በጃል ሰኚ ነጋሳ የተመሩ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)
ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ የደረሰው በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ የተመሩ የሠራዊቱ አባላት በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያንና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለውና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑን በመረዳት መንግስት ላደረገው ጥሪ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል።
ስምምነቱ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ለሌሎች አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
ጃል ሰኚ ነጋሳ በበኩላቸው፣ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የህዝብን ጉዳት ለመቀነስና የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመረዳታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
ለተደረገላቸው አቀባበል ማመስገናቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ህዳር 25 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et

👍13❤5
በጅቡቲ በችግር ውስጥ የነበሩ 94 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው መግባታቸው ተገለፀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር 94 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤምባሲው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር በመውጣት ወደ ሌላው ሀገር መግባት የሰው ልጅ ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት እንቀንስ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡
ህዳር 25 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
*******
(ኢ ፕ ድ)
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር 94 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤምባሲው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር በመውጣት ወደ ሌላው ሀገር መግባት የሰው ልጅ ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት እንቀንስ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡
ህዳር 25 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3
“እኛ ለዜጎቻችን የምናስበውን ያህል ለግብጾችም ለሱዳኖችም እናስባለን”
– ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር
******
(ኢ ፕ ድ)
“እኛ ለዜጎቻችን የምናስበውን ያህል ለግብጾችም ለሱዳኖችም እናስባለን፤ ለሁሉም የሚሻለው ባልተገባ መንገድ ወዲህና ወዲያ ማለት ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር ነው” ሲሉ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) አስታወቁ። ከዓባይ ግድብ በኋላ ብዙ የዓባይ ግድቦችን መገንባት እንደሚጠበቅም አመለከቱ።
ኢንጂነር ሀብታሙ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ሁሌም የምትከተለው የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን መርህ ነው። በምትከተለው መርህ መሠረት ለራሷ ዜጎች እንደምታስበው ሁሉ ለግብጾችም፣ ለሱዳኖችም ታስባለች፡፡
ለግብጻውያን የሚሻለው ባልተገባ መንገድ ወዲህና ወዲያ ማለት ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ጥሩውና አዋጩ መንገድ የትብብር ማዕቀፉ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ሕግ ሆኖ የጸደቀው ማሕቀፍ፤ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገሮች ማስጠለል የሚችል ትልቅ ጥላ ነው ሲሉም አስረድተዋል።
ግብጾች የዓባይ ግድብ ግንባታ እንዳይሳካ ያላደረጉትና ያልሞከሩት ጥረት አልነበረም፡፡ ዛሬ ሲታይ ግን እነርሱ ያሉት ሳይሆን እኛ ያልነው ትክክል ሆኖ ተገኝቷል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ግድቡ ሙሉ በሙሉ እነርሱን የሚጎዳ አድርገው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሲናገሩ የነበረ ቢሆንም፤ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን......https://press.et/?p=142231

👍4👎4👏1😁1
ኮሎምቢያ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሯን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሰታወቀ
👉ባለፉት ሳምንታት ከ20 በላይ ኩንያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል፣
👉በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጪ አገራት ኤምባሲዎች ቁጥር ወደ 137 ከፍ ብሏል
*
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፣በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጪ አገራት ኤምባሲዎች ቁጥር ወደ 137 ከፍ ብሏል።
በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ኮሚቴ ተቋቁሞ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጪ አገራት ኤምባሲዎች ቁጥር 137 ከፍ ማለቱን በመግለጽ በቅርቡ 24 የውጪ አገራት አዳዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤቸውን ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ አቅርበዋል ብለዋል።
አምባሳደሮቹ አገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ተናግረዋል።
ኮሎምቢያ አዲስ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሯንም ጠቁመዋል።
ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው አዲስ መነቃቃትን ፈጥሯል። ባለፉት ሳምንታት ከ20 በላይ ኩንያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል ብለዋል።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም ከማይናማር በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በሊባኖስ ለደህንነታቸው አስጊ የሆኑ 2 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በማርቆስ በላይ
ህዳር 26 ቀን 2017 ዓም

👍6❤2
በ2016 ዓመተ ምህረት የምርት ዘመን የስንዴ ምርት በምን ያህል ከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ያውቁ ይሆን?
አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ ገበሬዎች 3.6 ሚሊዮን ሄክታር አርሰው 123 ሚሊዮን ኩንታል ሲያመርቱ በመስኖ ከታረሰው 2.9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ደግሞ 107.7 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት ተችሏል። የ2016 የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት በድምሩ 230 ሚሊዮን ኩንታል ደርሷል።
ከ2012 የምርት ዘመን ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ ገበሬዎቹ 54 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ብቻ ነበር ያመረቱት። ዛሬ ይህ ቁጥር ትርጉም ባለው መጠን ከፍ ብሏል። ይህ እመርታ በፅኑ አመራር፣ በአስቻይ ፖሊሲዎች ብሎም ምርትን ለማሳደግ በተተገበረ ያላሰለሰ ጥረት የተገኘ ነው።
#PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ቴሌግራም https://t.me/ethpress

❤3😁1