Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በ2016 ዓመተ ምህረት የምርት ዘመን የስንዴ ምርት በምን ያህል ከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ያውቁ ይሆን?
አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ ገበሬዎች 3.6 ሚሊዮን ሄክታር አርሰው 123 ሚሊዮን ኩንታል ሲያመርቱ በመስኖ ከታረሰው 2.9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ደግሞ 107.7 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት ተችሏል። የ2016 የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት በድምሩ 230 ሚሊዮን ኩንታል ደርሷል።
ከ2012 የምርት ዘመን ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ ገበሬዎቹ 54 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ብቻ ነበር ያመረቱት። ዛሬ ይህ ቁጥር ትርጉም ባለው መጠን ከፍ ብሏል። ይህ እመርታ በፅኑ አመራር፣ በአስቻይ ፖሊሲዎች ብሎም ምርትን ለማሳደግ በተተገበረ ያላሰለሰ ጥረት የተገኘ ነው።
#PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ቴሌግራም https://t.me/ethpress
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
3😁1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3🔥1
2ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል
******
(ኢ ፕ ድ)

2ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የጥበብና ባህል ፌስቲቫል "ጥበብና ባህል ለቀጠናዊ ትብብር" በሚል መሪ ቃል ከጥር 15 እስከ 18 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከቀጠናው ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ለመወያየት በተዘጋጀው መድረክ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲን እንደገለፁት፤ ፌስቲቫሉ የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል።

ፌስቲቫሉን ኢትዮጵያ ማስተናገዷ የአገሪቱን ባህል አጉልቶ ለማሳየት እንደሚያስችል ጠቁመው፤ ፌስቲቫሉ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የሚሰባሰቡበት አጋጣሚን ይፈጥራል።

የመጀመሪያው የምሥራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በ2014 ዓ.ም በወዳጅነት ፓርክ ተካሄዷል።

ህዳር 27 ቀን 2017 ዓም
👍6👏1
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የወሰዱ ዜጎች ቁጥር 10 ሚሊየን ደረሰ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የወሰዱ ዜጎች ቁጥር 10 ሚሊየን መድረሱን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

የፕሮግራሙ የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አቤኔዘር ፈለቀ እንደገለጹት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሁሉን አቀፍ፣ አካታችና አስተማማኝ አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡፡

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አሰራር ሥርዓት በማዘመንና ዲጂታል በማድረግ ብልሹ አሠራርን ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ዲጂታል መታወቂያ በተለያዩ ተቋማት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው÷በቀጣይ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መታወቂያውን እንደ ቅድመ ሁኔታ እንደሚጠይቁ አንስተዋል፡፡

በቅርቡም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የባንክ አካውንት ለመክፈት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደቅድመ ሁኔታ መጠየቅ እንደሚጀመር ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በመዲናዋ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ አስገዳጅ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ድረስም 10 ሚሊየን በላይ ዜጎች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደወሰዱ ነው አቶ አቤኔዘር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የገለጹት፡፡

ስለሆነም ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የተለያዩ ማዕከላት ተመዝግበው ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

ህዳር 27 ቀን 2017 ዓም
👍9
#ውብአዲስ
የአዲስ አበባ አዳዲስ ገጽታዎች‼️
ህዳር 27 ቀን 2017 ዓም
👍108👎1
አምስቱ አውሮፕላኖች አንበጣን፣ ግሪሳንና ተባዮችን ለመከላከል ትልቅ አቅም ፈጥረዋል
******
(ኢ ፕ ድ)

የግብርና ሚኒስቴር የገዛቸው አምስት አውሮፕላኖች የአንበጣ መንጋን፣ የግሪሳ ወፍንና ድንበር ዘለል የሆኑ ተባዮች በሰብል ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ከመከላከል አኳያ ትልቅ አቅም ፈጥረዋል ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል የገዛቸው አምስት አውሮፕላኖች ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡

አውሮፕላኖቹ የጸረ ተባይ ኬሚካል ርጭት በማካሔድ የሰብል ምርቱን ከአንበጣ መንጋና ከግሪሳ ወፍ በመከላከል ረገድ ድርሻቸው የጎላ ነው፡፡ በተለይም ድንበር ዘለል የሆኑ ተባዮችን ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመፍጠር.....

https://press.et/?p=142383
👍41
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍2