ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን ተመልክተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ አርባምንጭ ከተማ የሚገኘው ብሔራዊ ፓርኩ የሳቫና የሳር ምድርን፣ የደንና የውቦቹን የአባያና ጫሞ ሃይቆችና ሌሎች መዳረሻዎች መገኛ ሲሆን በተለያዩ መልክዓምድሮች ውብ ኅብር የታወቀ የተፈጥሮ መስህብም ነው።
514 ስኩዌር ኪሎሜትሮች የሚሰፋው ፓርክ አይነተ ብዙ ለሆኑ የሜዳ አህያ፣ አጋዘን፣ አዞ፣ የዱር እንስሳት፤ ከ270 በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች መገኛ በመሆኑ ለተፈጥሮ አፍቃሪዎች የልብ አድራሽ አይነተኛ ስፍራ ነው። እንደሌሎች ብሔራዊ ፓርኮች ነጭ ሳር የተፈጥሮ ሥነምኅዳርን በመጠበቅና ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
#PMOEthiopia
ህዳር 29 ቀን 2017 ዓም

👍5❤3
ዛሬ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች የተሰማውን ተኩስ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታውቃል።
መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።
የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር ችሏል።
ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

👎20👍15❤5
ከ600 በላይ አውቶብሶችና ታክሲዎችን የሚያስተናግዱ ተርሚናሎች ተገንብተዋል
******
(ኢ ፕ ድ)
በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት በአንድ ጊዜ ከ600 በላይ አውቶብሶችና ታክሲዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ተርሚናሎች መገንባታቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። ከ185 በላይ የታክሲና የአውቶብስ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች መሠራታቸውንም ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ አስተዳደሩ አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግና ለማዘመን የኮሪደር ልማት እያካሄደ ነው። በመጀመሪው ዙር የኮሪደር ልማትም ትልቅ ትኩረት የተሰጠው የትራንስፖርት ዘርፉን ማዘመን ሲሆን በዚህም ከ600 በላይ አውቶብሶችና ታክሲዎችን የሚያስተናግዱ ተርሚናሎች ተገንብተዋል።
እንደ ቢሮ ኃላፊው ገለጻ፤ በልማቱ ለሞተር አልባ ትራንስፖርት በተሰጠው ትኩረት በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት 100 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የእግረኛ እና ከ100 ኪሎ ሜትር በላይ የብስክሌት መንገድ..... https://press.et/?p=142572

👍4👎1
388 ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገው የካርበን ሽያጭ
******
(ኢ ፕ ድ)
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጎዱ አካባቢዎችን በደን ለመሸፈንና እንዲያገግሙ ለማድረግ የአረንጓዴ ዐሻራን መርሐ ግብርን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው። የደን ሽፋንን ለማሳደግና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችም እየተሠሩ ይገኛል።
በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ፕሮጀክቶች አስተባባሪ አቶ ወርቅነህ ያደሳ እንደገለጹት፣ የተራቆተ መሬትን መልሶ እንዲያገግም በማድረግ የሁምቦና የሶዶ አርሶ አደሮች ብቻ ከካርቦን ሽያጭ አንድ ነጥብ 18 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።
የተራቆተ መሬትን መልሶ እንዲያገግም የሚያስችለው ፕሮጀክት በስምንት ክልሎች በሚገኙ 37 ወረዳዎች ላይ እየተተገበረ መሆኑን የገለጹት አስተባባሪው፣ እስካሁን ከ268 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን መልሶ ማልማት ተችሏል።
ፕሮጀክቱ አካባቢውን ከእንስሳት ንክኪ ነፃ በማድረግ መልሶ እንዲያገግሙ የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፣ ይህም የአፈር መሸርሸርን መቀነስ፣ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ለእንስሳት መኖን.......https://press.et/?p=142555

👍7
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍8
"ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገ ስብዕናን ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ ለሁሉም የምትመች እና ከሙስና ስጋት ነፃ የሆነች ከተማን መገንባት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገናል"
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️
የሀዋሳ ኮሪደር የራሱ ልዩ አሰራር ያለው ሆኖ በአዲስ አበባ የተጀመረውን የከተማ ልማት ጥረት ያስቀጠለ ሥራ ነው። ሰፋ ያሉ የእግረኛ መንገዶች፣ የተለዩ የብስክሌት መንገዶች፣ በሀገር ውስጥ የተመረቱ ስማርት የመብራት ምሰሶዎች ወዘተ የሥራውን ፈጠራን እና ቀጣይነትን ያሳያሉ። ይሁንና የከተማ ልማት የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ አይደለም፤ የተሳካ ይሆን ዘንድ የማኅበረሰቡን ንቁ ተሳትፎ ይሻል። ርምጃዎቻችን መልካም ቢሆኑም እነዚህን አሻጋሪ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ብዙ ሥራ ይቀረናል። ኢትዮጵያ ሰፊ እና ሀብት የሞላባት ሀገር እንደመሆኗ እምቅ አቅሟ ግዙፍ ነው። ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህን በመገንዘብ ለሥራ የሚነሱበት ጊዜው አሁን ነው።

እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=142642
መልካም ቀን!
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን‼️
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ 👇
https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et

👍5❤2
“በቀጣይ ጥቃት አድርሶ እንደተፈለገ መኖር የማይቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል” ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
*****************************************
( ኢ ፕ ድ )
በቀጣይ ጥቃት አድርሶ እንደተፈለገ መኖር የማይቻልበት ሁኔታ እንደሚፈጠር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ አስታወቁ፡፡ ጥቃት አድራሾችን መመዝገብ የሚያስችል ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት እየጎለበተ እንደሆነም ጠቆሙ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ የሴቶችና የሕፃናት ጥቃት ከእለት ተእለት እጨመረ መጥቷል። ችግሩን ውጤታማ በሆነ መንገድ መከላከል የሚያስችል አስተማሪ ሕግ እየተረቀቀ ነው ብለዋል ።
በአሁኑ ሰአት ቀደም ሲል የነበረውን ሕግ ለማሻሻል፤ ሕጉን የመፈተሽ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ማሻሻያው በቀደመው ሕግ ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች በመለየት የመከላከሉን ሥራ ውጤታማ ማድረግ …
https://press.et/?p=142635
ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም