በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ዙሪያ የተዘጋጀ መፅሐፍ ተመረቀ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ለውጥ የሚያስቃኝ መፅሐፍ ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል።
“Ethiopia in the wake of political Reform” የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሀፍ በጸሐይ አታሚ የተዘጋጀ ሲሆን በውጭ አገር እና በአገር ውስጥ የፖለቲካ ምሁራን ተሳትፎ እንዳደረጉበት ታውቋል።

ዛሬ 437 ኢትዮጵዊያን ከሳኡዲ አረቢያ እና ሊባኖስ ተመለሱ
********************************
(ኢፕድ)
ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓም 437 ኢትዮጵዊያን ከሳኡዲ አረቢያ እና ከሊባኖስ ተመልሰዋል።
ከዛሬ ተመላሾች ውስጥ 393 ከጅዳ ሳኡዲ አረቢያ ሲሆን፤ 144 ደግሞ ከቤሩት ሊባኖስ የተመለሱ ናቸው።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ጉዳዩ ከሚመከታቸው መ/ቤቶች የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የ8ኛ እና የ12 ክፍል ትምህርት ጥቅምት 16 ይጀመራል፡፡
በአዲስ አበባ ዘንድሮ ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ትምህርት ይጀምራሉ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በሰጡት መግለጫ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራታቸው የመልቀቂያ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች በሁሉም የከተማዋ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ቀድመው ትምህርት ይጀምራሉ ብለዋል።
የፊታችን ሰኞ ትምህርት የሚጀመርባቸው ትምህርት ቤቶች ላይም የፀረ ተዋህሲ ርጭት መካሄዱንና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች መከናወናቸውን አቶ ዘላለም አመላክተዋል።
የሙቀት መለኪያና ጭምብልም በሁሉም ትምህርት ቤቶች በመሰራጨት ላይ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው አስታውቀዋል።
የ8ኛ እና 12 ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች 45 ቀን ከተማሩ በኋላ ለፈተና እንደሚቀመጡም የገለጹት አቶ ዘላለም በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ ያሉ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ትምህርት የሚጀምሩት ጥቅምት 30 ቀን 2013 እንደሆነም ሃላፊዉ ተናግረዋል።
ሃላፊዉ እንዳስታወቁት የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ሲባል የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ቅዳሜን ጨምሮ በሳምንት 6 ቀናት እንደሚማሩ እና የተቀሩት ክፍል ተማሪዎችም በቀን ፈረቃ በሳምንት ሶስት ቀን ትምህርት መማር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በከተማዋ 230 ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት እንደሚበቁና የተማሪዎችን የጤና የሚከታተሉ በ513 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 2052 የጤና ባለሙያዎች ቅጥር መፈፀሙን ሃላፊዉ ተናግረዋል፡፡

ለትግራይ ወረዳዎች፣ ከተማዎችና ቀበሌዎች የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሠራር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
****************************
(ኢፕድ)
ለትግራይ ወረዳዎች፣ ከተማዎችና ቀበሌዎች የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሠራር ዝግጅት ማጠናቀቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃጂ ኢብሣ እንደተናገሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ሚኒስቴሩ ለክልሉ ወረዳዎች፣ ከተሞችና ቀበሌዎች የድጎማ በጀቱን የሚያስተላልፍበትን የአሠራር ዝግጅት አጠናቋል።
በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው የበጀት ድጎማ አሠራር በሚቀጥለው ሣምንት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ተግባራዊ እንደሚደረግም ኃላፊው ጠቁመዋል።
በዚህም በጀቱ በወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ አስተዳደር አካላት የባንክ ሂሳብ በኩል እንደሚተላለፍ አስታውቀዋል።
የአስተዳደር አካላቱ የባንክ ሂሳብ ማስተላለፊያ ደብተር ካላቸው በዚያው በኩል ከሌላቸው ደግሞ አዲስ የባንክ ሂሳብ በመክፈት በጀቱ እንዲደርሳቸው እንደሚደረግም ተናግረዋል።
የትግራይ ሕዝብ እንደ ሌሎቹ የአገሪቱ ክልሎች ሕዝቦች የትምህርት፣ የጤና፣ የንጹሕ መጠጥ ውኃ፣ የምግብ ዋስትናና ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋልም ብለዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከሥራ አስፈጻሚው ጋር ያለው ግንኙነት እንዲቋረጥ መወሰኑ ይታወቃል።
ምክር ቤቱ መስከረም 26 ስብሰባ አድርጎ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የፌደራል መንግሥት “የወረዳ፣ የከተማና የቀበሌ አስተዳደሮችን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ሕጋዊ ተቋማት ጋር ብቻ የሥራ ግንኙነት ማድረግ አለበት” የሚል ውሳኔ መወሰኑ የሚታወስ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 575 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል
*****************************
(ኢፕድ)
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6,676 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 575 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 91,693 ደርሷል።
በሌላ በኩል 754 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 45,260 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በትግራይ ያጋጠመውን የአንበጣ ወረራ ለመከላከል የትግራይ ብልፅግና በአስተባበረው የገቢ ማሳባሰቢያ መድረክ ከ10ሚሊዮን ብር በላይ ተገኘ *********************************************
(ኢ.ፕ.ድ)
በትግራይ ክልል ያጋጠመውን የአንበጣ ወረራ ለመከላከል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ባስተባበረው የገቢ ማሳባሰብያ መድረክ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።
ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ “የገበሬ ህልውና የአገር ህልውና ነው” በሚል መሪ መልእክት ያስተባበረው የገቢ ማሳባሰብያ መድረክ ተካሂዷል።
በዚሁ መድረክ ላይ የትግራይ የብልፅግና ከፍተኛ አማራር ዶ/ር አብርሃም በላይ እንደተናገሩት፤ ትግራይ ላይ ያጋጠመውን የበረሃ አንበጣ ወረራ ለመመከት ያለምንም የዘር፣ የሃይማኖትና የፖለቲካ ልዩነት መስራት ይገባል።
በተዘጋጀው የገቢ ማሳባሰበያ መድረክ ላይ ከፍተኛ የትግራይ ብልፅግና አመራሮች ከደመዋዛቸው 250 ሺህ ብር መስጠታቸው ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ ባለሀብቶችና የትግራይ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አካላት መገኘታቸውንና ድጋፍ ማድረጋቸውም ተገልጿል።
በማዕረግ ገ/እግዚአብሄር
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ትክክለኛውን
ለአጫጭር ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ የትዊተር አካውንታችን ይከተሉ
https://twitter.com/home?lang=en
በጋዜጦቻችን የወጡ ዜና፣ አርቲክልና ኤክስክሉሲቭ ቃለ መጠይቆችን ዌብሳይታችን ላይ ያገኛሉ
https://www.press.et/️

በሐዋሳ ከተማ የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የኮማንዶ ትርኢት እየተካሔደ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማዘዣ በአምስት ሻለቃ ያሰለጠናቸው የኮማንዶ አባላት የልዩ ግዳጅ ትርኢት እያሳዩ ነው።
በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፓሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በትርኢቱ የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የአየር ወለድ አባላት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢ ከሔሊኮፒተር የፎቅ ዝላይ በማድረግ የጸረ ሽብርና ጥቃት ትዕይንት አሳይተዋል።
በቶጋ፣ በወንዶ ጢቃና በወንዶ ገነት አካባቢ የሜዳና የገደል ዝላይ፤ ከሒሊኮፒተር በፓራሹት በመውረድ ትዕይንቱን እያሳዩ ነው።
የልዩ ሀይል ፀረ ሽብር ስልታዊ ተኩስ ትርኢትም በዝግጅቱ እየታየ ይገኛል።
በሌላ በኩል በልዩ ዘመቻዎች ሀይል የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላት የባህር ላይ ትርኢት በልዩ ሁኔታ እያቀረቡ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማዘዣ በአምስት ሻለቃ ያሰለጠናቸውን የኮማንዶ አባላት ነገ እንደሚያስመርቅ ኢዜአ ዘግቧል።

የመንግሥትም ሆኑ የግል ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ብቻ እንደሚማሩ ተገለጸ
*******************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- የመንግሥትም ሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ከጥቅምት 30 ጀምረው በቀናት ፈረቃ ሰኞ፣ ረዕቡ እና ዓርብ ሌሎቹን ደግሞ ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ ብቻ እንደሚያስተምሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እንደተናገሩት፤ ትምህርት የሚጀመረው በሁለት ዙር ነው። የመጀመሪያው ዙር የ8ኛ ክፍል የክልል ፈተና፣ የ12 ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተናን ለማካሔድ ከጥቅምት 16 ቀን እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ያለፈረቃ ሳምንቱን ሙሉ የክለሳ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል። ይህ ለፈተና እንዲዘጋጁ ያመለጣቸውን እንዲማሩ ለማድረግ ነው።
ሁለተኛው ዙር ማለትም ቀሪዎቹ ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ የሚማሩ ሲሆን፤ ይህ የሆነው ከአዋጭነት አንፃር ታይቶ መሆኑን አስረድተዋል። ቀድሞ ጠዋትና ከሰዓት በሚል ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የቀናት ፈረቃ የተሻለ ይሆናል ተብሎ ውሳኔ የተላለፈው ምልልሱን፣ መውጣት መውረዱን፣ የትራንስረፖርት ሁኔታን፣ ወጪውን እና ለወላጆች ያለውን አመቺነት ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አብራርተዋል።
በቀሪዎቹ ቀናት ተማሪዎቹ ለብቻቸው ከንክኪ ነፃ ሆነው በቤታቸው መልመጃዎችን እና የቤት ሥራዎችን እንደሚሠሩ እንዲሁም ጥናት እንደሚያከናውኑ ታሳቢ መደረጉን ጠቅሰው፤ በፈረቃ ሲማሩ እንደየክፍሉ ስፋት በክፍል ውስጥ የሚኖራቸውን ንክኪ ለመቀነስ ቁጥራቸው ከ20 እስከ 25 ብቻ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
አቶ አዲሱ እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች ተራርቀው እንዲማሩ አሁን ባሉት ክፍሎች ላይ ተጨማሪ 2ሺህ 300 ክፍሎች እንደሚያስፈልጉ ታውቋል። ሆኖም በአዲስ አበባ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በትምህርት ቤቶች ግቢም ሆነ በአካባቢያቸው በቂ ይህን ያህል ክፍሎችን የመገንቢያ ቦታ ባለመኖሩ 1ሺህ 720 ክፍሎችን በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመገንባት ዲዛይኑ ተከናውኖ፤ ውል የተገባ ሲሆን፤ ግንባታውን እስከ ጥቅምት 30 ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
የከተማ አስተዳደሩ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ቢያንስ ሁለት ሁለት የሙቀት መለኪያ በልዩ ሁኔታ በቀጥታ ግዢ እንዲከናወን ውሳኔ ያስተላለፈበት ሁኔታ መኖሩንም ገልጸው፤ ከጤና ቢሮ ጋር በመግዛት ለትምህርት ቤቶች ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል። አያይዘውም ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክፍለ ከተማ እና ከትረስት ፈንድ በማፈላለግ እያንዳንዱ ተማሪ ማስክ እንዲያገኝ ጥረት መደረጉን በመጠቆም፤ ማስኩ ለሁሉም እንደሚዳረስ አመልክተዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ዩኒፎርም መስጠት እና ምገባ ማከናወን እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ዕድሳት ላይ በመሥራት ታሪካዊ ውሳኔዎች ተላልፈዋል በማለት ያስታወሱት አቶ አዲሱ፤ ዘንድሮ ደግሞ ትምህርቱ ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ የትምህርት ጤና (school health) ፕሮግራም እንደሚተገበር ጠቁመዋል።
በትምህርት ዘርፉ ላይ የተማሪዎች የጤና ክትትልን ለማካሄድ በካቢኔው ልዩ ውሳኔ 2ሺህ 52 በአካባቢ ጥበቃ እና በጤና ላይ የሚሠሩ ነርሶች በኮንትራት እንዲቀጠሩ በመፈቀዱ ቅጥር እየተፈፀመ ነው ብለዋል።
ውሳኔው ጤናማ ተማሪዎች በጤናማ አካባቢ እንዲማሩ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ የከተማው አስተዳደር ከሁሉም ጉዳይ በላይ ለትምህርት ትኩረት ሰጥቶ እየደገፈ በመሆኑ ትምህርቱን እየዘመነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 13/2013
ምህረት ሞገስ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/ethpress

Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጪው ሳምንት ይጀመራል፡፡
--------------------------------------------
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30 /2013 ዓ.ም በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የፈተና ምዝገባ ሂደቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማካሄድ በተዘጋጀው ሶፈትዌር “Enrollment Kit” ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የአይ ሲ ቲ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በየክልል ከተሞች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በመላው ሀገሪቱ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሷል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በመላው ሀገሪቱ ዛሬ (ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም) ከረፋዱ 5 ሰአት ጀምሮ ለተወሰኑ ሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሷል።
የኃይል ማመንጫዎችን ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር መልሶ የማገናኘት ሥራው በስኬት በመጠናቀቁ ደረጃ በደረጃ ሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ተደርጓል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ህድብ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ትችት እያስከተለባቸው ነው
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ምሽት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ህድብ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ከተለያዩ ወገኖች ትችት እያስከተለባቸው ነው።
የዴሞክራት ፓርቲ ኮንግረስማን የሆኑት የኮሎራዶው ጃሶን ክሮው በትዊተር ገፃቸው ፕሬዝዳንቱ ግድቡን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ ሀላፊነት የጎደለው እና መረጃ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል::
ሚስተር ክሮው በዚሁ መልዕክታቸው አሜሪካ ሚዛናዊ አደራዳሪ በመሆን ዛላቂ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈጠር መስራት እንዳለባት በመጥቀስ የውጭ እርዳታን ማገድ የለባትም በማለት የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተችተውታል።

"ማንም ገዝቶን አያውቅም። ወደፊትም ማንም አይገዛንም። ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም። ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም"
- ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ በፍጣሪዋ ታምና በሕዝቧ አንድነትና ጽናት የቆመች ሀገር ናት። ጥቂት ሰጥተው ብዙ ሊያዟት በሚሞክሩ ተማምና አታውቅም። ሕይወታቸውን ሰጥተው ሊታዘዟት በተዘጋጁ ልጆቿ እንጂ። ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ነው። የገነቧት ደግሞ ልጆቿ ናቸው። እነዚህ ልጆቿ በከፈሉት መሥዋዕትነት ዓለምን ጉድ ያሰኙ ታሪኮችን ሠርታለች። እነዚህን አስደናቂ ታሪኮችን ስትሠራ አብረዋት ታሪክ የሠሩ ወዳጆች ነበሯት። የከዷት ወዳጆችም ነበሩ። ይህ ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም።
ነገር ግን የዓለም ታሪክ ያረጋገጣቸው ሁለት ሐቆች አሉ። ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም የሚለው ቀዳሚው ነው። ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለአንድ ዓላማ ከቆሙ ድል ማድረጋቸው አይቀርም የሚለው ደግሞ ሁለተኛው። የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ግድብ ነው። ኢትዮጵያውያን፣ አሰቡት፤ ኢትዮጵያውያን ጀመሩት፤ ኢትዮጵያውያን ገነቡት፤ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ይጨርሱታል። አይቀሬ ነው።
የሚያዋጣን ኅብረት አንድነታችን ነው። ለእኛ ያለነው እኛ መሆናችንን ዐውቀን ስለ እኛ ጉዳይ እኛው ራሳችን ኢትዮጵያን አለንሽ እንበላት። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን ለኢትዮጵያ እንቁም። ከባዱ ፈተና ከውጭ የሚመጣው አይደለም። ከባዱ ፈተና ተለያይተን ችግሩን ከተጋፈጥነው ነው።
ማንም ገዝቶን አያውቅም። ወደፊትም ማንም አይገዛንም። ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም። ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም።
ክንዳችንን እናበርታ። ትከሻችንን እናስፋ። ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር።
በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ እንቀርም። ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም። አንድ ሆነን የምንይዘው ጋሻ ኃያላኑን ሁሉ ሲመክት የኖረ ነው። ዛሬም ያንን ጋሻ በአንድነት እናንሣ። ሁላችንም፣ በየቦታችን፣ 24 ሰዓት፣ ለኢትዮጵያ እንቁም።

በዚህ አመት 5 ሚሊዬን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል:- ትምህርት ሚኒስቴር
------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በBiometric Digital Registration በመጪው ሰኞ እንደሚጀመር አስታውቃል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ የመጀመሪያዎቹ 450ሺ ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ እንደሚኖራቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ገለፀዋል።
በዚህ አመት ደግሞ 5 ሚሊዬን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል ብለዋል።
የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማድረግ አንዱ አካል ነው።

ኢትዮጵያውያን በፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር አይሸበሩም ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያውያን በፕሬዝዳንት ትራምፕ የትናንት ምሽት ንግግር ፈጽሞ አይሸበሩም ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ የትናንት ንግግር ሀላፊነት የጎደለው ነው ሲሉም ነው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የተናገሩት።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለሚናገሩት ጉዳይ ግንዛቤ እንደሌላቸው አቶ ኃይለማርያም ገልጸዋል።
አቶ ኃይለማርያም በዚሁ መልዕክትቸው፤ "ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን እንዲህ ባለ ሀላፊነት በጎደለው ንግግር አይሸበሩም፤ ታሪክ ሁሉንም ያስተምራል" ሲሉም ሀሳባቸውን ቋጭተዋል።

የፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ለግብጽ የወገነና ኢትዮጵያዊያንን በአግባቡ ካለማወቅ የተሰነዘረ ነው ሲሉ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አስታወቁ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አስተያየት ለግብጽ ወገንተኝነት የታየበት፣ ስለግደቡ ትክክለኛ መረጃ እንደሌላቸው እና ኢትዮጵያዊያንን በአግባቡ እንደማያውቁ የተያበት ነው ሱሉ የታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን የትናንት ምሽት ንግግር ተከትሎ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ የሰጡት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ እንደተናገሩት፤ የፕሬዝዳንቱ አስተያየት አሜሪካ ለግብጽ ያላትን ወገንተኝነት ዳግም በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል።
የፕሬዝዳንቱ ንግግር ከአንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚጠበቅ አይደለም ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ንግግራቸው ለግብጽ ያላቸውን ወገንተኝነት በግልጽ ያሳየ ነው። ይሄ ደግሞ የሆነው አገራቸው ከእስራኤል እና ከግብጽ ጋር ካላት ግንኙነት ጋር ይያያዛል ሲሉም ነው ያብራሩት።
"ግድቡ የተጀመረውና እዚህ የደረሰው በህዝብ ድጋፍ ነው፤ ዳር የሚደርሰውም በህዝብ ድጋፍ ነው፤ አሁንም ከተባበርን ይሄን አይደለም ሌላ ግድብ መስራት እንችላለን” ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ለግድቡ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ በአግባቡ እንዳልተረዱት ንግግራቸው ያሳያል ብለዋል።
ኢትዮጵያን የወረረው ጣሊያን አድዋ ላይ ድል የተነሳው በኢትዮጵያዊያን ትብብር እንጂ በውጭ ሀይል ድጋፍ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ አሁንም ከ70 በመቶ በላይ የደረሰን ግድብ ለማጠናቀቅ የሚያቆመን ምንም አይነት ሀይል የለም ሲሉ ነው የመንግስትንና የህዝቡን የትብብር መንፈስ ያስረዱት።
አንድ አንዱ ንግግራቸው ኢትዮጵያን በውል ካለማወቅ የመነጨና ኢትዮጵያዊያንም አገራቸውንና ድንበራቸወን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ካለመገንዘብ የተነሳ የሰጡት ሃሳብ ስለሆነ እንደ እርሳቸው አይነት ካላ ፕሬዝዳንት የሚጠቅ ንግግር ነው ሲሉም ነው ዶ/ር አረጋዊ
የተናገሩት።
ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ የጀመረችው ለጋራ ተጠቀሚነት መሆኑ እየታወቀ የዚህ አይነት ማስፈራሪያ መሰንዘር ፋይዳ የሌለው መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር አረጋዊ፤ ኢትዮጵያዊያን በዛቻና ማስፈራሪያ የማይንበረከኩ መሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል ሲሉም ነው የፕሬዝዳንቱን ንግግር የተቹት።
“በውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ተበብረን ግድቡን ከዳር ለማድረስ መፍትሄው በእጃችን ነውና አሁን ካለውም በላይ መተባበር አለብን” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት ሲፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ አመት ያህል የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት ሲፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የሀይል ስርቆቱ ሲፈፀም የቆየው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ዮቴክ ኮንስትራክሽን ህንጻ አካባቢ ነዉ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ እንዳስረዱት፤ ተጠርጣሪው ግለሰብ በእንጀራ ንግድ ላይ የተሰማራ ሲሆን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንብ እና አሰራር ውጪ የኤሌክትሪክ ሃይል ከቀጥታ መስመር በመቀጠል ለ አንድ አመት ያለአግባብ ሲጠቀም ቆይቷል፡፡
ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ እና መረጃው ከፖሊስ የደረሳቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቁጥጥር ሰራተኞ ወደቦታው ሄደው ባደረጉት ማጣራት ግለሰቡ በገንዘብ ሲተመን 55 ሺ 668 ብር ከ05 ሳንቲም በድርጅቱ ላይ ጉዳት ማድረሱን እና ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ ገልፀዋል፡፡
ድርጊቱ አስከ 5 አመት በሚደርስ እስራት እና እስከ 20ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተገልጿል።

እገዳ የተጣለበት ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት:- ትምህርት ሚኒስቴር
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመከተል እና ወላጆች ባቀረቡት ተደጋጋሚ ቅሬታ እገዳ ከተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የግሪክ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት፡፡
እገዳው የተነሳው ትምህርት ሚኒስቴር ባቋቋመው ቡድን ባደረገው የሱፐርቪዝን ስራ መሰረት ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን መስተካከያ በማድረጉ እና ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት በማጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ትምህርት ቤቱም ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስራውን ማከናውን እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ሌሎች ትመህርት ቤቶችም ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያ በመከተል የመማር ማስተማር ሄደቱን ማስቀጠል እንዳለባቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡