Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

19ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በውቢቷ አርባምንጭ ከተማ በደማቅና ባማረ ሁኔታ አክብረናል። የዓመት ሰው ይበለን።
አርባምንጮች እናመሰግናለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ህዳር 29 ቀን 2017 ዓም
👍4
"አብሮነታችን በምንም ሁኔታ የማይሸረሽር እንዲሆን በጋራ እንወስን"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አርባምንጭከተማ

በውብ የተፈጥሮ መልኳ እና በባህል ቅርስ ሃብታምነቷ የተከበረችውና የተወደደችው አርባምንጭ በአባያና ጫሞ ሀይቆች መሃል ታቅፋ የታዋቂው የአዞ ገበያ እና የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ መገኛ ሆና ደምቃ ትታያለች።

በግብርና ማዕከልነቷ ከፍራፍሬ እርሻ ባሻገር በድንቅ መልክዓ ምድሯና ድንቅ ባሕሏ ዋና የቱሪስት መዳረሻ ናት።

እንደ ገበታ ለትውልድ ያሉ አዳዲስ አስደናቂ ሥራዎች ለውቧ መዳረሻ የበለጠ መስህብ ሆነዋል።

ህዳር 29 ቀን 2017 ዓም
👍4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን ተመልክተዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ አርባምንጭ ከተማ የሚገኘው ብሔራዊ ፓርኩ የሳቫና የሳር ምድርን፣ የደንና የውቦቹን የአባያና ጫሞ ሃይቆችና ሌሎች መዳረሻዎች መገኛ ሲሆን በተለያዩ መልክዓምድሮች ውብ ኅብር የታወቀ የተፈጥሮ መስህብም ነው።

514 ስኩዌር ኪሎሜትሮች የሚሰፋው ፓርክ አይነተ ብዙ ለሆኑ የሜዳ አህያ፣ አጋዘን፣ አዞ፣ የዱር እንስሳት፤ ከ270 በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች መገኛ በመሆኑ ለተፈጥሮ አፍቃሪዎች የልብ አድራሽ አይነተኛ ስፍራ ነው። እንደሌሎች ብሔራዊ ፓርኮች ነጭ ሳር የተፈጥሮ ሥነምኅዳርን በመጠበቅና ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

#PMOEthiopia

ህዳር 29 ቀን 2017 ዓም
👍53