Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የወሰዱ ዜጎች ቁጥር 10 ሚሊየን ደረሰ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የወሰዱ ዜጎች ቁጥር 10 ሚሊየን መድረሱን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

የፕሮግራሙ የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አቤኔዘር ፈለቀ እንደገለጹት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሁሉን አቀፍ፣ አካታችና አስተማማኝ አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡፡

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አሰራር ሥርዓት በማዘመንና ዲጂታል በማድረግ ብልሹ አሠራርን ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ዲጂታል መታወቂያ በተለያዩ ተቋማት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው÷በቀጣይ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መታወቂያውን እንደ ቅድመ ሁኔታ እንደሚጠይቁ አንስተዋል፡፡

በቅርቡም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የባንክ አካውንት ለመክፈት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደቅድመ ሁኔታ መጠየቅ እንደሚጀመር ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በመዲናዋ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ አስገዳጅ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ድረስም 10 ሚሊየን በላይ ዜጎች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደወሰዱ ነው አቶ አቤኔዘር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የገለጹት፡፡

ስለሆነም ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የተለያዩ ማዕከላት ተመዝግበው ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

ህዳር 27 ቀን 2017 ዓም
👍9
#ውብአዲስ
የአዲስ አበባ አዳዲስ ገጽታዎች‼️
ህዳር 27 ቀን 2017 ዓም
👍108👎1
አምስቱ አውሮፕላኖች አንበጣን፣ ግሪሳንና ተባዮችን ለመከላከል ትልቅ አቅም ፈጥረዋል
******
(ኢ ፕ ድ)

የግብርና ሚኒስቴር የገዛቸው አምስት አውሮፕላኖች የአንበጣ መንጋን፣ የግሪሳ ወፍንና ድንበር ዘለል የሆኑ ተባዮች በሰብል ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ከመከላከል አኳያ ትልቅ አቅም ፈጥረዋል ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል የገዛቸው አምስት አውሮፕላኖች ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡

አውሮፕላኖቹ የጸረ ተባይ ኬሚካል ርጭት በማካሔድ የሰብል ምርቱን ከአንበጣ መንጋና ከግሪሳ ወፍ በመከላከል ረገድ ድርሻቸው የጎላ ነው፡፡ በተለይም ድንበር ዘለል የሆኑ ተባዮችን ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመፍጠር.....

https://press.et/?p=142383
👍41
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍2
የጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ምህረት ጠየቁ
***
(ኢ ፕድ)

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ምህረት ጠይቀው ገብተዋል።

የታጣቂ ቡድኑ ሎጄስቲክስና ፋይናንስ ኀላፊ ነጋ አዛናው እና የቡድኑ ዘመቻ ኃላፊ ዋና ሳጅን ክብረት አያሌው የሰላም ጥሪውን በመቀበል ምህረት ጠይቀው ገብተዋል።

የጽንፈኛ ቡድኑ አመራሮች በተሳሳተ አጀንዳ ተታልለው ወደ ጫካ መግባታቸውን በማስታወስ በቀጣይም የበደሉትን ማኅበረሰብ ለመካስ ለሰላም እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

እንደ አሚኮ ዘገባ፣ የጦርነት ትርፉ ኪሳራ ነው። በተሳሳተ አጀንዳ በመደናገር የወጡ አካላትም ቆም ብለው በማሰብ የሰላም ጥሪውን ተጠቅመው ወደ ማኅበረሰቡ ሊቀላቀሉ ይገባል።

ህዳር 28 ቀን 2017 ዓም
5👎4👍3👏1😁1🍌1
የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በጥሩ ሂደት እየተከናወነ መሆኑን በምልከታ አረጋግጠናል
******
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በጥሩ ሂደት እየተከናወነ መሆኑን በምልከታቸው እንዳረጋገጡ የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች ገለጹ።

የአፍሪካ ሕብረት፣ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽንና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች በዕዳጋ-ሀሙስና በመቀሌ ማዕከል የቀድሞ ታጣቂዎችን የተሀድሶ ሥልጠና አሰጣጥ ሂደት ተመልክተዋል።

በአፍሪካ ኅብረት ሥር የፕሪቶሪያ የሰላም ሥምምነት የቁጥጥር፣ ማረጋገጥና ማስከበር ተልዕኮ ቡድን አባል ብርጋዴር ጄኔራል ትሸፖ ማፉዛ በዕደጋ-ሀሙስና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መለስ ዜናዊ ካምፓስ በነበረ ምልከታ ለቀድሞ ታጣቂዎች የሚሰጠው የተሀድሶ ሥልጠና በጥሩ ሂደት እየተከናወነ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

ቅድመ ዝግጅቱ ስኬታማ በሆነው ሂደትም የቀድሞ ታጣቂዎች ሥልጠናቸውን በቀናነት በመከታተል ወደ ቤተሰቦቻቸው መዋሃድ የሚችሉበት ዕድል መፈጠሩን በሚያደርጉት የቁጥጥር፣ ማረጋገጥ፣ ማስከበርና የክትትል ሥራ ማረጋገጣቸውን አስረድተዋል።

የአፍሪካ ኅብረትም ከጅማሮው አንስቶ ለብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በሚያደርገው እገዛ ቀጣይነት ያለው የድጋፍ፣ ቁጥጥርና የክትትል ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ጸጥታ ክፍል የፖለቲካ ባለሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ቡድን አባል ኢርነስት ናያ ዶሎ በበኩላቸው የዕደጋ-ሀሙስና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መለስ ዜናዊ ካምፓስ ማዕከላት የቀድሞ ታጣቂዎችን ከመቀበላቸው በፊት የዝግጅት ሥራ ላይ ምልከታ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

በማዕከላቱ የምግብ፣ ምዝገባ፣ የባንክ ሂሳብ መክፈቻና አስፈላጊ ማዕከላት ተደራጅተው የቀድሞ ታጣቂዎችን በተገቢው መንገድ እያስተናገዱ እንደሚገኙ ተመልክተናል ብለዋል።

በአፍሪካ ኅብረት የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶ ሥልጠና የማሳለፍ መርህ መነሻነትም የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚያደርገው ጥረት ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የተሀድሶ ሥልጠና የሚሰጥባቸው የመቀሌና ዕዳጋ-ሀሙስ ማዕከላት በተቀመጠው ዕቅድ መሰረት የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሳካ መንገድ እያስተናገዱ ነው ያሉት ደግሞ በብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የፕሮግራም ዕቅድና ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል በላይ አበበ ናቸው።

የተሀድሶ ሥልጠና ተጠቃሚ የቀድሞ ታጣቂዎች በሚኖራቸው የስድስት ቀናት የቆይታ ሂደትም በጥሩ ሁኔታ እየተከታተሉ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በዚህም ዕዳጋ ሀሙስ ማዕከል ለ3ኛ ዙር፥ የመቀሌ ማዕከል ደግሞ ለ5ኛ ዙር እንዲሁም በአዲግራትና መቀሌ ከተማ ዙሪያ ተንቀሳቃሽ ማዕከላት እየተስተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በትግራይ ክልል በመጀመሪያው ምዕራፍ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ኅዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የፌደራል መንግሥት፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ተባባሪና ለጋሽ አሕጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት የተጀመረው ሥራ በሁለቱ ማዕከላት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ህዳር 28 ቀን 2017 ዓም
👍4👎1
የእጅ ስልክ ይዘው ሲያሽከረክሩ የተገኙ 28ሺህ አሽከርካሪዎች ተቀጡ
***
(ኢ ፕ ድ)

በመዲናዋ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የእጅ ስልክ ይዘው ሲያሽከረክሩ የተገኙ 28ሺህ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ገለጸ፡፡

በትራፊክ አደጋ በንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያና ሕዝብ ግንዛቤ ዲቪዢን ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2017 በጀት ዓመት ሶስት ወራትም 28ሺህ አሽከርካሪዎች የእጅ ስልክ ይዘው ሲያሽከረክሩ፣ ሰባት ሺህ 316 ከፍጥነት በላይ ያሽከረከሩ እንዲሁም ጠጥቶ በማሽከርከር የተያዙ 871 አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው ቅጣት ተላልፏል፡፡

የቴክኒክ ምርመራን ያላሟሉ ስድስት ሺህ 671 አሽከርካሪዎች ተገቢው ቅጣት የተላለፈባቸው.....

https://press.et/?p=142392
👍2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር መልዕክት‼️

ደቡብ ኢትዮጵያን መጎብኘት እና እንደአርባምንጭ ያሉ ከተሞችን እድገት መመልከት ሁልጊዜም አስደሳች ነው።

እንደ ሀገር የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለከተሞችም ሆነ ለገጠር አካባቢዎች ፈተና ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ዛሬ በመጎብኘት ላይ እንዳለነው አይነት የሙዝ ልማት ሥራዎችን በገጠር አካባቢዎች በማሳዎች ላይ የኩታ ገጠም እርሻ አሰራረን ጀምረናል። እነዚህን ጥረቶች የሚደግፈው የሌማት ትሩፋት ሥራ በየአርሶአርብቶአደሩ ቤት የእንቁላል ምርትን ከአሳ እና ከብት ርባታ ብሎም ንብ ማነብ ጋር ምርት በማሳደግ ላይ ይገኛል።

እነዚህ መርሃግብሮች በጥምር የገጠሩ እና የከተማው ነዋሪዎች ከትሩፋቱ እንዲካፈሉ አልመው ሰርተዋል። በተለይ የኩታ ገጠም እርሻ በአርባምንጭ ታላቅ ተስፋ የሰነቀ ነው።

ህዳር 28 ቀን 2017 ዓም
👍9