Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የዕድሎች ማሳያ የሆነች በአህጉሩ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት አንዷ ናት። በማደግ ላይ ካሉት ዘርፎቿ መካከል ለሀገር ውስጥም ሆነ ለአለምአቀፍ ኢንቨስትመንት ሰፊ አቅም ያለውና እድገቷን በመምራት ትልቅ ስፍራ እየያዘ የመጣው የወርቅ ማምረት ኢንደስትሪ አንዱ ነው።
በወርቅ ክምችት የታደሉት የሻኪሶ እና ሰፊው የጉጂ አካባቢ የማዕድን ማውጣት ሥራው ዐቢይ ስፍራዎች ናቸው። በሻኪሶ በቅርቡ የተመረቀው የዋይ ኤም ጂ ጎልድ ማይኒንግ ተቋም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተስፋ ሰጪ እድሎችን ይዞ የመጣ ሆኗል። በመሬት ስበት ተመሥርቶ የሚሰራውን ዘመናዊ የማዕድን ቴክኖሎጂን የሚጠቀመው የዋይ ኤም ጂ የምርት ሥራ ጠንቀኛ ኬሚካሎችን ከመጠቀም የተጠበቀ ፈጠራ የሞላበት እና የአካባቢ ጥበቃ ተስማሚነትን ያረጋገጠ ነው።
በጉጂ በነበረኝ ጉብኝት በኢትዮዽያ መሪ የወርቅ ምርት ኩባንያዎች አንዱ የሆነውን የሚድሮክ ጎልድ የሥራ እንቅስቃሴንም ተመልክቻለሁ። በዘርፉ ቀዳሚ እንደመሆኑ በትልቅ አቅም እና ደረጃ በሚሰራው የወርቅ ምርት ሥራ ለኢትዮጵያ የማዕድን ከባቢ ከፍ ያለ አስተዋጽዖ አበርክቷል።
5👍2
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍63
ትላንት በገላን ጉራ በተመረቁት ሶስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ተጀመረ
**************************************
(ኢ.ፕ.ድ)
ትላንት በገላን ጉራ በተመረቁት ሶስት ትምህርት ቤቶች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) የመማር ማስተማር ስራውን አስጀምረዋል።

ተማሪዎች ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ሆነው በተገነቡት ትምህርት ቤቶች እየተማሩ የላቀ ውጤት ለማምጣት እንዲተጉ የቢሮ ሀላፊው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከተማው ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
👍91
በምዕራብ ጉጂ ገላን ወረዳ ከዚህ ቀደም ታርሶ የማያውቅ መሬት በቀርጫንሼ ትሬዲንግ አማካኝነት ወደ ምርታማ የቡና እርሻ ስፍራነት ተቀይሯል።
በቀርጫንሼ የለማው መሬት ሜካናይዝድ እርሻን በመጠቀም አመርቂ የሆነ በሄክታር የ60 ኩንታል ምርት የሚያስገኝ ነው።
በጉብኝቱ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የቡና ችግኝ ተክለዋል።
#PMOEthiopia
ታህሳስ 1ቀን 2017 ዓ.ም
👍11👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ያደረጉት አቀባበል

#PMOEthiopia
7🤣7🤬4👍2👎2
እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=142705
መልካም ቀን!
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን‼️
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ 👇
https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et
👍5🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን ከፍተኛ ቡና አምራች ሀገር ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ስራዎች ዓመታዊ የቡና ምርት መጠንን ከነበረበት 500 ሺህ ቶን በእጥፍ ማሳደግ ተችሏል።

ከገቢ አንጻርም በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፤ በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ ይህን አሃዝ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው።

እስካሁን ባለው ሂደትም እቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ አበረታች ውጤቶች ከወዲሁ እየተመዘገቡ ነው።

ዘመናዊ የቡና መስኖ ልማትና በማሽን የታገዘ የቡና ለቀማ በማካሄድ በሄክታር እስከ 60 ኩንታል ማግኘት መቻሉ ደግሞ ለዚሁ ስኬት ጥሩ ማሳያ ነው።
👍14👏2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከቻይና ኩባንያዎች ጋር የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረመ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከዢያሜን ኤርፖርት ግሩፕ ኩባንያ የስትራቴጂክ ትብብር እና ከቻይናው ሄናን አቪዬሽን ግሩፕ ኩባንያ ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።

የስትራቴጂክ ትብብር ስምምነቱ የአየር ካርጎ ንግድ ትስስርን ማጠናከርና በዘርፉ ያለውን የጥራት እድገት መጨመር፤ በዓለም የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ያላቸውን የትብብር አድማስ ማስፋትን አላማ ያደረገ መሆኑ የአየር መንገዱን መረጃ ያመለክታል።

ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓም
👍51🔥1👏1