Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
344 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአማራ ክልል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያልተከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሥራዎች ይከናወናሉ
********
(ኢ ፕ ድ)

በአማራ ክልል በቀጣዩ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያልተከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሥራዎች እንደሚከናወኑ ኮሚሽኑ ገለጸ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከታሕሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እንደሚካሄድ ጠቁሟል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ(ፕሮፌሰር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአማራ ክልል በወረዳ ደረጃ ተሳታፊዎችን የሚያስመርጡ ከሁለት ሺህ 200 በላይ ተባባሪዎች ሥልጠና ተጠናቋል፡፡

በክልሉ በብዙ ወረዳዎች ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎችን በመለየት አስመርጠዋል ያሉት ዋና ኮሚሽነር ፤ በቀጣዩ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቀሪ የምክክር ሥራዎችን ለማካሄድ መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡

ኮሚሽኑ አሁን ላይ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ለዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት ላይ መሆኑን ያመላከቱት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ሥራው በ9 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች መጠናቀቁን አውስተዋል፡፡

ከታሕሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ለዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ እንደሚከናወንም ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ከ350 በላይ ወረዳዎች ከሚመጡ ከሰባት ሺህ 700 በላይ ተሳታፊዎች እና ከክልሉ ባለድርሻ አካላት..... https://press.et/?p=142145
👍3
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የውይይት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስረከቡ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የውይይት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በወቅቱ እንደገለፁት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ተባባሪ አካላት ናቸው።

በዚህም የጋራ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ያፀደቀውን የውይይት አጀንዳ በዛሬው ዕለት አስረክቧል ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ የተሳታፊ ልየታ፣ መረጣና የአጀንዳ የማሰባሰብ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል።

በቀጣይ ቀናት የፌዴራል ባለድርሻ አካላትና ተቋማት መንግስትን ጨምሮ አጀንዳ እንዲያስረክቡ ይደረጋል ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ ያስረከበው አጀንዳ በጠቅላላ ጉባኤው የፀደቀ ነው። በዚህም ታሪክና ትርክት፣ የሀገርና የተቋማት ግንባታ፣ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎችን መሠረት ያደረጉ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ መግባታቸውን ተናግረዋል።

ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በጋር እንደሚሰሩ ገልፀው፤ በመተባበርና በመከባበር ሀገርን በጋራ እንገነባለን ብለዋል።

እውነተኛ ዲሞክራሲ ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን

ህዳር 25 ቀን 2017 ዓም
👍1👏1
“ብሄራዊ ጥቅምን በሚያስከብሩ ጉዳዮቻችን ላይ የጋራ አቋም መያዝ አለብን” – ኡስታዝ ጀማል በሽር
*******
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያውያን በውስጥ ግጭቶች እና ልዩነቶችን ከሚፈጥሩ አጀንዳዎች ይልቅ ብሄራዊ ጥቅምን በሚያስከብሩ አጀንዳዎች ላይ የጋራ አቋም መያዝ አለብን ሲሉ ኡስታዝ ጀማል በሽር ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ የዓባይ ጉዳይን በተመለከተ ያላትን አቋም ለአረብ ሀገራት በአረብኛ ቋንቋ በስፋት በማድረስ የሚታወቁት ኡስታዝ ጀማል በሽር እንደ ሕዝብ ብሄራዊ የሆኑ አጀንዳዎቻችን ላይ አንድ ሆነን መቆም አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኡስታዝ ጀማል ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ግብጻውያን በመሀከላቸው መከፋፈል ቢኖርም በሀገር ጉዳይ ላይ ያላቸው አንድነት ጠንካራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግብጻውያን በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ላይ የሚገኙ ፤ ረጅም ዓመት ተፈርዶባቸው በእስር የሚገኙ ዜጎቻቸው ጭምር በሀገራቸው ጉዳይ ያላቸው አቋም አንድ ከመሆኑም በላይ ጠንካራ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የዓባይ ውሃ ባለቤት ብትሆንም በዜጎች ዘንድ የሚሰጠው ትኩረት ሊሠራበት የሚገባው መሆኑንም አንስተዋል፡፡ እንደሀገር በትምህርት ሥርዓታችን ውስጥ ተተኪ ለሆኑ ትውልዶች ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብት.......

https://press.et/?p=142169
👍8
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍41
በጃል ሰኚ ነጋሳ የተመሩ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)
ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ የደረሰው በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ የተመሩ የሠራዊቱ አባላት በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያንና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለውና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑን በመረዳት መንግስት ላደረገው ጥሪ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል።

ስምምነቱ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ለሌሎች አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ጃል ሰኚ ነጋሳ በበኩላቸው፣ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የህዝብን ጉዳት ለመቀነስና የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመረዳታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ለተደረገላቸው አቀባበል ማመስገናቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ህዳር 25 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍135
#ውብአዲሲ

አዲስ አበባ በምሽት‼️
👍82