በትግራይ ክልል የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ 640 የቀድሞ ታጣቂዎች ማህበረሰቡን ተቀላቀሉ
***
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል በመቀሌና ዕዳጋ ሀሙስ ማዕከላት ትጥቅ በመፍታት፣ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ በማስረከብ የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ 640 የቀድሞ ታጣቂዎች ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ መደረጉን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።
በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የዲሞብላይዜሽን ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ጎሳዬ ጥላሁን፤ በትግራይ ክልል በመቀሌና ዕዳጋ ሀሙስ የስልጠና ማዕከላት 640 የቀድሞ ታጣቂዎች ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ መደረጉን ገልጸዋል።
በስልጠና ማዕከላቱ 1ሺህ 360 የቀድሞ ታጣቂዎች የዲሞብላይዜሽን ሂደት ላይ ሲሆኑ በቀጣይ ወደ ማህበረሰቡ የሚቀላቀሉ መሆኑን ተናግረዋል።
በዲሞብላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም መርህ መነሻነትም ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የተሃድሶ ስልጠና መስጫ ማዕከላትን የቅበላ አቅም በማሳደግ በተቻለ ፍጥነት የቀድሞ ታጣቂዎች መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የቀድሞ ታጣቂዎች መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ ለማስቻል በሚደረገው ጥረት የፌዴራል መንግስት እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋማትና የስራ ኃላፊዎች ገንቢ ሚና እየተወጡ መሆኑን ገልጸው፤ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍና አጋርነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ከመንግስት፣ ከተባባሪና ለጋሽ አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሚቀጥሉት አራት ወራት 75 ሺህ የትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በሰባት ክልሎች በ1ኛ ዙር 75 ሺህ፣ በ2ኛ ዙር 100 ሺህ፣ በ3ኛው ዙር 150 ሺህ እንዲሁም በ4ኛው 46 ሺህ፤ በድምሩ 371 ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎችን የትጥቅ ማስፈታትና መልሶ የማቋቋም ስራ ይከናወናል።
የፌደራል መንግስት፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአሕጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ኅዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀሌ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት መካሄዱ ይታወቃል።
ህዳር 24 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et

👍3
በትግራይ ክልል 70 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል
********
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል በበጋ መስኖ 70 ሺ ሄክታር መሬት ለማልማት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ የግብርና ቢሮ የሆርቲካልቸር ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በቂ የሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ማዳበሪያም እየቀረበ መሆኑን አመለከተ።
የጽህፈት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ሃይሌ ታደለ ለኢፕድ እንዳስታወቁት ፤ በ2017 ዓ.ም 70 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት እቅድ ተይዟል፤ በዚህም ሁለት 228 ሺህ 905 ዜጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።
እስካሁንም ከእቅዱ 27 ነጥብ አምስት በመቶ በዘር ለመሸፈን መቻሉን ያመለከቱት ኃላፊው ፤ በቀሪዎቹም ቦታዎች የመስኖ ልማትን ለማካሄድ የማሳ ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በክልሉ የመስኖ ልማት የክላስተር አመራረት በመጠቀም በተለይ በጎመን፤ በድንች፤ በበርበሬ፤ በቲማቲም እና በሽንኩርት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ያሉት አቶ ሃይሌ ፤ በዘንድሮ ዓመት አንድ ሺህ 400 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ለማልማት እቅድ መያዙን......https://press.et/?p=142120

👍2
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍4❤2👏1
የትላንቷ "ፀሐይ" አውሮፕላን‼️
✍️ "ፀሐይ" ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት በኢትዮጵያ የተሰራች ብቸኛ አውሮፕላን ናት ፣
✍️ የ1930ዎቹ የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ጥረት ማሳያ ናት፣
✍️ "ፀሐይ" አውሮፕላን ከጣሊያን በየካቲት ወር 2016 ዓም ወደ ሀገሯ ተመልሳለች፣
የዛሬዋ "ፀሐይ 2" አውሮፕላን‼️
✍️ ''ጸሐይ 2 '' የተሰኘችና በአየር ኃይል የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ሆናለች፣
✍️ አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ናት፣
✍️ በኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ላይ ለዕይታ በቅታለች
በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት ወደ ሮም ተወስዳ የነበረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጣሊያን መንግሥት ጋር በተደረሰ ስምምነት ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ መረከባቸው ይታወሳል።
ህዳር 24 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
✍️ "ፀሐይ" ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት በኢትዮጵያ የተሰራች ብቸኛ አውሮፕላን ናት ፣
✍️ የ1930ዎቹ የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ጥረት ማሳያ ናት፣
✍️ "ፀሐይ" አውሮፕላን ከጣሊያን በየካቲት ወር 2016 ዓም ወደ ሀገሯ ተመልሳለች፣
የዛሬዋ "ፀሐይ 2" አውሮፕላን‼️
✍️ ''ጸሐይ 2 '' የተሰኘችና በአየር ኃይል የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ሆናለች፣
✍️ አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ናት፣
✍️ በኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ላይ ለዕይታ በቅታለች
በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት ወደ ሮም ተወስዳ የነበረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጣሊያን መንግሥት ጋር በተደረሰ ስምምነት ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ መረከባቸው ይታወሳል።
ህዳር 24 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍9❤2
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ በጥራት እና በፍጥነት ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የተገኙ ልምዶችን ቀምረን የጀመርነው 2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች አገልግሎት ክፍት ማድረግ በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት፣ ከኮንትራክተሮች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተወያይተናል።
በውይይታችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከመጀመሪያ ዙር አንጻር ሰፊ እና የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በትብብር፣ በተያዘለት ጊዜ፣ በጥራት እና ስታንዳርዱን ጠብቀው እንዲያጠናቅቁ ተግባብተናል።
በትራፊክ መጨናነቅ እና አንዳንድ ምቾት በማይሰጡ ጊዜያዊ ሁኔታዎች የተንገላታችሁ የከተማችን ነዎሪዎችን ይቅርታ እየጠየቅኩ፣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በውጤቱ እንደምንክሳችሁ ቃል ለመግባት እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

👍7❤3
ለዓባይ ግድብ ግንባታ ከ311 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ለዓባይ ግድብ ግንባታ ከ311 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ግድቡ ከተጀመረ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ ከ20 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን ዳንኤል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2017 በጀት ዓመት አራት ወራት ለግድቡ ግንባታ ከ311 ሚሊዮን 573 ሺህ ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡
የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት 97 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፤ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ቦንድ በመግዛትና በተለያዩ ዌብ ቤዝድ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ላይ በተመሳሳይ ከየትኛውም አካባቢ የሚገኝ ዲያስፖራም ይሁን ሀገር ውስጥ የሚገኝ ዜጋ አፕሊኬሽኑን በማውረድ እና ስልካቸው ላይ በመጫን በየጊዜው መደገፍ ይችላሉ ብለዋል፡፡
በሀገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቦንድ በመግዛት፣ በ8100 ላይ A ብለው በመላክ፣ የኢትዮዳይሬክት የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
ዓባይ ግድብ የወል ትርክት በመሆኑ እንድነታችንን ከሚያጠናክሩ እሴት መካከል አንዱ የታሪክ አሻራ ነው ብለዋል፡፡
በሄለን ወንድምነው

👍12👏1
በአማራ ክልል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያልተከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሥራዎች ይከናወናሉ
********
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ ክልል በቀጣዩ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያልተከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሥራዎች እንደሚከናወኑ ኮሚሽኑ ገለጸ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ከታሕሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እንደሚካሄድ ጠቁሟል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ(ፕሮፌሰር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአማራ ክልል በወረዳ ደረጃ ተሳታፊዎችን የሚያስመርጡ ከሁለት ሺህ 200 በላይ ተባባሪዎች ሥልጠና ተጠናቋል፡፡
በክልሉ በብዙ ወረዳዎች ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎችን በመለየት አስመርጠዋል ያሉት ዋና ኮሚሽነር ፤ በቀጣዩ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቀሪ የምክክር ሥራዎችን ለማካሄድ መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡
ኮሚሽኑ አሁን ላይ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ለዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት ላይ መሆኑን ያመላከቱት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ሥራው በ9 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች መጠናቀቁን አውስተዋል፡፡
ከታሕሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ለዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ እንደሚከናወንም ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ከ350 በላይ ወረዳዎች ከሚመጡ ከሰባት ሺህ 700 በላይ ተሳታፊዎች እና ከክልሉ ባለድርሻ አካላት..... https://press.et/?p=142145

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የውይይት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስረከቡ
******
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የውይይት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በወቅቱ እንደገለፁት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ተባባሪ አካላት ናቸው።
በዚህም የጋራ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ያፀደቀውን የውይይት አጀንዳ በዛሬው ዕለት አስረክቧል ብለዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ የተሳታፊ ልየታ፣ መረጣና የአጀንዳ የማሰባሰብ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል።
በቀጣይ ቀናት የፌዴራል ባለድርሻ አካላትና ተቋማት መንግስትን ጨምሮ አጀንዳ እንዲያስረክቡ ይደረጋል ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ ያስረከበው አጀንዳ በጠቅላላ ጉባኤው የፀደቀ ነው። በዚህም ታሪክና ትርክት፣ የሀገርና የተቋማት ግንባታ፣ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎችን መሠረት ያደረጉ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ መግባታቸውን ተናግረዋል።
ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በጋር እንደሚሰሩ ገልፀው፤ በመተባበርና በመከባበር ሀገርን በጋራ እንገነባለን ብለዋል።
እውነተኛ ዲሞክራሲ ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሳሙኤል ወንደሰን
ህዳር 25 ቀን 2017 ዓም

👍1👏1