Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጋና ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
*******
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲስ ለተመረጡት የጋና ፕሬዚዳንት ጆን መሃማ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ “በአመራር ጉዞዎና ወደፊት በሚያደርጉት ጥረት ታላቅ ስኬትን እመኛለሁ” ብለዋል።

ህዳር 30 ቀን 2017 ዓም
👍54
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️
የሀዋሳ ኮሪደር የራሱ ልዩ አሰራር ያለው ሆኖ በአዲስ አበባ የተጀመረውን የከተማ ልማት ጥረት ያስቀጠለ ሥራ ነው። ሰፋ ያሉ የእግረኛ መንገዶች፣ የተለዩ የብስክሌት መንገዶች፣ በሀገር ውስጥ የተመረቱ ስማርት የመብራት ምሰሶዎች ወዘተ የሥራውን ፈጠራን እና ቀጣይነትን ያሳያሉ። ይሁንና የከተማ ልማት የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ አይደለም፤ የተሳካ ይሆን ዘንድ የማኅበረሰቡን ንቁ ተሳትፎ ይሻል። ርምጃዎቻችን መልካም ቢሆኑም እነዚህን አሻጋሪ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ብዙ ሥራ ይቀረናል። ኢትዮጵያ ሰፊ እና ሀብት የሞላባት ሀገር እንደመሆኗ እምቅ አቅሟ ግዙፍ ነው። ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህን በመገንዘብ ለሥራ የሚነሱበት ጊዜው አሁን ነው።
👍7
እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=142642
መልካም ቀን!
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን‼️
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ 👇
https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et
👍52
“በቀጣይ ጥቃት አድርሶ እንደተፈለገ መኖር የማይቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል” ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
*****************************************
( ኢ ፕ ድ )
በቀጣይ ጥቃት አድርሶ እንደተፈለገ መኖር የማይቻልበት ሁኔታ እንደሚፈጠር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ አስታወቁ፡፡ ጥቃት አድራሾችን መመዝገብ የሚያስችል ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት እየጎለበተ እንደሆነም ጠቆሙ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ የሴቶችና የሕፃናት ጥቃት ከእለት ተእለት እጨመረ መጥቷል። ችግሩን ውጤታማ በሆነ መንገድ መከላከል የሚያስችል አስተማሪ ሕግ እየተረቀቀ ነው ብለዋል ።

በአሁኑ ሰአት ቀደም ሲል የነበረውን ሕግ ለማሻሻል፤ ሕጉን የመፈተሽ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ማሻሻያው በቀደመው ሕግ ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች በመለየት የመከላከሉን ሥራ ውጤታማ ማድረግ …
https://press.et/?p=142635
ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
👍7
ምሥራቅ አፍሪካን የማስተሳሰር ጉዞ
****************
( ኢ ፕ ድ )
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለሚኖር ወዳጅነት እና የጋራ ተጠቃሚነት ከፍተኛ ትኩረት እየሰጠ ነው። ይህ ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ አካሄድ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ አጋርነት፣ የጸጥታ ትብብር፣ የባህል ልውውጦች እና የአካባቢ ዘላቂ ግንኙነትን ጨምሮ የሁለትዮሽ እና ክልላዊ ትብብርን በተለያዩ መስኮች ማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጥ ነው።

ኢትዮጵያ አካባቢያዊ ቀጣናዊ መረጋጋትን፣ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ የልማት ስራዎችን መስራት ፣ በተለይም ሰላምን በማስፈን ሀብቶችን ለጋራ ጥቅም ለመጠቀምና ለማልማት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ አስታውቃለች። ለጉዳዩ ያላትን ቁርጠኝነትም በተጨባጭ አሳይታለች።

ለዚህም በማሳያነት የሚገለፀው የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን እያካሄደች ነው። በተለይም በኃይል አቅርቦት፣ በባቡር መስመር ግንባታ እና በንጹህ ውሃ አቅርቦት ዙሪያ ተጠቃሽ የሆኑ ሥራዎችን አከናውናለች፤ ለሱዳን፣ ለደቡብ ሱዳን፣ ለኬንያ እና ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች ነው። ለጅቡቲ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ እያቀረበች ትገኛለች።

ከሰላም አኳያም የሶማሌን ሰላም ለማረጋገጥ የከፈለችው መስዋእትነት እንዲሁም፤ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳናውያን የውስጥ ችግራቸውን በሰላም እንዲፈቱ ሰፊ ጥረቶችን…
https://press.et/?p=142652
ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
👍2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የዕድሎች ማሳያ የሆነች በአህጉሩ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት አንዷ ናት። በማደግ ላይ ካሉት ዘርፎቿ መካከል ለሀገር ውስጥም ሆነ ለአለምአቀፍ ኢንቨስትመንት ሰፊ አቅም ያለውና እድገቷን በመምራት ትልቅ ስፍራ እየያዘ የመጣው የወርቅ ማምረት ኢንደስትሪ አንዱ ነው።
በወርቅ ክምችት የታደሉት የሻኪሶ እና ሰፊው የጉጂ አካባቢ የማዕድን ማውጣት ሥራው ዐቢይ ስፍራዎች ናቸው። በሻኪሶ በቅርቡ የተመረቀው የዋይ ኤም ጂ ጎልድ ማይኒንግ ተቋም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተስፋ ሰጪ እድሎችን ይዞ የመጣ ሆኗል። በመሬት ስበት ተመሥርቶ የሚሰራውን ዘመናዊ የማዕድን ቴክኖሎጂን የሚጠቀመው የዋይ ኤም ጂ የምርት ሥራ ጠንቀኛ ኬሚካሎችን ከመጠቀም የተጠበቀ ፈጠራ የሞላበት እና የአካባቢ ጥበቃ ተስማሚነትን ያረጋገጠ ነው።
በጉጂ በነበረኝ ጉብኝት በኢትዮዽያ መሪ የወርቅ ምርት ኩባንያዎች አንዱ የሆነውን የሚድሮክ ጎልድ የሥራ እንቅስቃሴንም ተመልክቻለሁ። በዘርፉ ቀዳሚ እንደመሆኑ በትልቅ አቅም እና ደረጃ በሚሰራው የወርቅ ምርት ሥራ ለኢትዮጵያ የማዕድን ከባቢ ከፍ ያለ አስተዋጽዖ አበርክቷል።
5👍2
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍63
ትላንት በገላን ጉራ በተመረቁት ሶስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ተጀመረ
**************************************
(ኢ.ፕ.ድ)
ትላንት በገላን ጉራ በተመረቁት ሶስት ትምህርት ቤቶች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) የመማር ማስተማር ስራውን አስጀምረዋል።

ተማሪዎች ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ሆነው በተገነቡት ትምህርት ቤቶች እየተማሩ የላቀ ውጤት ለማምጣት እንዲተጉ የቢሮ ሀላፊው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከተማው ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
👍91