የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር መልዕክት‼️
ደቡብ ኢትዮጵያን መጎብኘት እና እንደአርባምንጭ ያሉ ከተሞችን እድገት መመልከት ሁልጊዜም አስደሳች ነው።
እንደ ሀገር የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለከተሞችም ሆነ ለገጠር አካባቢዎች ፈተና ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ዛሬ በመጎብኘት ላይ እንዳለነው አይነት የሙዝ ልማት ሥራዎችን በገጠር አካባቢዎች በማሳዎች ላይ የኩታ ገጠም እርሻ አሰራረን ጀምረናል። እነዚህን ጥረቶች የሚደግፈው የሌማት ትሩፋት ሥራ በየአርሶአርብቶአደሩ ቤት የእንቁላል ምርትን ከአሳ እና ከብት ርባታ ብሎም ንብ ማነብ ጋር ምርት በማሳደግ ላይ ይገኛል።
እነዚህ መርሃግብሮች በጥምር የገጠሩ እና የከተማው ነዋሪዎች ከትሩፋቱ እንዲካፈሉ አልመው ሰርተዋል። በተለይ የኩታ ገጠም እርሻ በአርባምንጭ ታላቅ ተስፋ የሰነቀ ነው።
ህዳር 28 ቀን 2017 ዓም

👍9
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባምንጭ የተደረገላቸው አቀባበል
19ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ነገ ለማክበር የተዘጋጀችው እንግዳ ተቀባይዋ የአርባ ምንጭ ከተማ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ለከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርጋለች።

👍7
የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ
****
(ኢ ፕ ድ)
የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ ለስራ ጉብኝት ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባሉ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።
ጁሬስካ ከውይይታቸው በተጨማሪ የአድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችና ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዳር ወር 2016 ዓም በቼክ ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው አይዘነጋም። የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ በጥቅምት ወር 2016 ዓም በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያና የቼክ ሪፐብሊክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደ አውሮፓውያን አቆጠጣር በ1993 እንደተጀመረ መረጃዎች ያሳያሉ። ሁለቱ ሀገራት በግብርናና ገጠር ልማት፣ በሕዝብ አስተዳደርና ሲቪል ማኅበረሰብ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ማኅበራዊ ልማት ላይ ትብብራቸውን ለማጠናከር እየሰሩ እንደሚገኙ የኢዜአ መረጃ ያመለክታል።

የልጅነት ህልሙን ያሳካው ወጣት
ካፒቴን ልዑል ማሙዬ ይባላል፡፡ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በአብራሪነት ለሁለት ዓመት ስልጠናውን በመከታተል በከፍተኛ ውጤት አጠናቋል ፡፡
ካፒቴን ልዑል አብራሪ መሆን የልጅነት ህልሙ እንደነበር ይናገራል፡፡ ለልጅነት ህልሙ መሳካት ጊዜ እና ትኩረት ሰጥቶ ሲሰለጥን እንደቆየ ያስረዳል፡፡
ህልሙን ለማሳካት ከራሱ ጥረት ባለፈም ወላጆቹና የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ እገዛ እንዳደረጉለት ያብራራል፡፡
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ስልጠናውን በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የሚሰጥበት የተሟላ የትምህርት መሳሪያ ያለው መሆኑ ለእኔ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት አንዱ ምክንያት ነው ሲል ያስረዳል፡፡
አሁን ሀገሬ እኔ ላይ ኢንቨስት ያደረገችውን የምከፍልበት ጊዜ ነው የሚለው ከፒቴን ልዑል፤ ያለኝን ጊዜ እና የተማረኩትን ትምህርት ሀገሬ ላይ ኢንቨስት አደርጋሉ ነው ያለው፡፡
የሀገሬን ባንድራ የያዘወን የኢትዮጵያ አውሮፕላን በተለያዩ የዓለም ሀገራት በማብረር የአየር መንገዱን ስኬታማነት ለማስቀጠል ጥረት አደርጋለሁ ሲል ተናግሯል፡፡
ለኢትዮጵያ ኩራት በአፍሪካ ደግሞ አንደኛ በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አባል በመሆኑ መደሰቱን ገልጿል፡፡
የካፒቴን ልዑል ወላጅ እናት ወይዘሮ ሀና አንበሴ በበኩላቸው፤ ልጄ ከልጅነቱ ጀምሮ ስነስርዓት ያለው እና ትምህርቱን በአግባቡ የሚከታተል ነው፡፡ ልጄ በከፍተኛ ውጤት እንደሚመረቅም እርገጠኛ ነበርኩ ተሳክቶልኛል ይላሉ፡፡
ልዑል ከልጅነት ጀምሮ አብራሪ የመሆን ህልም አለው የሚሉት ወይዘሮ ሃና፤ ህልሙ ተሳክቶለት ለዚህ ደርሷል ነው ያሉት፡፡
የካፒቴን ልዑል ወላጅ አባት ኮሎኔል ማሙዬ ወሰና በበኩላቸው ልጄ በአብራሪነት በከፍተኛ ውጤት በመመረቁ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
በሄለን ወንድምነው

👍6❤3