙማን ነጻ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ተሰጥቷል። በዓመት አንድ ሺህ 300 የሚደርሱ ታካሚዎችን ከተለያዩ የሕክምና ተቋማት በሪፈራል እንደሚቀበል ተመላክቷል፡፡

በ11 ወራት ለ10 ሺህ 938 ሰዎች ከቀዶ ጥገና በፊትና በኋላ የህክምና ክትትል አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

ለሕክምና የሚያገለግሉ ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ባለመገኘታቸውና በሌሎች ምክንያቶች መስራት ከሚችለው ከ50 በመቶ በታች አቅሙ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ገበያ አለመኖራቸውና የገንዘብ እጥረት ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ እንዳይሰራ ምክንያት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ተቋማትና ግለሰቦች በተለያዩ አማራጮች ድጋፍ የሚያደርጉበትን ምቹ ሁኔታን በመፍጠር አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡

የልብ ማዕከሉ በማዕከል ደረጃ ከተቋቋመ ጀምሮ ለስድስት ሺህ 800 ታካሚዎች ነጻ የልብ ቀዶ ጥገና አድርጓል።

በሀገሪቱ ያለውን የልብ ህክምና ማዕከል እጥረት ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ሰፊ ጥረት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል፡፡

በሄለን ወንድምነው

ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓም
👍5👎1
“በአማራ ክልል ግጭቶች ባልነበሩባቸው ጊዜያት ከሚደርሰው የበለጠ ማዳበሪያ አድርሰናል”
-ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የግብርና ሚኒስትር
*******
(ኢ ፕ ድ)

አምና በአማራ ክልል ግጭቶች ባልነበሩባቸው ጊዜያት ከቀረበው የበለጠ ማዳበሪያ አድርሰናል ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ የምርጥ ዘር አቅርቦት በሁሉም አካባቢ እጥረት መኖሩን ጠቁመዋል።

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደገለፁት እንደ ግብርና ሚኒስቴር ግጭት ያሉባቸው አካባቢዎች የግብርና ግብዓቶችን ማድረስ ይጠበቅብናል። አምና አማራ ክልል ተደራሽ ያደረግነው ማዳበሪያ እስካሁን በክልሉ ግጭቶች ባልነበሩባቸው ጊዜያት ከሚደርሰው ማዳበሪያ የበለጠ ማድረስ ተችሏል።

ማዳበሪያ ለማድረስ የተከፈለው ዋጋ ቀላል አለመሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ማዳበሪያውን ለማጓጓዝ በጸጥታ ኃይል እጀባ እየተደረገ መሆኑን አሰታውሰው፣ ለዚህ ዋና ምክንያቱ አርሶ አደሩ ማረስና መዝራት ስላለበት..... https://press.et/?p=142797
👍11🖕2
በአዲስ አበባ ከተማ የፅንፈኛው የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ የፅንፈኛው የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በተደረገባቸው ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

በሽብር ወንጀል የተጠራጠሩት አራቱ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ሊውሉ የቻሉት በአዲስ አበባ ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ከፅንፈኛውን የሽብር ቡድን የወሰዱትን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ 120 የክላሽንኮቭ ጥይትና ኤፍ ዋን ቦንብ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ጠንካራ ክትትል ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ እጅ ከፍጅ ተይዘው ምርመራ እየተጠራባቸው እንደሚገኝ የምርመራ ቡድኑ ገልጿል።

ሕብረተሰቡ እስከአሁን እያደረገ ላለው ተሳትፎ ምስጋና እያቀረበ ተመሳሳይ የወንጀል ተግባር ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ጥሪ አቅርቧል።

ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓም
👍12👎81🔥1🤣1
በኦሮሚያ ክልል ከ800 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ተሰበሰበ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በ2017 የምርት ዘመን ከ800 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት መሰብሰቡን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡

በምርት ዘመኑ ከአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት ለማግኘት መታቀዱም ተጠቁሟል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቡናና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሳኒ አሚን ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ከመስከረም ወር ጀምሮ የቡና ምርት የመሰብሰብ ሥራ ተጀምሯል፡፡ ከመስከረም ወር እስከ ኅዳር ወር 2017 ዓም መጨረሻ ድረስ ከ800 ሺህ ቶን በላይ ቡና መሰብሰብ ተችሏል፡፡

ባለፈው ዓመት አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቶን የቡና ምርት እንደተገኘ ጠቅሰው፤ በዘንድሮ የምርት ዘመን አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ቶን ቡና ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት በክልሉ የቡና ምርት ከጥቅምት መጨረሻ ወይም የኅዳር ወር አጋማሽ ሳይደርስ መሰብሰብ.......

https://press.et/?p=142864
👍1
"ከተሞችን ውብና ዘመናዊ ለማድረግ በኮሪደር ልማት የጀመርናቸው እንቅስቃሴዎች ፍሬያማ እየሆኑ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ከተማ የታዩ ስኬታማ ተሞክሮዎችን ወደ ክልል ከተሞች በማስፋት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገቡ ነው። ለአብነት በሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ምን ያህል የከተማዋን ገፅታ በመቀየር ጉልህ አስተዋፆ እያበረከተ እንደሚገኝ ማየት እንችላለን"

- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ

ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍1