Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

ከአምስት ወራት በፊት ከነበረኝ ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ የአርባምንጭ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ገምግመናል። ይኽ ሥራ የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም የሚያጠናክር የአካባቢውን አስደናቂ የተፈጥሮ መልክዓ ምድርና የተትረፈረፈ ሀብት ቆጥሮ የሚጠቀም ሁሉን ያካተተ ነው።

ቱሪዝምን ከማሳደግ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ፕሮጀክቱ ትርጉም ባለው ደራጃ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። እነዚህን መሰል ሥራዎች በስኬት ሥራ ሲጀምሩ ለዘላቂ ልማትና ብልፅግና መንገድ የሚጠርጉ ይሆናሉ።

ህዳር 28 ቀን 2017 ዓም
6👍4
#አርባምንጭከተማ

19ኛው የብሔሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት"

19ኛው የብሄር ብሄረሰብ በዓል በአርባምንጭ ከተማ በአርባምንጭ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

ህዳር 29 ቀን 2017 ዓም
👍31
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ19ኛው ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ ባስተላለፉት መልዕክት‼️

✍️ ጋምዎች ውብ ስለሆናችሁ፣ ፍቅር ስለምታውቁ፣ ምድራችሁ እጅግ ያማረ ነው፣

✍️ ኢትዮጵያ ትልቅ ቤተ-መፃህፍት ናት፣

✍️ ህብረ ብሄራዊት ኢትዮጵያን ለማፅናት መሰል ታላላቅ በዓላት ጉልህ ሚና ይጫወታል፣

✍️ኢትዮጵያን ማበልፀግ ቀዳሚ አጀንዳችን እንዲሆን ስራና ስራ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ይገባል፣

✍️ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ምሳሌ ሆናችሁ እንድትቀጥሉ በታላቅ ትህትና ላሳስባችሁ እወዳለሁ!

✍️ ኢትዮጵያ ከላይ በአምላኳ ተፈቅዶላታልና ትበለጽጋለች!

✍️ ኢትዮጵያ በፈጣሪ ቸርነት በእኛ ትጋት ከጀመረችው የብልጽግና ጉዞ የሚያስተጓጉላት የለም!

✍️ ፍቅር ታጥቀን ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን!

✍️ መነጋገር ከመገዳደል ይሻላል!

✍️ ይኸንን አስደናቂ ዓለም የፈጠረ፣ በማንም የማይሸነፍ፣ ፍቅር የሆነ አምላካችንን በመተማመን የኢትዮጵያ ብልጽግና በማንም ኃይል እንደማይቀለበስ በእርግጠኝነት እንናገራለን!
👍92
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ተከብሮ ተጠናቀቀ
***
(ኢ ፕ ድ)

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የታለመለትን ዓላማ በማሳካት በአማረና በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታውቋል።

20ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ባዕልን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንዲያዘጋጅ ተወስኗል።

19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በአርባ ምንጭ ከተማ ተከብሯል።

ህዳር 29 ቀን 2017 ዓም
👍4